Get Mystery Box with random crypto!

የትግራይ ኃይሎች ከአማራ ክልል እንዲወጡ የብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጠየቁ! የትግራይ | ሰበር ዜና

የትግራይ ኃይሎች ከአማራ ክልል እንዲወጡ የብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጠየቁ!

የትግራይ ኃይሎች በአማራ ክልል የጀመሩትን ውጊያ አቁመው ወደ ትግራይ ክልል እንዲመለሱ የብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ጠየቁ። ሚኒስትሯ በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ኃይሎች ክልሉን ለቀቅው መውጣት አለባቸው ብለዋል።

ቪኪ ፎርድ ይህን ያሉት የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና የኢትዮጵያ መንግስት ኃይሎች ዳግም ወደ ግጭት መመለሳቸውን በተመለከተ ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 26፤ 2014 ባወጡት መግለጫ ነው። ሁለቱ ኃይሎች እንደገና ወደ ግጭት መግባታቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ “መከራ የሚያመጣ” ነው ያሉት የብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር፤ በክስተቱ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸውን የማጣት አደጋ እንደተጋረጠባቸው ገልጸዋል።

በሁለቱ ኃይሎች ውጊያ ምክንያት በቀጥታ ከሚደርሰው የሰዎች ሞት ባሻገር፤ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ የሚገኘው ሰብዓዊ ሁኔታ በግጭቱ ምክንያት ይበልጥ ስለሚባባስ የሰዎችን ሞት ሊያስከትል እንደሚችል ፎርድ በመግለጫቸው ጠቁመዋል። የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት በትግራይ፣ በአማራ እና አፋር የሚገኙ 13 ሚሊዮን ሰዎችን የሰብዓዊ እርዳታ ፈላጊ እንዳደረጋቸው ያስታወሱት ሚኒስትሯ፤ የአሁኑ ውጊያ እና በህወሓት የተያዘው የዓለም የምግብ ድርጅት ነዳጅ፤ የሰብዓዊ ድርጅቶችን ስራ “ይበልጥ አስቸጋሪ ያደርገዋል” ብለዋል።

የብሪታንያ መንግስት፤ ህወሓት የያዘውን ነዳጅ ለእርዳታ ማከፋፈል እና ለሌሎች አንገብጋቢ አገልግሎቶች እንዲውል እንዲያደርግ ጥሪ ያቀርባል ሲሉም የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትሯ አክለዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ፦ https://ethiopiainsider.com/2022/7931/

@BreakingNewsEthiopiaa