Get Mystery Box with random crypto!

“....እንዘ ይፀውረኪ በሐቂፍ ወይስዕመኪ በአፍ አመ አፍለሰኪ ወልድ ውስተ የማኑ ለዐሪፍ ጽጌ ዕፀ | ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

“....እንዘ ይፀውረኪ በሐቂፍ ወይስዕመኪ በአፍ
አመ አፍለሰኪ ወልድ ውስተ የማኑ ለዐሪፍ
ጽጌ ዕፀ ገነት ማርያም ዘትጼንዊ ለአንፍ
እንዘ ይትጓድዑ አክናፈ በክንፍ
ለቀበላኪ ወረዱ አእላፍ....”

".....ለአፍንጫ መዐዛን የምትሰጪ የገነት ዛፍ ማርያም ሆይ፤ ልጅሽ በክንዱ ዐቅፎ በአፉ እየሳመ በቀኙ ሊያሳርፍሽ ባሳረገሽ ጊዜ፤ አንቺን ለመቀበል ክንፍ ለክንፍ እየተጋጩ እልፍ አእላፋት መላእክት ወረዱ...."

ማሕሌተ ጽጌ


እንኳን ለአምላክ እናት ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም (ኪዳነምህረት) #በዓለ_ትንሣኤ_ወዕርገት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡

መልካም በዓል ይሁንልን።