Get Mystery Box with random crypto!

'ጥቂት ጊዜ' የሚያጽናና ቃል. . . “በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ | ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

"ጥቂት ጊዜ" የሚያጽናና ቃል. . .

“በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ
#ለጥቂት_ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 5፥10

“በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን
#ለጥቂት_ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 1፥6-7

#ጥቂት_ጊዜ ተውሁሽ፥ በታላቅም ምሕረት እሰበስብሻለሁ።”
— ኢሳይያስ 54፥7

“ቍጣው
#ለጥቂት_ጊዜ ነው፥ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን፤ ልቅሶ ማታ ይመጣል፥ ጥዋት ግን ደስታ ይሆናል።”
— መዝሙር 30፥5