Get Mystery Box with random crypto!

አምላካችን እና መድሃኒታችን ተፃፈ በ Girum Difek በብሉይ ኪዳን መፅሃፍት ውስጥ እግዚአብ | የክርስትና እውነቶች

አምላካችን እና መድሃኒታችን
ተፃፈ በ Girum Difek

በብሉይ ኪዳን መፅሃፍት ውስጥ እግዚአብሔርን አምላካችን እና መድሃኒታች ብሎ መጥራት የተለመደ ነው። እንዲያድናቸው ሲፈልጉ መድሃኒት እንዲሆናቸው ሲሹ እግዚአብሔርን አምላካችን መድሃኒታችን እያሉ ይጠሩታል።ለምን ካልን እውነትም እርሱ አምላክና መድሃኒት ስለሆነ ነው።

“ቤተ መቅደስህ ቅዱስ ነው በጽድቅም ድንቅ ነው። በምድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስፋቸው የሆንህ፥ #አምላካችንና_መድኃኒታችን ሆይ፥ ስማን።”
— መዝሙር 65፥5
“#አምላካችንና_መድኃኒታችን ሆይ፥ እርዳን፤ ስለ ስምህ ክብር፥ አቤቱ፥ ታደገን፥ ስለ ስምህም ኃጢአታችንን አስተሰርይልን።”
— መዝሙር 79፥9

እስራኤላውያን ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ማንም አምላካችን እና መድሃኒታችን ብለው አይጠሩም ።ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ አምላክ የለምና። ይህንን በገማሊያል እግር ስር ቁጭ ብሎ የተማረው ጳውሎስም ወንጌላትን የፃፉልንም ጠንቅቀው ያውቁታል።

ስለዚህ የወንጌላት ፀሃፊዎች እና ብዙ መልዕክታትን የፃፈልን ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ እና ሌሎቹም ሐዋሪያት ኢየሱስን አምላክና መድሃኒት ብለው ሲጠሩት እርሱ እግዚአብሔር ነው ከማለት ወጪ ሌላ ምን አስበው ሊሆን ይችላል?

“ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም #የታላቁን_የአምላካችንንና #የመድኃኒታችንን_የኢየሱስ_ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤”
— ቲቶ 2፥12-13

ጴጥሮስ የሁለተኛ ጴጥሮስ መልዕክቱን በሰላምታ ሲጀምር እንዲህ ይላል።

“የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ የሆነ ስምዖን ጴጥሮስ፥ #በአምላካችንና_በመድኃኒታችን_በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ፤”
— 2ኛ ጴጥሮስ 1፥1

ይሁዳም በመልዕክቱ እንዲህ ይለናል።

“ብቻውን ለሆነ #አምላክ_መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።”
— ይሁዳ 1፥25

ኢየሱስ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ህይወት መድሃኒትም ነው።

ክብር ምስጋና ለእርሱ ይሁን አሜን!!