Get Mystery Box with random crypto!

በክርስቶስ ( in christ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ cgfsd — በክርስቶስ ( in christ)
የቴሌግራም ቻናል አርማ cgfsd — በክርስቶስ ( in christ)
የሰርጥ አድራሻ: @cgfsd
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 464
የሰርጥ መግለጫ

Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-01 09:27:48 ኢየሱስ ክርስቶስ የቅርብ ወዳጅ ስለሆነን ነው ፤ የእግዚአብሔርን ቤተሰብ የተቀላቀል ነው።
120 viewsFilimon Nega, edited  06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 21:56:49 ( ታላቅ አባትነት )


በዛን ሰሞን የተለቀቁ የማህበሩ አባላት ፅሁፍ እና ግጥም ላይ ክርክር እና ወይይት ይዘናል ። ለተዘጋጀው የስነፅሁፍ ምሽት የምናቀርባቸውን ስራዎች ከመቅረባቸው በፊት ለብቻችን ሂስ እየተራጨን ነበር ። ልንጨርስ ዳር ዳር ስንል በመሃል ግን ተባራሪ ወሬ እና ሀሳብ ተነሳ ... ጉዳዩ ከሰሞኑን በማህበሩ የቴሌግራም ግሩብ ውስጥ በማይታወቅ ስም እየተለቀቀ ያለ ግጥም አለ እና የማን ነው የሚል ነበር ። የማን እንደሆነ ውስጤ አውቆታል ቢሆንም ቢሆንም ቢሆንም እንዲሉ ሀምሳ አለቃ ገብሩ እኔም ባላወቀ በቢሆንም አንዳችም ትንፍሽ ሳልል ተከታተልኳቸው ። በመጨረሻም እጣ ሳይጣጣሉ ማን እንደሆነ ታወቀ ወደ ተባለ ሰው የሁሉም ትኩረት ዞረ ። ግጥሞቹ የሚፃፉበት አዲሱ ስም እንደዚህ ይሰኛል " ታላቅ አባትነት" ። ታላቅ አባትነት እንደ ነፃ ትግል ብዙ አሟገተ ። ታላቅ አባትነት የሚገልፀው አብን እንደሆነ ተረድቻለው ደግሞም ነው ከአብ በላይ አባትነት ይኖራል እንዴ ??

ሐዋሪያው ጳውሎስ የአብን ታላቅ አባትነት አጠር ባለ ሀረግ እንዲህ ይገልፀዋል " የክብር አባት " (ኤፌ1:17) ....የክብር አባት የከበረ አባት ነው እንደማለት ነው ።

አሁንም ጳውሎስ በዛው በኤፌሶን ላይ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ ይላል (ኤፌ 3:14) ። ስለ መንበርከኩ ያስረዳል ዝም ብሎ ተንበርካኪ ወይም ትርጉም የሌለው መንበርከክ ሳይሆን ትርጉም ሊሰጥ በሚችል ፊት ነው በጉልበቱ የተንበረከከው ።ይሔን የፃፈው በእስር ቤት ነው ፤እናም ከእስር ቤት መንበርከክ ማለት ከባድ ነገር ነው ። እስር ቤት ሆነ የትም የጳውሎስ ጉዳይ መንበርከኩ በሰው አይደለም ፣ በአለቆች፣ በራሱ ፊትም አይደለም የሚንበረከከው እሱ በሰማይ እና በምድር አባትነት ከሚሰየምበት ከአብ ፊት ነው ።በሰማይ እና በምድር አባትነት ከሚሰየምበት ማለት አባትነት በሰማይም ሆነ በምድር የሚጀምረው ከአብ ነው ። አባት ማለት መገኛ ምንጭ ማለት ነው ።ስለዚህ ከአብ ነው ለምድር ቢሆን አባትነት የመነጨ ። ታዲያ ይሔ በሰማይም ሆነ በምድር አባትነት የሚሰየመው የሚጀምረው ከአብ ከሆነ የአብ አባትነት ታላቅ ነው ። ታላቅ አባትነት !!!ካሉስ ቢሆን ይሔ ነው ።

...... ነገር በ3 ምስክር ይፀናል ካሉ አይሁድ በህጋቸው መሰረት እኛም አንድ ጨምረን የአብ አባትነትን ከጳውሎስ እንመልከት ።

.....
በሮሜ (ሮሜ 8:15) ላይ እንደሚነግረን ማንም ፍጥረታዊ ሰው አብን አባቴ የማለት ብቃቱም ድፍረቱም የለውም ። አብን አባ የማለት አቅሙ ያለው በውስጡ መንፈስ ቅዱስ ያደረ እና መንፈስ ሲረዳው ብቻ ነው ሊል የሚችለው ። የመፀሀፍ ቅዱስ አስተማሪዎች እንደሚናገሩት አሁን የጠቀስነው አብ አባቴ የሚለው ቃል በግሪከኛ አባ አባዬ ብሎ ይተረጎማል ይላሉ ። አባ አባዬ ደግሞ ሁለት መጠሪያ ነው ልክ ንጉሰ ነገስት ተብሎ ከንጉስ እንደሚልቅ ሁሉ አብ አባዬ የላቀ አባትነት ያሳያል ይላሉ ። ታዲያ አባ አባት ታላቅ አባትነት ነው ማለት ነው ። መንፈስ ቅዱስ ይሔን ታላቅነት አባትነት በልብ ውስጥ ያሰርፀዋል ፣ ያፈሰዋል እንድናጣጥም በልባችን ያጥነዋል ያኔ አባ እንላለን አፉን እንደሚፈታ ህፃን እየተኮላተፍን አብን እንጠራለን ።

...........

የፍቅር ሐዋሪያው ዩሀንስ ደግሞ የአብን ታላቅ አባትነት በፍቅር ይገልፀዋል ።እንደ ዩሀንስ አባባል " የአባት ፍቅር " ። 1ዩሀ3:1) ... በዚህ ታላቅ አባትነት ወይንም ለአብ ልጆች ልንባል እንዴት አይነት ፍቅር አየን ። እኛን ልጆች ለማድረግ አብ ህመምን ታሟል ማለትም አንድ ብቻ ልጅ አለው እሱ ኢየሱስ ነው ።ኢየሱስ ውድ ልጁ ነው ። እኛን ለማዳን ውድ ልጁን ሰጠ ..ልጅ ሲሰጥ ቀላል አይደለም ህመም አለው ።ፍቅር ነዋ ልጅ ነዋ ። እና እኛን ልጅ ያረገን ይሔን አልፎ ነው ታዲያ እንዴት ያለ ፍቅር ነው??አዎ ይሔ አባትነት ነው ታላቅ አባትነት ።

ሊሰመርመት የሚገባው እኛ የፀጋ ልጆች ነን ኢየሱስ ግን የባህሪ አምላካዊ ልጅ ነው !!!


ታላቅ አባትነት


ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
116 viewsFilimon Nega, 18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 19:27:45 ጵራቅሊጦስ ( አፅናኙ መንፈስ ቅዱስ) በምድር ላይ ለቅዱሳን አለኝታ ነው ።

ጵራቅሊጦስ (ጠበቃው ኢየሱስ) በሰማይ ለቅዱሳኑ አለኝታ ነው።
115 viewsFilimon Nega, 16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 14:32:25 የዩሀንስ ወንጌል ጥናት


ክፍል 5: በኋላ ያለው በፊት ነበር
(ዩሀንስ 1:15)

ህይወትን መረዳት !!!

በፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
261 viewsFilimon Nega, 11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 13:36:47 #ከአባቱ እቅፍ እሰከ #አባቱ ቀኝ ያለው ርቀት በትኩረት ሲታይ #ሰው የሆነው #ስጋ የለበሰው ላይመለስ ለዘላለም ነው #በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ #ሳይቆጥር እንደተጣለ #ራሱን ባዶ ባዶ አድርጎ #ባሪያ መስሎ ወርዶ ወርዶ #ከፍ ከፍ አረገው አባቱ #ከስም ሁሉ በላይ ስም ሰጠው #የእኔ ነው የእኔ ነው የምለው #ኢየሱስ ብቸኛ ጌታ ነው ።


(በረከት ደጀኔ)
127 viewsFilimon Nega, 10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 11:20:25 በተስፋው ደስ ይለናል !! የተባረከው ብሩኩ ተስፋ ኢየሱስ ነውና ።
115 viewsFilimon Nega, 08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 11:19:43 ..... ኢየሱስን ብቻ የሚያሳውቅ #የሰማይ ነገር እያብራራ #ዛሬም በእኛ ዘመን የሚሰራ

መንፈስ ቅዱስ
111 viewsFilimon Nega, edited  08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 18:42:28 ያልተረጋጋውን የወጣቶችን ዓለም በወንጌል እውነት ማረጋጋት ለወጣቶች እጅግ መልካም ከመሆኑ በላይ በጨለማ እንዳይዋጡ እንረዳቸዋለን ።

ኢ/ር ሙላት በፀጋው
127 viewsFilimon Nega, 15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 07:31:13 ( የዩሀንስ ወንጌል ጥናት)


ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው !!


የዩሀንስ ወንጌል ከአራቱ የወንጌል መፀሀፍት አንዱ ነው ። አራቱ ወንጌላት :-
ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ ፣ዩሀንስ ናቸው ። እነዚህ አራቱ ወንጌላት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወት ፣ ያስተማራቸውን ፣የተናገራቸውን የሚናገሩ ናቸው ። ሶስቱ ወንጌላት (ማቴዎስ፣ማርቆስ፣ ሉቃስ) በብዛት የአፃፃፋቸው ፣ የአተራረካቸው፣ አጀማመራቸው ይመሳሰላል ። ሶስቱም ወንጌላት ስለ ኢየሱስ መናገር የጀመሩት ከኢየሱስ ወልደት በመጀመር ነው ይሔ ማለት ኢየሱስ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ነው እና እነዚህ ወንጌላት ከፍፁም ሰውነት በመነሳት ይፀፋሉ ። የዩሀንስ ወንጌል ደግሞ ከሶስቱ ወንጌል አተራረኩ ለየት ይላል ።የሚያተኩረው እንደ ሶስቱ ወንጌላት ከፍፁም ሰውነቱ በመነሳት ሳይሆን ፍፁም አምላክነት ላይ በመነሳት ይተርካልናል ።

የዩሀንስ ወንጌል የተፃፈው ከሶስቱም ወንጌል መጨረሻ ላይ ነው ። ጊዜው አዲስ ትውልድ እየመጣ ስለሆነ የጌታችን ኢየሱስ ማንነት እንዲያውቁ በማሰብ ነበር የተፃፈው ።

#ዩሀንስ ወንጌል የተፃፈበት ዋነኛው ዓላማ ሰዎች የኢየሱስ ስም በማመን የዘላለም ህይወት እንዲያገኙ ነው ። ዩሀንስ የዘላለም ህይወት የሚገኘውን መንገድ ነው የፃፈው ...የዘላለም ህይወት የሚገኘው ደግሞ ኢየሱስ በማመን ነው። ኢየሱስን ማመን ማለት ደግሞ ስለ እኛ እንደሞተ እናም የሀጢያት ዋጋ እንደከፈለልን ደግሞ ጌታችን እንደሆነ ማመን ነው ።
ዮሐንስ 20 (John)
31፤ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።

#የዘላለም ህይወት ሰው እንዲያገኝ ይሔ የእግዚአብሔር ሀሳብ ነው
።እግዚአብሔር እኛ የዘላለም ህይወት እንድናገኝ ስለሚፈልግ ልጁን ኢየሱስ በመስቀል ላይ እንዲሞት እና እኛን ለማዳን አንድ ልጁን ሰጥቷል ። ሰው የዘላለም ህይወት እንዲያገኝ ነው ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ለዚህ ዓላማ ነው ።
ዮሐንስ 3 (John)
16፤ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።

#የዘላለም ህይወት ተቃራኒው የዘላለም ሞት ነው ። የዘላለም ሞት ለዘላለም መሞት ማለት ከእግዚአብሔር መለየት ነው ። አዳም ሀጢያት በመስራቱ ከእግዚአብሔር ተለየ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው ግንኙነት ተቋረጠ ስለዚህ የዘላለም ሞት ሞተ !! ስለዚህ የዘላለም ህይወት ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ማድረግ ነው ። የዘላለም ሞት ከእግዚአብሔር መለየት ከሆነ የዘላለም ህይወት ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር መሆን ነው ።

#የዘላለም ህይወት እግዚአብሔር ማወቅ ነው ። ሰው ስለ ብዙ ነገር ማወቅ ይፈልጋል ስለ ሰው ፣ ስለ ሀገር፣ ማንኛው እውቀት ማወቅ ይፈልጋል ። እግዚአብሔርን ማወቅ እንደ ማንኛው እውቀት አይደለም ! እግዚአብሔር ማወቅ ከእውቀት ያለፋል !!!ከእውቀት ሁሉ ትልቁ እውቀት እግዚአብሔር ማወቅ ነው ። እግዚአብሔር ማወቅ የአይምሮ ክምችት ወይም የአይምሮ ሀብት አይደለም !!!!እግዚአብሔር ማወቅ የዘላለም ህይወት ነው ። እግዚአብሔር እንዲታወቅ ይፈልጋል !!!ትልቅ አምላክ ነው ቢሆንም ራሱን አይደብቅም ፣ ራሱን አይሸሽግብንም እንድናውቀው ያረጋል ። እናም የዘላለም ህይወት ዋና ዓላማው እግዚአብሔር ማወቅ ነው ። እኛን ከሞት እንድንድን ከሲኦል እንድንተርፍ የፈለገው ተርፈን ቁጭ እንድንል ብቻ አይደለም ...እግዚአብሔር እንድናውቅ ነው ።
ዮሐንስ 17 (John)
3፤ እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።

** እግዚአብሔር እንዴት ሊታወቅ ይችላል ??? ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር እንዴት እናውቀዋለን በማለት ጥያቄ ያነሳሉ ። እግዚአብሔር የሚታወቀው በኢየሱስ ብቻ እና ብቻ ነው ።ኢየሱስ በምድር በነበረ ጊዜ ስለ እግዚአብሔር ነው ። ስለ እግዚአብሔር ማንም በሙላት ሊናገር የሚችል እግዚአብሔር በደንብ በሙላት ከኢየሱስ በቀር ማንም አያቀውም ። ወደ እግዚአብሔር ከኢየሱስ በቀር ማንም ሊሄድ አይችልም ። ለምን ኢየሱስ ብቻ ካልን ኢየሱስ ስላሴ ነው ። ኢየሱስ አምላክ ነው ።
ዮሐንስ 1 (John)
18፤ መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።

ዮሐንስ 14 (John)
6፤ ኢየሱስም፡— እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።

@ownkin
@cgfsd
129 viewsFilimon Nega, 04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ