Get Mystery Box with random crypto!

በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ አስተሳሰብ !! ጳውሎስ በክርስቶስ ስለነበረው አስተሳሰብ(ሃሳብ) ሲና | የክርስትና እውነቶች

በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ አስተሳሰብ !!

ጳውሎስ በክርስቶስ ስለነበረው አስተሳሰብ(ሃሳብ) ሲናገር እንዲህ ይላል።

“በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ያ አስተሳሰብ፣ በእናንተም ዘንድ ይሁን፤”
— ፊልጵስዩስ 2፥5 (አዲሱ መ.ት)

በእርግጥ ይህ የክርስቶስ ሃሳብ ምንድነው ? ብለን መጠየቅ አለብን ለምን ቢባል ሁኑ እየተባልን ያለው ነገር ስለሆነ ወይም በእናንተ ዘንድ ይኑር እየተባልን ያለው አስተሳሰብ ስለሆነ !!

ምንድነው ይህ ሃሳብ ካልን የትህትና ሃሳብ ነው ።ራስን ዝቅ የማድረግ ሃሳብ ነው። የክርስቶስ ሃሳብ ወይም አስተሳሰብ የሚለው ይህንኑ ራስን ዝቅ ማድረግን ነው።በዚህ ዘመን ይህንን መመከር እንዴት ከባድ መሰላቹህ ሰዎች ራሳቸው ከፍ ማድረግ በሚፈልጉበት በዚህ ዘመን ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ በትህትና ተመላለሱ ማለት ከባድ ነው።

ትህትና ማለት የሌለንን ነገር እንዳለን በመቁጠር ዝቅ ማለት ሳይሆን እንዳለን እያወቅን ዝቅ ማለትን የሚያመለክት ቃል ነው።ኢየሱስ የሆነው ይህንኑ ነው። እርሱ መለኮት ሆኖ ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር በእኩልነት በእኩልነት የሚኖር የእግዚአብሔር አብ አቻ መለኮት በባህሪው ፍፁም ከእርሱ የሚስተካከል ሆኖ ሳለ ለሰው ልጆች ሲል በስጋ የውርደትን ህይወትና ሞት ለመኖርና ለመሞት በማሪያም ማህፀን ተፀነሰ!!

ትሁታን ምንሆነው ከእውቀት ነፃ ስለሆንን አይደለም !ትሁታን የምንሆነው ገንዘብ ስለሌለን ዲግሪ ስለሌለን ማስተርስ ፒኤችዲ ስለሌለን በስጋ የሚያስመኩ ነገሮች ስለ ሌሉን አይደለም ። ኢየሱስ እግር ያጠበው ሁሉ እንደተሰጠው አውቆ ከሚል ቃል በኋላ እንደሆነ አስተውላቹሃል።

ዮሐንስ 13

³ ኢየሱስ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ አውቆ፥
⁴ ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤
⁵ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ።

ጳውሎስ ይህንን ነው ሚለን ይህ በክርስቶስ ውስጥ ያለው አስተሳሰብ በእናንተ ሊኖር ይገባል ።ኢየሱስ ትሁት እንደሆነ ትሁታን ሁኑ አንዳቹ አንዳችሁን አክብሩ በመከባበር እንጂ በመወቃቀር ህብረት አይፀናም ነው እያለ ያለው ለትህትና የመረጠው ምሳሌ የኢየሱስን ሰው መሆን ነው ።

በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ( in the form of God) በባሪያ (በሰው)መልክ ተገኘ ነው የሚለን

ፊልጵስዩስ 2 (አዲሱ መ.ት)
⁶ እርሱ በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን ሊለቀው እንደማይገባ አድርጎ አልቈጠረውም፤
⁷ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ፣ በሰውም አምሳል ተገኝቶ፣ ራሱን ባዶ አደረገ፤

Philippians 2 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ Who, being in the form of God, thought it not robbery to be #equal_with_God:
⁷ But made himself of no reputation, and took upon him the form of a servant, and was made
in the likeness of men:

ትሁት መሆን ሞኝነት አይደለም ።ትሁት መሆንን ልንፈፅመው የሚገባ ኢየሱስን በመምሰል የምንመላለሰው ህይወት ነው ።

ጌታ እግዚአብሔር ይህንን እንድንሆን ፀጋ ያብዛልን አሜን!!


ግሩም ድፈቅ