Get Mystery Box with random crypto!

ዮሴፍ ጌትነት - Yoseph

የቴሌግራም ቻናል አርማ bieteyoseph — ዮሴፍ ጌትነት - Yoseph
የቴሌግራም ቻናል አርማ bieteyoseph — ዮሴፍ ጌትነት - Yoseph
የሰርጥ አድራሻ: @bieteyoseph
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 552
የሰርጥ መግለጫ

የተራበች ነፍስ ፣ የተራበ ሀገርና ህዝብ የሃይማኖት አዝመራን የሚሸምትበት ፤ የቅዱሳንን ዳረጎትና ፍርፋሪ የሚቋደስበት ፤ የሕይዎት ክንውኑን በኦርቶዶክሳዊ እሳቤ የሚያነፅርበት ገፅ ነው!
የዚህ ኅብረት አካል ሲሆኑ ፤ ለተቸገሩት የመድረስን እርምጃ ወደ ፊት ይጓዛሉ፥ያስቀጥላሉ።
ለአሁንና ለነገው ትውልድ ፥
ዛሬን በቤተ-ዮሴፍ ማዕድ !
ቤተ-ዮሴፍ
https://t.me/bieteyoseph

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-10 20:07:33 Watch ""የአበውን ርስት አንሰጥም" ZwT || ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን (Official Video)" on YouTube


100 views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 13:12:35
207 views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 09:00:17
ፊልጵ 4፥4-9
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይብልላችሁ።
ገርነታችሁ ለሰው ሁሉ ይታወቅ።
ጌታ ቅርብ ነው።
በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጅ በአንዳች አትጨነቁ።

አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።

በቀረውስ ወንድሞች ሆይ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን እነዚህን አስቡ።

ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ ፤ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
211 viewsedited  06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 08:18:04
ለዛሬ
ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 37 ፣ 39 ፣ 40 ፣ 41 ፣ 42 እና 45ን እንድታነቡት ጋበዝኩ በማስቀጠልም
በዮሴፍ ታሪክ መነሻነት ሃሳቦችን በተከታታይነት እንጋራለን።

የምዕራፎቹ ቁጥር ቢበዛም ፦
• ምዕራፎቹ አጫጭር
• ታሪኩም ስትጀምሩት ለማቋረጥ የማያስመኝ ነውና አንብቡት።
ስትጨርሱ አሳውቁኝ።
መልካም ቀን
ዮሴፍ ጌትነት
02/10/2014 ዓ.ም
187 views05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 13:58:58
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተመዘገቡ ታሪኮች ውስጥ ያለውን አሁናዊ የእግዚአብሔር መልእክት በተከታታይነት መመልከቱ መልካም ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

ለዚህም፦
1- መጽሐፍ ቅዱስ ቢኖረን መልካም ነው።
2- ተከታታይነት ስላለው ፥ ይህንን በ "ቤተ-ዮሴፍ" ለመከታተል የሚሆን መደበኛ ጊዜ ይኑረን።
3- ድንቅ እይታችሁን እያጋራችሁ ፥ ንሥርነታችሁ ይለምልም ፤ ተሳታፊ ሁኑ።
4- የተጋራነውን ወደ ሕይዎት ለመቀየር ፥ በየጊዜው ራሳችን ቆም ብለን በመፈተሽ ተግባራዊ የሕይዎት ልምምድ እናድርግ።
5- ሌሎች ይህንን ኅብረት እንዲቀላቀሉ የድርሻችን እንወጣ

መልካም ቀን
መልካም ወር
ዮሴፍ ጌትነት
226 viewsedited  10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 20:21:53
እንኳን ለመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን ፥ አደረሳችሁ
ከቅዱሱ ረድኤትና በረከት ያሳትፈን።

====
አርኬ
ሰላም ለልደትከ ከመ ገብርኤል አደሞ
፮ተ አውርሀ ለልደተ ክርስቶስ ዘይቀድሞ
ዮሐንስ ምዑዝ እምስሂን ወቀናንም
ለእለ ነበብኩ በጽሒቅ ለመልክእከ ሰላም
ከመ ከላስስት በሕፅንየ ሲም
====
236 viewsedited  17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 21:26:40 Watch "አዲስ መዝሙር "ክነፈ ርግብ" ዘማሪ ዲያቆን ሀብታሙ እሸቴ እና ዘማሪት ሰብለወንጌል እሸቴ" on YouTube


302 views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 21:55:52 ዮሴፍ ጌትነት - Yoseph pinned «ቢያንስ ከሦስት ቀን አንድ ቀን ወደ ፩ - <<ቤተ-ዮሴፍ>> Group ወይም ፪- <<ዮሴፍ ጌትነት>> Channel በዓላማ የምትገቡ አባላት በሚቀጥሉት ሦስት ቀን ውስጥ "እኔ አለሁ" ብላችሁ እንድታሳውቁኝ ስል በትህትና አሳስባለሁ። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን። ዮሴፍ ጌትነት 26/10/2014 ዓ.ም»
18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 20:47:24 ቢያንስ ከሦስት ቀን አንድ ቀን ወደ
፩ - <<ቤተ-ዮሴፍ>> Group
ወይም
፪- <<ዮሴፍ ጌትነት>> Channel
በዓላማ የምትገቡ አባላት
በሚቀጥሉት ሦስት ቀን ውስጥ "እኔ አለሁ" ብላችሁ እንድታሳውቁኝ ስል በትህትና አሳስባለሁ።
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን።
ዮሴፍ ጌትነት
26/10/2014 ዓ.ም
299 views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 20:02:55
አግኝቻቸው በረከትን ለመቀበል ከምሳሳላቸው ትልቅ አባቶች አንደኛው አባት ነበሩ።

የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ የዛሬ 10 ወር ገደማ አገኘዋቸው።
በአባታዊ ፍቅር ተቀብለው ፥ ሰላም ለኪ ደግመውልን ተቀመጥን።
የሄድኩት ከትንሽ ወንድሜ ጋር ነበር። <<ከየት መጥታችሁ ነው?>> ሲሉ ጠየቁኝ።
ከባ/ዳር አልኳቸው።
<<ባ/ዳር መነኩሴ የለም >> እንዴ አሉኝ።
ከዛም ወዳሉት እንሄዳለን ፥ ወደዚህም ብንመጣ ጥሩ ነው ብለን ነው አልኳቸው።
ስለጊዜው አጫወቱን።
መፍትሔው ቤትን ዘግቶ ማልቀስ ነው አሉን።
የሚያስፈልገወት ምንድን ነው ፥ ስል ጠየቅሁ። <<ቤ/ክኑ እየተሰራ ነውና የቻላችሁትን አድርጉ። እኔ የምፈልገው እሱን ነው።>> ሲሉ አሳሰቡኝ።
ሌላ ጊዜ ደግሜ ሂጀ መጠየቅ እንዳለብኝ ባስብም ፤ ዳግም በአካል ላላገኛቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ሰማው።
(የኔታ ነብዬ ልዑል)
አባታችን በረከተወ ይድረሰን።
283 viewsedited  17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ