Get Mystery Box with random crypto!

IPTV    IPTV  (Internet Protocol Television) ይህ ሲስተም ለመጠቀም መጀመ | G-Share Sports

IPTV   
IPTV  (Internet Protocol Television) ይህ ሲስተም ለመጠቀም መጀመርያ ሪሲቨራችን ይህ ሲስተም ሊኖረው ይገባል:: በሃገራችን ይህ ሲስተም ያላቸው ሪሲቨሮች LEG,TIGER,STARSAT እና ሌሎችም ሪሲቨሮች ናቸው:: እንደዚሁም በተጨማሪ አንድሮይድ ስልኮች ፣ አንድሮይድ ቦክስ ወይም ቲቪ ቦክስ እና ስማርት የሆኑ ቲቪዎች ላይ በሚጫኑ አፕሊኬሽኖች መሰረት መጠቀም ይቻላል

ይህ IPTV ከCard sharing ወይም IKS የሚለየው ነገር መጀመርያ እንደካርድ ሼሪንግ: ሼር የሚደረግ ኪ ዳታ አይደለም:: ሪሲቨራችንን በWIFI ወይም በ4G ኢንተርኔት ኮኔክትድ ከሆነ በሁዋላ: ይህን ሰርቪስ በሚሰጡ ካምፓኒዎች አማካኝነት የተለያዩ የነፃና በክፍያ የሚታዩ ቻናሎችን በአነስተኛ ክፍያ የምናይበት ነው::

የእዚህ ሲስተም ትልቁ ጥቅም የምንፈልገው ቻናል እኛ ሀገር ይደርሳል አይደርስም የሚባል ነገር የለውም:: የትኛው ሃገር የሚተላለፍ ቻናል በIPTVማየት አንችላለን:: ምክንያቱም ካምፓኒዎቹ በምርጫችን ስለሚሰጡን:: የቲቪ ቻናሎችን ብቻ ሳይሆን ቪድዮችንም እንደምርጫችን ማየት እንችላለን:: ይህን ጥቅም ከCard sharing አናገኘውም:: ምክንያቱ በCard sharing ቻናሎቹን የምናገኘው ጣራ ላይ በሰቀልነው የዲሽ ሰሃን ሲሆን: በIPTV ግን ቻናሎቹን የምናገኘው ይህንን አገልግሎት ከሚሰጡ ካምፓኒዎች በአነስተኛ ክፍያ ከምንገዛው ፓኬጅ ነው::

የእዚህ IPTVሲስተም ጉዳቱ: ቻናሎቹ ወደሪሲቨራችን የሚመጡት ጣራ ላይ በሰቀልነው ዲሽ አማካኝነት ሳይሆን በኢንተርኔት ስለሆነ: ዋጋው ትንሽ ሲወደድ: በእዛ ላይ በጣም ሃይ ስፒድ የሆነ ኢንተርኔት ኮኔክሽን ይፈልጋል:: ይህን ሲስተም ለመጠቀም ቢያንስ የኢንተርኔት ፍጥነታችን 3mb/s በላይ ሊሆን ይገባል አንድ አንድ ቦታ ደሞ በትንሽ ኢንተርኔት በጥራት እየሰራልን ነው ያሉኝም አሉ Iptv ተጠቃሚዎች በጥራት ያለመቆራረጥ የሚመክረው ምክር 4G UNLIMITED ኢንተርኔት ወይም wifi ከ2mb/s በላይ በሆነ ቢጠቀሙ በጥራት ሊያዩ ይችላሉ

ስለዚህ ለእኛ ከIPTV ይልቅ Card sharing ይመረጣል:: ምክንያቱም በCard sharing በየተወሰነ ሰከንዶች የምንቀበለው ኪ ዳታ የሆነ በጣም አነስተኛ የሆነ ባይትስ ስለሆነ:: ነገር ግን ኢንተርኔታችን ፍጥነትና አስተማማኝነት ሲሻሻል እና ዋጋው አሁንም ካለበት በጣም ሲረክስ ደግሞ ያኔ ከCard sharing ይልቅ IPTV ይመረጣል::

IPTV ለመጠቀም ምርጥ ሪሲቨር #LEG N24+ PLUS ፣ N24 Pro Iron ፣ N 24 Pro የተሻሉ ናቸው ምክንያቱም በውስጡ #E_VISION IPTV ስለያዘ በ E_VISION IPTV ውስጥ ተፈላጊዎቹ
BEIN SPORT
Sky Sport
DAZN sport
Laliga Bar
Zeggo sport
eurosport
sport የፖርቹጋሉ
RMC Sport ስለያዙ የተሻለ ነው በዚህ ውስጥም የሌሎች ሀገር የኳስ ቻናሎች እና ከ 5000 በላይ የተለያዩ ሀገራት ቻናሎችን ይዟል


ማንኛውን አይነት የዲሽ እቃ ሲፈልጉ እንደቤተሰብ ተመካክረን ጥሩ እቃ እንዲገዙ እናደርጋለን።

@Umer4K
0911590613