Get Mystery Box with random crypto!

ይህንን ያውቃሉ?-ጊዜ ካልዎት ጨርሰው ያንብቡ -------------------------------- | Biruk Getiso-ብሩክ ገቲሶ

ይህንን ያውቃሉ?-ጊዜ ካልዎት ጨርሰው ያንብቡ
--------------------------------
ሁሉም ሰው በተመሳሳይ ሳይክል ያልፋል።
ይወለዳል
ያድጋል
ይሞታል።
የሁሉም ሰው እድገት እንጂ ውልደትና ሞት ተመሳሳይ ነው፤ምንም እንኳ የመሞቻችን ምክንያት የተለያየ ሊሆን የሚችል ቢሆንም።

እድገት ላይ ግን:-
አንዱ እድሜ ልኩን ሲቸገር፣አንዴም ሳይስቅ የራሱ የሚባል ነገር እንደናፈቀው ኖሮ ይሞታል።
አንደኛው በጣም ሲቸገር ኖሮ የሆነ ሰዓት ላይ አልፎለት ተንደላቆ ኖሮ ይሞታል።
ሌላኛው ከእድገት እስከ ሞት ችግር የሚባል ሳያውቅ እንደተዝናና ደስተኛ ኑሮ ኖሮ ይሞታል።
ሌላኛው በቅንጦት ከሚኖርበት ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ተቸግሮ ተሰቃይቶ ይሞታል...ወዘተ.

➬ሁሉም ሰው ስወለድ ባዶ እጁን ይመጣል። ስሞትም ባዶ እጁን ይሞታል።
➬ሰው ስኖር ተንደላቆ ኖረም ተሰቃይቶ ኖረም መሞቱ አይቀርም።
➬ፎቅ ቤት የሠራም ጎዳና ላይ የሚኖርም በተመሳሳይ መንገድ ያልፋሉ(መወለድ_ማደግ_መሞት)።
➬ምድር ላይ ኖሮህ ቢትሞት ለምድራዊ ዝናና አክብሮት እጅግ ጠቃሚ ነው። ነገር ምድር ካልተቀበለችህ ደስታህን ከነጠቀችህ፣አልመችህ ካለችህ ምድራዊ ዝናም ሆነ አክብሮት አታገኝም።
➬ምድራዊ ዝናና አክብሮት ማግኘትም ሆነ አለማግኘት ግን ከሞት አያድንም።
➬ምድር ያልተቀበለችውንም የተቀበለችውንም አንድ ላይ የሚቀበል ዘላላማዊ ሠማይን ላለማጣት መኖር ግን ከየትኛውም ምድራዊ ድሎት ይበልጣል።
የዛሬን ሁሉን ነገር ረስተን ዘላለም ወደምንኖርበት ወደ ሰማይ መግቢያ መንገዳችንን በየሀይማኖቶቻችን ዛሬ መጥረግ እንጀምር።
ከክፋት እንራቅ። መልካም ብቻ እንሁን። ከዚያ ዘላለም እናርፋለን!!!

መልካም ቀን!
ብሩክ ገቲሶ!