Get Mystery Box with random crypto!

ታህሳስ 20/2015 በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን 1ኛ ሴሚስተር የመጀመሪ | Bule Hora University

ታህሳስ 20/2015
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን 1ኛ ሴሚስተር የመጀመሪያ የትምህርት ቀን የመጀመሪያ ክፍል Day One Class One (DOCO) በትክክል ተግባራዊ ያደረጉ ኮሌጆች የዕዉቅና መረሃ ግብር ተዘጋጀ።

እንደሚታወቀው በዚህ በያዝነዉ የትምህርት ዘመን ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 5 እና 6 ቀን 2015 ዓ.ም ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎቹን በመመዝገብ ህዳር 07 ቀን 2015 ዓ.ም የመማር ማስተማሩን ሰራ በይፋ መጀመሩ ይታወቃል።
በዚሁ መሰረት ለ2015ዓ.ም የትምህርት ዘመን 1ኛ ሴሚስተር የመጀመሪያ የትምህርት ቀን የመጀመሪያ ክፍል Day One Class One (DOCO) በትክክል ተግባራዊ ያደረጉ ኮሌጆች ዕዉቅና ተበርክቶላቸዋል።
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይ ረዳት ፕሮፌሰር ገመዳ ኦዶ እንደተናገሩት ለኮሌጆች ለስራቸው በማበረታቻ ዕውቅና በሰጡበት ወቅት የዛሬው እውቅና ዓላማ በዩኒቨርሲቲያችን የሚወጡትን መመሪያዎችን እንዲተገብሩ ለማድረግ የታሰበ ነዉ በማለት ይህ የማበረታቻና የዕዉቅና ፕሮግራም የተዘጋጀዉ ብለዋል ።
ይህ የማበረታቻ የምስክር ወረቀት ለወደፊቱ መልካም ስንቅ ይሆነናል እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲዉ የሚሰጡ የተለያዩ የስራ መመሪያዎችን ተግባራዊ እንድናደርግ ተነሳሽነትን ይፈጥርልናል ሲሉ ማበረታቻውን የተቀበሉት የኮሌጅ ዲኖች ተናግረዋል።
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
ለላቀ ለዉጥ እንተጋለን!