Get Mystery Box with random crypto!

አቢሲንያ ባንክ ታክሲ አሽከርካሪዎችን እንደ አምባሳደር! አቢሲንያ ባንክ እና ሊትል ታክሲ ለሜት | Bank of Abyssinia

አቢሲንያ ባንክ ታክሲ አሽከርካሪዎችን እንደ አምባሳደር!

አቢሲንያ ባንክ እና ሊትል ታክሲ ለሜትር ታክሲ አሽከርካሪዎች በአይነቱ ለየት ያለ የተጨማሪ ገቢ እና ብድር የማግኛ ዕድል በአጋርነት ማቅረባችውን ዛሬ ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ አስታውቀዋል።
ባንካችን አቢሲንያ በቅርቡ ይፋ ባደረገው አፖሎ የዲጅታል ባንክ እጅግ ዘመናዊ የፋይናንስ አግልግሎቶችን ይዞ የመጣ ሲሆን አሁንም አሽከርካሪዎችን የሚጠቅም የሥራ አማራጭ ከሊትል ታክሲ ጋር በአጋርነት አቅርበዋል።
ሊትል ታክሲ በአይነቱ ልዩ የሆነ፣ የ7 ዓመት የአገልግሎት ልምድ ይዞ የመጣ የአሽከርካሪ መተግበሪያ ሲሆን ፣ የኢትዮጵያን የሜትር ታክሲ ዘርፍ በማዘመን ተመራጭ አገልግሎት እየሠጠ አሁን ላይ በስምንት የአፍሪካ ሀገራት በሥራ ላይ ይገኛል።

ባንካችን አቢሲኒያ፤ ሊትል ታክሲ አሽከርካሪዎችን በሁሉም ዘርፍ ጠንካራ፣ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን በመረዳት እጅግ ዘመናዊ በሆነው አፖሎ ዲጂታል ባንክ በኩል ተጨማሪ የገቢ ምንጭ እንዲሁም የብድር አማራጭ በማቅረብ የሥራ ቆይታቸውን ምቹ ለማድረግ በማሰብ ይህን ዕድል አመቻችቷል።
የአቢሲንያ ባንክ የከስተመር አኩዚሽን ዳይሬክተር አቶ አባይ ስሜ "ከሊትል ታክሲ ጋር በመተባበር ለአሽከርካሪዎች ተጨማሪ የሥራ ዕድል በመፍጠራችን ተደስተናል " ብለዋል። "ይህ አጋርነት አሽከርካሪዎች የገቢ ምንጫቸውን እንዲያሻሽሉ እና በኢትዮጵያ ያለውን የራይድ-ታክሲ ኢንዱስትሪ ዕድገትን ይደግፋል" በማለት አክለዋል፡፡
የሊትል ታክሲ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባሮክ በበኩላቸው "ለአሽከርካሪዎቻችን አማራጭ የሥራ ዕድሎችን እና የፋይናንስ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ከአቢሲንያ ባንክ ጋር በመተባበር መሥራታችን አሽከርካሪዎች ደንበኞቻችውን እንዲያሳድጉ እና ህይወታቸውን እንዲያሻሽሉ በጣም ይረዳቸዋል" ብልዋል።
አሽከርካሪዎች ይህን ዕድል ለመጠቀም ማድረግ የሚጠበቅባቸው ፡-
# የአፖሎ መተግበሪያን በማውረድ መጠቀም
# የሊትልን መተግበሪያ በማውረድና በሊትል መስራት
ይህን_ሲያደርጉ፡-
* የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን ዕድሉን ያገኛሉ
* ሰዎች አፖሎን እንዲጠቀሙ በማድረግ በእያንዳንዱ ሠው የሚታሠብ ተጨማሪ ገቢ ያገኛሉ
አፖሎን ለማውረድና ለመጠቀም ዝግጁ ይሁኑ!
ተሣፋሪዎን ወይም ጓደኞቾን አፖሎ ላይ ይመዝግቡ!
#ለመመዝገብ_እንዲሁም_ለተጨማሪ_ማብራሪያ:
7933 ሊትል/8397 አቢሲንያ ባንክ ይደውሉ ወይም ቦሌ ደንበል አከባቢ በሚገኘው ቢትወደድ ባህሩ አብርሀም ህንፃ 9ኛ ፎቅ፡ ሊትል ቢሮ በአካል በመገኘት መመዝገብ ይችላሉ፡፡

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
Apollo :https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
Littile : https://play.google.com/store/apps/details?id=com.craftsilicon.littlecabrider