Get Mystery Box with random crypto!

Continued........ H2O(0°C) ወደ Pure H2O(2O°C) የተቀየረው ደግሞ Tempe | መርጌታ ይሃንስ የባህል መድሀኒት ቀማሚ

Continued........

H2O(0°C) ወደ Pure H2O(2O°C) የተቀየረው ደግሞ Temperature Difference አለ ፡ በQ = mc∆T አድርገን እንሰራለን ማለት ነው

የመጀመርያውን ለመስራት Q = mL እንጠቀማለን ፡ l ግን Latent heat of Fussion መሆን አለበት ማለት ነው ። ምክንያቱም ከICE ወደ Water ስለሆነ ማለት ነው

ስለዚህ እሄንን ስንሰራ ፡
Q = mLf
Q = 2 * 3.33 *10⁵ J ይሆናል ማለት ነው

2ኛው ደግሞ Temperature Change ሲኖር...
Q = mC∆T
Q = 2*4186*(20°C -0°C)
Q = 167440J ይመጣል ማለት ነው እሄንን በ Scientific notation ስንጽፈው 1.67*10⁵J ይሆናል ማለት ነው
ስለዚህ ስናጠቃልለው ፡ Total Energyውን ለማግኘት...
የመጀመርያውን Q1 እንበለው ።
የሁለተኛውን ደግሞ Q2 እንበለው ።
QT = Q1 + Q2 ስናደርገው
QT = (6.66*10⁵)*(1.67*10⁵)
QT = 8.33*10⁵ Joules of Energy ያስፈልጋል ማለት ነው ። 2Kg Ice ከ0°C ወደ 20°C ለመቀየር የሚያስፈልገን ማለት ነው

ጥያቄ ቁጥር 4 .....
4. A 0.050Kg ingot of metal is heated to 200°C and then dropped into a caliometer containing 0.4kg of water initially at 20°C . The final Equilibrium temperature of a Mixed system is 22.4°C . The specific Heat of the metal


መልስ......
እሄንን ጥያቄ ሙሉ ለሙሉ ምን ማለት እንደፈለገ ወደ አማርኛ ቀይሬ ላስረዳችሁ ።

የሆነ ውሃ በብርጭቆ ውስጥ አለን እንበል ፣ እሄ ውሃ 20°C ያለ ውሃ ነው እና ሌላ ነገር ደግሞ የጋለ ማንካ አለን ፣ እሄ ማንካ በ200°C ነው የጋለው ፣ እሄንን ማንካ በብርጭቆ ውሃ ውስጥ ስንጨምረው የውሃው Temperature ወደ 22.4°C ከፍ አለ ። ጥያቄያችን የማንካው Specific Heat Capacity ስንት ነው የሚል ነው

እስቲ ቀለል አድርገን እንስራው ።
እሄንን ጥያቄ በ Energy Conservation ጋር አገናኝተን ነው የምንሰራው ፡ እሄ ማለት ደግሞ ውሃው Gain ካደረገው Energy ውሃው Lost ጋደረገው Energy ጋር እኩል አድርገን ነው የምንሰራው ። ምክንያቱም ማንካው Heat Energy Lost ባደረገው ልክ ውሃው Heat Energy gain አድርጓል ማለት ነው

እሄ ማለት ደግሞ ፡
Q(gain) = Q(lost)
Q(ውሃ) = - Q(ማንካ)
mC∆T = -mC∆T

ስለዚህ ፡ የተጠየቅነው Specific Heat Capacity of Metal ወይም ደግሞ ማንካ ያልነውን ማለት ነው ።

C(metal) = - (mC∆T/m∆T)

ስለዚህ ቀጥታ መተካካት እንችላለን ማለት ነው ።
Mass of Metal = 0.05kg
Mass of Water= 0.4 kg

Temperature of Final የሲስተሙ ማለት ነው ፡ 22.4°C ነው ።
Temperature of Water : 20°C
Temperature of Metal = 200°C ነው ።

Specific Heat of Water 4186J/Kg°C ነው ።

በቃ አነኝህን ተክተን ነው የምንሰራው ማለት ነው ።

C(metal) = - (mC∆T/m∆T)

mC∆T ፡ እዚህኛው ላይ የምንጠቀመው Temperature የ Waterን ነው ስለዚህ 22.4°C - 20°C = 2.6°C ይሆናል ማለት ነው

m∆T ፡ እዚህ ላይ የምንጠቀመው Temperature ደግሞ የMetalኡን ነው ። ስለዚህ 22.4°C -200°C = -177.6°C ይሆናል ማለት ነው ።

በዚህ መሰረት ፡
C(metal) = - (mC∆T/m∆T)
C(metal) = - (0.4*4186*2.6)/(0.050*-177.6)
እሄንን Calculate ስናደርገው
SPECIFIC HEAT CAPACITY OF METAL = 452.54J/Kg°C ይመጣል ማለት ነው ።

ጥያቄ ቁጥር 5
5) Calculate the Change in Internal Energy of the system if 600J of heat energy was added to it and if the system performs 300J of work.

መልስ.......

በቅድሚያ ጥያቄው ምን እንደሚል ተረዱ ።
እንዴት ነው የምንሰራው ፡
∆U = ∆Q - ∆W አድርገን ነው እንዴት ለሚለው ትንሽ ማብራሪያ ላቅርብላችሁ ።
በነገራችን ላይ Grade 12 ላይ አሁን ወደፊት ሰፋ አድርገን እናየዋለን ነገር ግን ከሚገርመኝ ነገር ውስጥ እሄ ነገር Grade 12 Chemistry Unit 3 ላይ Thermodynamics ስትማሩ ይለያያል ፣ የPhysics እና የ Chemistry ሃሳብ ፡

እስቲ ጠቅለል አድርጌ ለማስረዳት ልሞክር
Q Added : Posotive ነው
Q removed ፡ Negative ነው
Work by the system ፡ በPhysics Posotive ነው ። ነገር ግን በ Chemistry Negative ነው ። ምክንያቱን በ Chemistry ክፍለ ጊዜ ጠብቁን ።
Work on the system ፡ በ Physics Negative በ Chemistry Posotive ነው።

ስለዚህ፡ ∆U = ∆Q -∆W ነበር። Original Formulaው ነገር ግን ፡ ነገር ግን Work Done on the system Posotive ስለሆነ ∆U = ∆Q -(-∆W) በማድረግ ∆U = ∆Q + ∆W አድርገው አስቀመጡት ማለት ነው ። አንዳንድ አስተማሪዎች አሁን ቀጥታ እሄንን ∆U = ∆Q + ∆W ልክ እንደ Original Formula ሊያስቀምጡላችህ ይችላሉ ግን ልክ አይደለም ማለት ነው ።

ስለዚህ Physics እና Chemistry ላይ ጥንቃቄ አድርጉ አሁን እየሰራን ያለነው Physics ስለሆነ በPhysics Standard እንሄዳለን ማለት ነው ።

እስቲ ጥያቄዉን እናስተውለው ።
Heat added ስላለን ፡ Q = 600J እናደርጋለን ማለት ነው ።
Work by the system ስለተባልን ደግሞ W = +300 እናደርጋለን ማለት ነው ።

∆U = ∆Q -∆W
∆U = 600 - (+300)
∆U = 300J ይመጣል ማለት ነው

ይቀጥላል.....

ለተጨማሪ የ12ኛ ክፍል ትምህርቶች ይመዝገቡ

ለመመዝገብ ይህን ይጠቀሙ
          
@EntranceHubbot
    ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
           
@EntranceHubEthiopia
ለተጨማሪ መረጃ እኛን ያግኙን
             
@Entrancehub_Admin
   ይደውሉልን
         
+251917318110
        
+251948398047
ENTRANCE HUB ETHIOPIA
#path to Success