Get Mystery Box with random crypto!

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ዐረፉ ********************* የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተ | Campus Edu life

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ዐረፉ
*********************

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ማረፋቸውን የቤተክርስትያኗ መገናኛ ብዙኃን ጠቅሶ የዘገበው ኢዜአ ነው።

ቅዱስነታቸው ሰሞኑን ባደረባቸው ህመም የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው መቆየቱ ይታወሳል።

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በ1980 ዓ.ም ነሐሴ 29 ቀን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ፓትርያርክ ተብለው የተሾሙ ሲሆን ላለፉት 34 አመታት በፓትርያርክነት አገልግለዋል።

ብጹዕ ወቅ አቡነ መርቆሬዎስ የቤተክርስቲያኗ ትምህርት የሆኑትን አቋቋም፣ ድጓና ዝማሬ መዋስዕት በላቀ ሁኔታ የተማሩ መሆናቸውን ከሕይወት ታሪካቸው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።