Get Mystery Box with random crypto!

ታህሳስ 23/2015 የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ማዕከል | Bule Hora University

ታህሳስ 23/2015
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ማዕከል (ኢሰመጉ) ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድም ተፈራርመ።
የስምምነቱ አላማ የሰብአዊ መብት እና የፆታ እኩልነት ድርጅት በማንኛውም የመንግስት ተቋም ውስጥ በመገኘት ሰብአዊ መብቶች እንድረጋገጡ ለማስቻል ነው፡፡
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሰብአዊ መብትና የሥርዓተ ጾታ እኩልነት ተሟጋች ክለብ ለማቋቋምና ለማስተዳደር ከዩኒቨርሲቲው የህግ ትምህርት ቤት ጋር በቅንጅት ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ነው- የጋራ ስምምነቱ የተደረገው፡፡
ማዕከሉ ከትምህርት ቤቱ ጋር በመተባበር ከተለያዩ የትምህርት ዘርፎች የተወጣጡ ተማሪዎችን በመምረጥ ለ20 ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል (ኢሰመጉ) አስተባባሪ አቶ በፍቃዱ ድሪባ እንዳሉት ማዕከሉ ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጋር የሁለት አመት ውል መፈራረም መቻሉ ለሰብአዊ መብትና ለጾታ እኩልነት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው።
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ዲን የሆኑት መ/ርት ዱርሲቱ በሪሶ በበኩላቸው የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ጋር በጋራ ለመስራት ዩኒቨርሲቲው ቁርጠኛ እንደሆነ በመግለጽ የተቋቋመውን የሰብአዊ መብትና የፆታ እኩልነት ክለብን አጥብቀው እንደሚያበረታቱ ተናግረዋል።
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
ለላቀ ለውጥ እንተጋለን!