Get Mystery Box with random crypto!

መጀመሪያ ግቢ ስንደርስ ማን ጋር ነው ምንገናኘው ? ግቢ በር ላይ ከመኪና ኦር ከታክሲ እን | Campus Edu life

መጀመሪያ ግቢ ስንደርስ ማን ጋር ነው ምንገናኘው ?



ግቢ በር ላይ ከመኪና ኦር ከታክሲ እንደወረዳቹህ በመጀመሪያ የምታገኙት እንኳን ደህና መጣቹህ የሚል ፈገግ ያለ ፊት ነው ። ( like አስጌ ዴንዴሾ )

እዚህ ጋር መርሳት የሌለባቹህን ላገጠጠላቹህ በሙሉ ሻንጣ እንዳትሰጡ በተለይ መናሀሪያ የምትወርዱ ከሆነ በጣም ተጠንቀቁ አንገታቸው ላይ or ደረታቸው ላይ ባጅ ያጠለቁ እሱንም የዩንቨርሲቲው ማህተም ያለበት መሆኑን ቼክ አርጉ አንዳንድ ከተሞች ላይ በጣም የተደራጁና ረቀቅ ያሉ ሌቦች ስለሚኖሩ be take care.

የትኛውም ግቢ አዲስ ተማሪዎች በሚገቡበት ቀን በር ላይ የተለየ ዝግጅት በማድረግ ጥብቅ ፍተሻ ይደረጋል ።

ማንኛውም ተማሪ የያዘውን ሻንጣ ከፍቶ ሳያስፈትሽ እግሩ ወደ ግቢ አይገባም ።
ከፍተሻው በተጨማሪ ግን ሁሉም ተማሪ የዶርምና ብሎክ ቁጥር ማወቅ አለበት እሱም ከግቢ ውጭ ወይም ግቢ ውስጥ ይለጠፋል አንዳንዶች ግቢዎች ደግሞ ዌብሳይት ላይ አስቀድመው ይለቃሉ like AAU እንዳደረገዉ።
የብሎክና ዶርም ቁጥራችሁን ካወቃቹህ ጓዛችሁንም ካስፈተሻቹህ በኋላ ቀጥታ የምትሄዱት ወደ ዶርም ነው ።(ነባር ተማሪዎች ብሎክ ድረስ ይሸኟቹሃል)
ብሎካቹህ ጋር ስትደርሱ ground ላይ የብሎክ ሃላፊው(ፕሮክተር) ቢሮ በመስኮት በኩል ዶርም ቁጥራችሁን፣ ስም፣ phone number እና ፎቶ በመስጠት ፈርማቹህ የዶርም ቁልፍ ትቀበላላቹህ ።( ቁልፍ የሚሰጠው ቀድሞ ለመጣ አንድ የዶርም አባል ብቻ ነው ከተቀደማቹህ ቁልፍ የተሰጠውን ዶርሜት ስልክ ቁጥር ተቀብላቹህ መደወል ነው)


ዶርም ስትገቡ የመጀመሪያ ሰው ከሆናቹህ ያሻችሁን አልጋና ሎከር መርጣቹህ የመያዝ ሙሉ መብት አላቹህ ። ደስ ካላችሁም ትራስ ምናምን መቀያየር ችቡድ ሰባራ ከሆነ እሱንም መቀየር... ብቻ በዶርሙ ላይ የተመቻችሁን የግል ንብረት ማሽከርከር ትችላላቹህ coz ማንም በቦታው ላይ የለምና ።
ከተቀደማቹህ ግን ከቀደማቹህ ሰው ጋር ሳትጋፉ ያገኛችሁትን ....
አደራ ግን እንዳትጨቃጨቁ

ሌላው ዶርም ስትገቡ አንሶላና ትራስ ጨርቅ ምናምን ሳትጠቀሙ ጋደም ማለት ቢያምራቹህ እንኳ እንዳተኙ coz ፎከታም ትሆኑብኛላቹህ(biology ላይ የተማራችሁትን አትርሱ fungus+virus)

የዶርም ጣጣችሁን ከጨረሳችሁ ቀጥታ የምትሄዱት ወደ register ይሆናል (በስራ ሰዓት ብቻ)
አመሻሽ ላይ ግቢ ከደረሳቹህ ለምዝገባ ስለማትደርሱ የዶርማችሁን ጣጣ ለመጨረስ ሞክሩ ለምዝገባው አታስቡ በነገታው መመዝገብ ትችላላቹህ ።

ምዝገባ ቦታ ላይ ያለው process

መጀመሪያ ክላሰር ወረቀት ትገዙና የሚሰጣችሁን ፎርም ትሞላላቹህ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ኦሪጂናሉንና ኮፒውን ትጠየቁና ኦሪጂናሉ ይመለስላቹሃል ። ፎቶም ትጠየቃላቹህ
በሌላ መስኮት ደግሞ ID ምናምን ታወጣላቹ ከዛ ትንሽ ትንቀዋለሉና ትጨርሳላቹህ

Above ሁለት ሺህ ተማሪ ምናምን በአንድ መስኮት ስለሚስተናገድ በጣም መጨናነቅ ይኖራል ቻል ማድረግ ነው ።

ምዝገባ ከጨረሳቹህ መታወቂያ ከተቀበላቹ ዶርም ሂዳቹ ደስ ካላቹህ ተገልብጣቹህ ለጥ ማለት ትችላላቹህ ።



አንዳንድ ግቢዎች ላይ መጨናነቁ በከፊል ሊቀንስ ይችላል ።

አንዳንዶች ጋር ደግሞ ባስ ይላል



ተማሪዎችም በተመሳሳይ መልኩ ይሆናል register ላይ ግን እንደፍሬሽ አይንከራተቱም ID ማሳደስ ብቻ ሌላው ነገር በሙሉ ተመሳሳይ ነው ።

ለአስተያየት ፣ ለጥቆማ አልያም
ለጥያቄ
@EtTemari_bot


╔═════════════╗
@HigherEduEt 
@HigherEduEt
╚═════════════╝ #SHARE