Get Mystery Box with random crypto!

ታህሳስ 24/2015 'በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና' በሚል ፅንሰ ሀሳብ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የም | Bule Hora University

ታህሳስ 24/2015
"በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና" በሚል ፅንሰ ሀሳብ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በፕሮግራሙ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታምሩ አኖሌ መድረኩ የጋራ ውይይት በማድረግ ለሀገር ግንባታ ምሁራን ያላቸው ሚና የሚዳሰስበት በመሆኑ ጥልቅ የሆነ ውይይት ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ በበኩላቸው ያለን የጋራ ሀገር በመሆኑ የጋራ ውይይት በማድረግ ሀገራችንን በጋራ ለመገንባት የታለመ መድረክ እንደሆነ አስረድተዋል።
'በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና' የሚል የምክክር ሰነድ ያቀረቡት የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታና የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ስዩም መስፍን ሲሆኑ በሀገራችን ኢትዮጵያ በሀገር ግንባታ ላይ የምሁራን ሚና ታሪካዊ ዳራ እና የምሁራን አሁናዊ ሚና ምን እንደሚመስል በሰነዱ ተብራርቷል።
ለሀገር ግንባታ እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮች፣ያላቸው ተፅእኖ እና ከምሁራን የሚጠበቁ ቁልፍ ተግባራት በምክክር ሰነዱ ተዳሰዋል።
በምክክር መድረኩ የሀገራችን ኢትዮጵያ እና የሌሎች አለም ሀገራት በሀገር ግንባታ ረገድ ያላቸው ተሞክሮ እና የምሁራኖቻቸው ሚና በጥልቅ ተብራርቷል።
መድረኩ በዩኒቨርሲቲው ለተከታታይ አራት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን በዛሬው እለት ከዩኒቨርሲቲው የካውንስል አባላት ጋር ነው - የምክክር መድረኩ የተደረገው።
በቀረበው የምክክር ሰነድ ላይ የካውንስል አባላቱ ጥልቅ ውይይት አድርገዋል። የምክክር መድረኩ በቀጣይ ቀናቶች ከዩኒቨርስቲው መምህራን ጋርም በተመሳሳይ መነሻ ሀሳብ የሚቀጥል ይሆናል።
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
ለላቀ ለውጥ እንተጋለን!