Get Mystery Box with random crypto!

#ድንግልናዬን_ለማን_ልስጥ በአብርሃም ( @AbrishEL)          እና ቤተል ( @Bet | Marriage Tube

#ድንግልናዬን_ለማን_ልስጥ

በአብርሃም ( @AbrishEL)
         እና
ቤተል ( @BetiEL)

#ድንግልና( Virginity) ማለት ድንግልና /ክብረ-ንፅህና/ የሚለዉ ቃል ቀጥታ ትርጉም አገልግሎት ያልጀመረን ወይም ያለመነካትን የሚያመለክት ሲሆን በተለይ ከተነሳንበት የጋብቻ ወይም ጾታዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ምንም እንኳን በኅብረተሰባችን በነበረዉ ልማዳዊ አጠራር ቃሉ የግብረ ስጋ ግንኙነት ከወንድ ጋር ፈጽመው የማያውቁ ሴቶች መጠሪያ ሆኖ ቢያገለግልም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከሴት ጋር አድርገው የማያውቁ ወንዶችም ድንግል የሚባሉበት ሁኔታ አለ::

የሴት ድንግልና የሚለይበት በብልቷ ግብረ ሥጋ
ግንኙነት ማከናወኛ በግቢያ በር ላይ የሥጋ ልፋጭ መሰል ሽፋን ሲሆን ይህም ሽፋን በእንግሊዝኛው / hymen /ተብሎ ይጠራል።

የድንግልና መለያ ወይም ስስ የክብረ ንጽህና ሽፋን
ዓይነታቸዉ አራት ሲሆኑ በሁሉም ሴቶች ላይ የሚኖረዉ
ዓይነት ምንም እንኳን በተፈጥሮ ተወስኖ የተፈጠረ ቢሆንም ሆኖም ግን ከግብረ ስጋ ግንኙነት ዉጭ ድንግልናየሚጠፋባቸዉ ወይም የሚወገድበት የጥንቃቄ ጉድለቶች በመኖራቸዉ ተገቢዉ ጥንቃቄ ማድረግ ድንግልናን ከመጠበቅ አንጻር በጣም ጠቃሚነቱ የጎላ ነዉ፡፡

ከላይ ለመፃፍ እንደሞከርነው የሴትም የወንድም ድንግል እንዳለ ገልፀናል። ስለዚህ እነዚህ #ድንግል የሆኑ ሰዎች ድንግልናቸውን ለማን መስጠት አለባቸው የሚለውን ሃሳብ ልንዳስስ ወደናል።
…………………………………………………………………………

#ሃሳብ1. ነገ ስለምንጋባ ዛሬ ድንግልናሽን ስጪኝ!
…………………………………………………………………………
  ስለነገ እርግጠኛ መሆን የሚችለው ጌታ ብቻ ነው። ነገ ምናልባት የሆነ አደጋ ደርሶብህ ልትለያዩ ትችላላችሁ። ያን ጊዜ ደግሞ ዛሬ ድንግልናዋን በነገ ተስፋ ያጣች ሴት ለቀጣዩ እጮኛዋ ለማስረዳት ጭንቅ ውስጥ ትገባለች። ይህም ሰው የሰውን ሰርቋል!

ስለዚህ ይህ ንግግር ውሸትና ከትክክለኛነት የራቀ ነው!
………………………………………………………………
#ሃሳብ2. ድንግልናሽን የማትስጪኝ ከሆነ እንደማይወትጂኝ አውቃለሁ!
………………………………………………………………

ብዙ እህቶች በዚህ ነገር እንደተጎዱ ይነግሩናል። ይህን ካላደረገች እንደሚለያት እሷም ያንን ፍራቻ ድንግልናዋን ትሰጣለች። ይህ ደግሞ ከምንም በላይ እግዚአብሔርን መበደል ነው። ሥለዚህ እንዲህ ብሎ ለሚጠይቃው ሳው መልሱ "እውድሃለሁ ነገር ግን ድንግልናዬን ለአንተ መስጠቴ ለአንተ ያለኝን ፍቅር ለመግለጥ አልጠቀምበትም። የምትታገስ ከሆነ ከተጋባን በኋላ እንደርስበታለን" ብሎ መመለስ ነው።

………………………………………………………
#ሃሳብ3. Sex ካላደረግን እለይሻለሁ!
………………………………………………………

እንደዚህ አይነት አፍቃሪ ቢቀርብሽም ችግር የለውም። እያስፈራራ የሚቆይ...አብሮ ለመሆን Sex ማድረግን የሚፈልግ። Sex የማታደርጊው እግዚአብሔርን ለማክበር ነው። በዛ ደግሞ ጌታ ይደሰታል። ስለዚህ Sex ካላደረግን እለይሻለው ለሚለው አትጨናቂ አንቺ ብቻ ለጌታ ታማኝ ሁኚ!

…………………………………………………………………
#ሃሳብ4. ድንግልናሽን ሳላረጋግጥ አላገባሽም ሥለዚህ SEX እናድርግ
…………………………………………………………………

በቅድሚያ ለምድነው የማገባው የሚለው ጥያቄ ሊመለስ ይገባል። አንዳንድ ሰው Sex ለማድረግ ብቻ አስቦ ያገባል። ጋብቻ ከዛም ያለፈ ነው። ድንግል ነኝ ካለችህና የእውነት ድንግል ከሆነች እመናት። ምናልባት በተለያየ አደጋ ምክንያት( ተደፍራ,በጥንቃቄ ጉድለት) ድንግልናዋን አጥታም ከሆነ ከምር ካፈቀርካት እመናት!

ስለዚህ ድንግልናን ለማሳመን ተብሎ #ዝሙት ማድረግ አይጠበቅም!

ታዲያ ድንግልና የሚሰጠው ለማን ነው
ድንግልናን ለመገርሰስ የግድ ወሲብ መፈፀም ግድ ነው። ግ ረ ስጋ ግንኙነት ደግሞ የሚደረገው እጮኛሞች ከተጋቡ በኋላ ነው። ሥለዚህ ድንግልና የሚሰጠው ለዛሬው እጮኛ ሳይሆን ነገ ካገባነው በኋላ ባል ለሚሆነው ሰው ብቻ ነው።


#ምክር!

ድንግልና ክብር ነው። በአንድ #አፈ_ቀላጤ ነገሽን ማበላሸት የለብሽም። ድንግልናሽን ጠብቂው።


ድንልናቸውን በአደጋ ምክንያት ሊያጡ ይችላሉ?
ካጡስ ምን ማድረግ አለባቸው?

የወንድ ልጅ ድንግል አለ እንዴ????

ይቀጥላል!...

#ለሴቶች ድንግልናዬን የምሰጠው ለባሌ ብቻ ነው የምትሉ እህቶች ጠቅ አድርጉ

#ለወንዶች ከእጮኛዬ ድንግልናዋን የምወስደው ካገባዋት በኋላ ነው እኔም ድንግልናዬን ለሷ እጠብቀዋለው የሚል ወንድ ጠቅ ያድርግ


ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ
@Biblicalmarriage_bot ይጠቀሙ!
       Share Join   Share
      መልካም ቤተሰብ እንመስርት!
     ለበለጠ ቤተሰብ ይሁኑ
      @Biblicalmarriage
      @Biblicalmarriage
             ይቀላቀሉን
     ━━━━━━━━━━━━

       እንዴት እንደምንወዳችሁ!