Get Mystery Box with random crypto!

አላማጣ የአላማጣ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ስጋቶች ምክንያት የእንቅስቃሴ ገደቦችን ጣለ! የከተማ | ብሩህ ወቅታዊ ዜና

አላማጣ
የአላማጣ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ስጋቶች ምክንያት የእንቅስቃሴ ገደቦችን ጣለ!

የከተማው  ማህበረሰብ  በተለያዩ ሁኔታዎች ስጋት ውስጥ እንዳይገባና  የከተማችንን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል የሚከተሉትን  ውሳኔዎች አሳልፍል ፡፡

1.  ማንኛውም እግረኛ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው የተገኝ ግለሰብ 1000 (አንድ ሺ ብር) ይቀጣል።

2.  ለጸጥታ ስራ ስምሪት ከተሰጣቸው ተሸከርካሪዎች ውጭ ማንኛውም ተሸከርካሪ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ  ነው።

3.  ከጸጥታ መዋቅሩ ውጭ በየትኛውም ሰዓትና ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና የማይመለከተውን የልዩ ሀይልና መከላከያ የደንብ ልብስ ለብሶ  መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

4.  የማህበረሰቡን የኑሮ ውድነት የሚያባብሱ ምክኒያታዊ ያልሆነና ያለአግባብ  የዋጋ ጭማሪ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው
5 ጫት ወደ ከተማው ማስገባት እና መቃም በጥብቅ   የተከለከለ ነው ይህን ሲያደርግ የተገኘ ርምጃ ይወሰዳል።

5.  ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ማለትም ሱቆች፣ ሆቴል፣ መጠጥ ቤቶች እና ሌሎች ከ1:00 ስዓት በኃላ ከፍቶ አገልግሎት እየሰጠ የተገኝ 10,000( አስር ሺ ብር ) ተቀጥቶ ወዳያውኑ እንዲዘጋ ይደረጋል።

6.  በከተማችን የሚገኙ የመንግስትና የግል ባንኮች ስራ እስከሚጀምሩ እስከ 50,000( አምሳ ሺ ብር )ይዞ መንቀሳቀስ የተፈቀደ ሲሆን ከዚህ የብር መጠን በላይ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው ።

7.  ማንኛውም ማህበራዊ ሚዲያ  ተጠቃሚ ግለሰብ ሆነ ድርጅት የትኛውንም  ሚዲያ ተጠቅሞ የሃሰት መረጃዎችን ማሰራጨት፣ በተለይ የጥላቻ እና የተዛባ መረጃ  መስጠት በጥብቅ የተከለከለ ነው።

8.  ማንኛውም የቤት አከራይ ወይም አልጋ ቤቶች ተከራዮቻቸውንና ተጠቃሚዎቻቸውን የመለየትና ማንነታቸውን የሚለይ ህጋዊ መታወቂያ ስለመኖራቸው የማረጋገጥ ግደታ አለባቸው ፡፡ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ከተፈጠሩ ለፀጥታ መዋቅሩ ጥቆማ የመስጠት ሃላፊነት አለባቸው።

9.  ማንኛውም የከተማ ኗሪ ማህበረሰብ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር የመቀናጀትና የመተባበር  ግዴታ አለበት ።

10. ከፀጥታ መዋቅር ውጭ ማንኛውም አካል ቤት መፍተሽ, አይችልም ይህን ሲያደርግ  የተገኝ  በፀጥታ መዋቅር እርምጃ  ይወስዳል።

11. ታርጋ የሌላቸው ተሸከርካሪ  ፤ መንጃ ፍቃድ የሌለው አሽከርካሪ ማሽከርከር የተከለከለ ነው ይህን ተላልፎ የተገኘ 5000 (አምስት ሺ ብር ) ይቀጣል።

ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች በማያከበር ማንኛውም አካል የፀጥታ መዋቅራችን አስፈላጊውን  እርምጃ የሚወስድ መሆኑን  እናሳዉቃለን።

የአለማጣ ከተማ አስተዳደር  ፀጥታ ምክር ቤት
ህዳር 9/2015 ዓ/ም
 @BruhDailyNews
@BruhDailyNews