Get Mystery Box with random crypto!

ለአራተኛው የወያኔ ወረራ መዘጋጀት ግድ ሊሆን ነው። ========================= ሲተረ | ብሩህ ወቅታዊ ዜና

ለአራተኛው የወያኔ ወረራ መዘጋጀት ግድ ሊሆን ነው።
=========================
ሲተረጎም ወያኔ ለወረራ እየተዘጋጀች ነው። የመጨረሻው ድርድር ክሽፈት ለመጨረሻው ጦርነት እንድንዘጋጅ ጥሪ ይጋብዛል። የአሁኑ ጦርነት ዋዜማ በአሜሪካኖቹ ኡኡታና ስሞታ የታጀበ መሆኑ በሰሜን ዕዙ ጥቃት ዋዜማ አንድ ጥይት ሳይተኮስ የነበረውን የምዕራባውያን ሚዲያዎችን ጫጫታ ያስታውሳል። አሁንም ጫጫታው ተደግሟል።

መቀሌ ደጅ ላይ መከላከያ እንደደረሰ ወያኔ "ያለምንም ቅ/ሁኔታ እስማማለሁ፤" ስትል መጠርጠር ይበጅ ነበር። የድርድሩን ስምምነት ወያኔ በሳምንቱ "የምፈታው ትጥቅ የለኝም፣ የወከለኝ የለም፣ ...." አለችና አፈረሰችው። ትላንት ጌታቸው ረዳ አዲስ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል። "የኤርትራ እና የአማራ ሰራዊት ሳይወጣ ትጥቅ አንፈታም።" አለ። ሌላ ቅዠት።

የዋሁ መንግስታችን ከዋናኛዉ ጸረሰላም ጋር ተጨባብጦ "በዚህም በዚያም ያሉት ፀረ-ሰላም" ያላቸው ላይ ዛቻውን ሲዘነዝር እነታደሠ ወረደ የልባቸውን አድርሰው ወደ መቀሌ ጉዞ እያደረጉ ነበር። በማግስቱ ገብተናል ብለው ጉራቸውን ነሰነሱና ደጋፊዎቻቸውን ጮቤ አስረገጡ። ትግራይ ውስጥ ያለው ሕዝብ እፎይታ የሚያመሽ አይመስልም።

ለማንኛውም አሁንም ወያኔ ለዕልቂት እየተዘጋጀች ነው። የትግራይ ገበሬዎች እንቁላልና ስንቅ ለጦርነቱ እያዋጡ ነው።
በመንግሥት በኩል ያለውን ዝግጅት አናውቅም። እንደዜጎች ግን ለመጨረሻው ፍልሚያ አለመዘጋጀት የሚቻል አይደለም። ወያኔ አሸንፎ አይደለም እስካልጠፋ ድረስ ሰላም አይኖርም።

@BRuhDailyNews