2022-04-05 23:25:14
ይሔ አንቺን አይገልፅም!፨፨፨፨፨//////////፨፨፨፨፨
አዎ! ይሔ አንቺን አይገልፅም፤
ይሔ ያንተ ማንነት አይደለም።
ሰውኛውን የሰው ልጅ ባህሪ በመተው በሰዎች ውድቀት ከፍ ብሎ መታየት፣
በሌሎች ህመም መደሰት፣
በሰዎች የኋሊት ጉዞ ድል አድራጊነትን ማክበር የከባድ ምቀኝነት ህመም ነውና ልንጠየፈው ይገባል።
አዎ! ጀግኒት..! ክፋትን በክፋት መመለስ፣
የጎዳሽን ለመጉዳት መጣጣር፣
ጉዳቱን፣ ህመሙን መመኘት፣
ለሰበረሽ የስብራት መንገድ መፈለግ፣
ለጣለሽ ዳግም እንቅፋት ሆኖ መገኘት
አንቺን አይገልፅም። ያንቺ ተሽሎ መገኘት የሚታወቀው ከወረዱት ጋር በመውረድ ሳይሆን ላለመውረድ በመታገለ፣ ከእነርሱም ተሽሎ በመገኘት ነው። ለጎዳሽ ጉዳትን አትመኚም፤ ያንቺን ስቃይ ማንም እንዲያየው ስለማትፈልጊ፤
ለጠላሽ፣ ለገፋሽ መጠላትን መገፋትን አትመኚም የመጠላትን፣ የመገፋትን ስሜት ስለምታውቂ፤
ላዋረደሽ መቼም ውርደትን አትመኚም ይልቅ ክብርን፣ ሞገስን ትመኚለታለሽ።
አዎ! ያንቺ መገለጫ ይሔ ነው። ጥላቻን በፍቅር መሻር፣ ክፋትን በበጎነት፣ ስብራትን በመልካምነት ማበስ።
አዎ! ጀግናዬ..! በሰው ስኬት መቅናት፣
በሰው ከፍታ መከፋት፣
በሰው ደስታ መናደድ፣
በሌላው ማማር፣ በሌላው መዋብ ማዘን በፍፁም
ያንተ ማንነት አይደለም። እርሱን ለትንሾችና ለታሰሩት ተውላቸው፤ አንተ እራስህን በመልካምነት፣ በበጎነት፣ በቅንነት ነፃ አውጣ።
የሰው ልጅ ምርጫ ግሩም ነው ምንም እንኳን ሁሉም ለክፋቱ ምክንያት ባያጣም ለመልካምነት ሲሆን ግን ለክፉነት የተገኘው ያ በቂ ምክንያት መጥፋቱ ይገርማል። ምናልባት እጅጉን መልካምና ቅን የሚባለው ሰው ከማንም በላይ ተበድሎ፣ ተጎድቶ፣ ተሰቃይቶ ይሆናል፣ ነገር ግን ክፉ መሆን እየቻለ መልካምነትን መርጧል። ቀላል ስለሆ አይደለም፤ ጫና ስለሌለው አይደለም፣ ስሜቱን ማዳመጥ አቅጦትም አይደለም ቢታመምም መድሃኒቱ በጎነት እንደሆነ ስላመነ ነው፤
ቢሰበርም ጠጋኙ መልካምነት እንደሆነ ስለገባው ነው፤
ምንም ቢከፋ የሰው ደስታ ለእርሱ እረፍቱ እንደሆነ ስለተረዳ ነው።
አዎ! የክፋትን ጥግ ቢያሳዩህም አንተም ተሽለህ ለመገኘት የመልካምነትን ጥግ አስጎብኛቸው።
የቅስምን ስብራት፣ ጥልቁን ህመም ቢያሰሙህም የስብራቱን መድሃኒት፣ የህመሙን ፈዋሽ በጎነትን ከልብህ አካፍላቸው።
የጣለህን ተነስተህ አንተም ዳግም ብትጥለው መቼም ከእርሱ አትሻልም፤ ያንተ ተሽሎ መገኘት የሚታየው ከወደክበት ተነስተህ እርሱንም ይዘሀው መጓዝ ስትጀምር ነው።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
2.1K views...1669 kiya Tesfu fikadu, 20:25