Get Mystery Box with random crypto!

#ድንግልና እና #ክብረንፅህና በአብርሃም (@AbrishEL) እና ቤተ | Marriage Tube

#ድንግልና እና #ክብረንፅህና


በአብርሃም (@AbrishEL)
እና
ቤተል(@BetiEL) የተዘጋጀ

#ድንግልና፡-

የወንዶችም ሆነ የሴቶችን የአካል መቆጠብ ለመግለፅ የምንጠቀምበት ቃል ሲሆን ይሄም የሚያገለግለው ከግብረ ስጋ ግንኙነት መቆጠብን ይመሰክራል፡፡ ይህ የመቆጠብና የመጠበቅ ሒደትም ለሰውነቴ ክብር መስጠት ነውና የሰውነትን ንፅህና ለመግለፅ ስንጠቀምበት ክብረ ንፅህና (የንፅህና ክብር) በማለት ይብራራል፡፡

#ድንግልና_በምን_ይገለፃል?

በእርግጥ ለሁለቱም ፆታ መታቀብን ተከትሎ ቢያገለግልም በወንዶች ላይ መታቀቡና መጽናቱን ተከትሎ የሚታይ አካላዊ ለውጥ የለም፡፡ በሴቶች በኩል ግን የተራክቦ አካላት ከሆኑት መሀል በብልት አካባቢ ይህን የድንግልና መገለጫ ምልክት ይሆን ዘንድ ተፈጥሮ አስቀምጦት ይገኛል፡፡

#በምን_መልኩ?

ድንግልና በሴቶች ብልት በራፍ ላይ የተቀመጠ አነስተኛ መጠን ያለው በደም ስሮች የተሞላ ስስና ሴንሴቲቭ /ስሱ/ የሆነ የሰውነት ክፍል ነው፡፡ ይህ ስስ የሰውነት አካል ለሽንትና ለወር አበባ መፍሰሻ በሚያገለግል መልኩ በትንሿ ጣት ልክ ክፍተት ያለው ክብ ቀዳዳ ነው፡፡

#የድንግልና_አይነት

የድንግልና አይነት በተለያዩ ሴቶች ላይ በአራት (4) ሁኔታ ይገኛል፡፡

1ኛ. ሙሉ የብልት አካልን በራፍ እንደ መጋረጃ የዘጋና ለወር አበባና ለሽንት ማለፊያ በትንሿ ጣት ልክ ቀዳዳ በክብነት ያለው ሆኖ ይገኛል፡፡


2ኛ. ብዙ ጊዜ ባይሆንም በአንዳንድ ሴቶች ላይ እንደሚታየው የወንፊት መልክ በያዘ የተበሳሳ በርካታ ቀዳዳዎች ሙሉ ለሙሉ የብልቱ በራፍ የተጋረደ ሆኖ የሚገኝበት ሁኔታ ነው፡፡


3ኛ. በተፈጥሮ ምንም አይነት የሰውነት ክፍል በብልቱ በራፍ ላይ ሳይጋረድ ወይም የብልቱ በራፍ ከሆነው ቀዳዳ በላይ በሆነ አካል ግርዶሽ ተሸፍኖ የሚገኝበት አጋጣሚም አለ፡፡

እነዚህ በተፈጥሮ የሚሆኑ ሲሆኑ በግንኙነት ጊዜ በሚፈጠረው ፍትጊያና በወንዱ አካል (ብልት) የሚወገዱ ናቸው፡፡

4ኛ. በተፈጥሮ በጠነከረ ቆዳና በቀላሉ በወንዱ አካል (ብልት) ሊወገድ የማይችል አይነት ነው(ጭንጫ ድንግል ይባላል)፡፡

ይህ አይነቱ ድንግልና ብዙ ጊዜ በህክምና ተቋም በመሄድ በቀዶ ህክምና ከሴቷ ብልት በራፍ የሚወገድ ለተራክቦ አካሏ የሚስተካከልበት ሁኔታ ነው፡፡

ከሞላ ጎደል የሴት ልጆች ድንግልና በዚሁ መልኩ በተፈጥሮ የሚሰጣቸው ልዩ ፀጋ ነው፡፡

ይህ ፀጋ ደግሞ አንዴ በመወለድ የሚገኝ የአንድ ጊዜ ዕድል ነውና በህይወታቸው ውስጥ ሴቶች የማይረሱት አሻራን ያስቀምጡ ዘንድ ሰፊ ዕድል ያለው ነው፡፡ ይህ አካልና የክብር መግለጫ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚደረግ የግብረስጋ ግንኙነት ሊጠፋ ይችላል፡፡



ድንግልና በምን ሊጠፋ ይችላል

በግብረ ስጋ ግንኙነት

በአላስፈላጊ እንቅስቃሴ፣

በፈረስና ሳይክል ግልቢያ፣

ከባድ ዕቃ በማንሳትና በጀርባ በመሸከም በሂደት በመስፋትም ሆነ በመተርተር ሊጠፋ ይችላል፡፡


#ድንግልናዬ

Share Join Share
መልካም ቤተሰብ እንመስርት!
ለበለጠ ቤተሰብ ይሁኑ
@Biblicalmarriage
@Biblicalmarriage
ይቀላቀሉን
━━━━━━━━━━━━

እንዴት እንደምንወዳችሁ!