Get Mystery Box with random crypto!

የቀጠለ... #ቃልም_ሥጋ_ሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር ለምን መጣ? 11. ወንጌል ለ | 🗣ወንጌል ለአለም ሁሉ

የቀጠለ...

#ቃልም_ሥጋ_ሆነ


ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር ለምን መጣ?



11. ወንጌል ለመስበክ

“የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ፦ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ። መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብም የነበሩት ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር። እርሱም፦ ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ ተፈጸመ ይላቸው ጀመር። ”
ሉቃስ 4፥17-21

“እርሱ ግን፦ ስለዚህ ተልኬአለሁና ለሌሎቹ ከተማዎች ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እሰብክ ዘንድ ይገባኛል አላቸው።”
ሉቃስ 4፥43

12. ፍርድን ለማድረግ

“ኢየሱስም፦ የማያዩ እንዲያዩ የሚያዩም እንዲታወሩ እኔ ወደዚህ ዓለም ለፍርድ መጣሁ አለ።”
ዮሐንስ 9፥39

13. ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ለመስጠት

“እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”
ማርቆስ 10፥45

“መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።”
ቲቶ 2፥14

14. ሕግንና ነቢያትን ለመፈጸም

“እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።”
ማቴዎስ 5፥17

15. ለኃጢአተኞች የእግዚአብሔርን ፍቅር ለመግለጥ

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
ዮሐንስ 3፥16


ይቀጥላል...

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

SHARE SHARE SHARE
   JOIN US

@christ_mossion
@christ_mossion
@christ_mossion