Get Mystery Box with random crypto!

የሰላም ጥሪን ሁሉም እንዲቀበል ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጥሪ አቀረቡ የኢትዮጵያ እናቶች እ | ሰበር ዜና

የሰላም ጥሪን ሁሉም እንዲቀበል ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጥሪ አቀረቡ

የኢትዮጵያ እናቶች እና ሰላም ወዳድ ዜጎች እያቀረቡት ያለውን የሰላም ጥሪ ሁሉም እንዲቀበልና ተግባራዊ ምላሽ እንዲሰጥ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ፕሬዚዳት ሳህለወርቅ ዘውዴ ዛሬ በተካሄደው የኢትዮጵያ እናቶች የሰላም ጥሪ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሀገራችን ኢትዮጵያ ፍቅርና ሰላም የሰፈነባት እንዲሁም ለዜጎች የምትመች ሀገር እንድትሆን በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ የዳያስፖራ ማህበረሰብን ጨምሮ ኢትዮጵያውን እናቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ተወካዮች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪና ታዋቂ ግለሰቦች እያደረጉት ያለውን ጥረት አድንቀዋል፡፡

እስካሁን ለተደረገው ጥረት አመስግነው÷ ጥረቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።

@BreakingNewsEthiopiaa