Get Mystery Box with random crypto!

ለዛሬ ዩቲዩበር ለመሆን ያሰባችሁ ልታውቋቸው የሚገቡ ነገሮችን እንጠቁማቹ በአሁን ሰዓት ዩቲዩበ | Beteseb Media

ለዛሬ ዩቲዩበር ለመሆን ያሰባችሁ ልታውቋቸው የሚገቡ ነገሮችን እንጠቁማቹ

በአሁን ሰዓት ዩቲዩበር መሆን ከፍተኛ ስራ የሚጠይቅ ነገር ነው! ምክንያቱም YouTube በ2018 ያወጣው ህግ ብዙዎች ቻናል ለመክፈት ያሰቡ ሰዎችን ወደኋላ እንዲመለሱ ያደረገ ነገር ነው! በዛው ልክ ደግሞ በራሳቸው ፈጠራ እና ብርታት ለሚሰሩ Youtubers ትልቅ ደስታ ሆኗል..

ህጉ ምን ነበር፡
አንድ ዩቲዩበር ከቻናሉ ላይ ብር ለማግኘት (Monetization : enable ለማድረግ) ቢያንስ እነዚህን ማሟላት አለበት!
ቻናሉ ከተከፈተ 12ወር / 1አመት መሙላት አለበት!
ቻናሉ ላይ የለቀቃቸው ቪዲዮዎች ተደማምረው 4000 ሰዓት መታየት አለባቸው!
ቻናሉ ቢያንስ 1000 ሰብስክሪፕሽን ሊኖረው ይገባል (1ሺ ሰው ሰብስክራይብ ሊያረጉለት ይገባል)

ትልቁ ራስ ምታት መስፈርቶቹ ትንሽ ከበድ የሚሉ ናቸው! ግን ትክክለኛ ታማኝ እንዲሁም ተፈላጊ መረጃ ለሚለቅ ሰው ቪዲዮዎቹ በ1-2 ቀን ውስጥ ሙሉ አለምን ሊያዳርሱ (Viral) ሊሆን ይችላል! ምክነያቱም አሪፍ Like, Share, Comment ስለሚያገኙ ዩቲዩብ ቪዲዮውን Score ያረገዋል።

በፕላኔታችን ትልቁ የ YouTube ቻነል የህንድ የሙዚቃ ቪዲዮ ቻነል T-Series ሲሆን አሁን 120 million subscribers አሉት። ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ትልቅ ሰብስክሪፕሽን ያየሁት የHope Entertainment ወደ 1.1 Million ነው!

አሁንም ለኢትዮጵያውያን ችግሩ ይበልጥ እየከበደ የሚመጣው ከጊዜ ወደ ጊዜ ዩቲዩብ ተጠቃሚ እየጨመረ ቢመጣም ግን Subscribe የሚያረግ ሰው ስለሌለ ነው! ስለዚህ ቻነል ያላችሁ ሰዎች ሰብስክራይብ የማድረግ ጥቅሙን በማስረዳት ብዙ Subscribers ማግኘት ይቻላል!

ዩቲዩበሮች ምን ያክል ይከፈላቸዋል፡

T-Series ከ 200ሺ እስከ 1.2 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በወር እንደሚከፈለው መረጃዎች ያሳያሉ! ወደ ሀገራችን ስንመጣ የHope Entertaimemt በግምት ስናይ በወር ብቻ 840ሺ+ የኢትዮጵያ ብር በወር ያገኛል ማለት ነው! ስለዚህ ዩቲዩበር መሆን ለፈለጋችሁ ብር ለማግበስበስ ሳይሆን ምርጥ ነገር መስራት ላይ ብቻ ትኩረታችሁን ካደረጋችሁ ብሩ ሳትፈልጉት ይመጣል!

የዩቲዩበሮች ትልቁ ችግር፡

ሰይብስክራይብ ከፈለክ አንተም ሰብስክራይብ አድርግ Comment ከፈለክ Comment አድርግ Like ከፈለክ አንተም የሌሎችን Like አድርግ!
እጅህን አጣጥፈህ ሌሎችን ብቻ የምትጠብቅ ከሆነ ስኬታማ አትሆንም!

የተፎካካሪያቸውን ቪዲዮ ምንም ሳያዩት Dislike ማረግ! ( ለምሳሌ እኔ የTECH ቻነል አለኝ ሌላ ሰውም እነደዚሁ እና እኔ የሆነ ቪዲዮ Publish ሳረግ እሱ መጥቶ ምን ይሁን ምን ቪዲዮውን ሳያይ በደመነፍስ Dislike ማረግ አንዱ የዩቲዩበሮች ችግር ነው! በተለይ የኛ ኢትዮጵያውያን አብረን ለመብላት ብቻ አንድ መሆን የለብንም ምንም ሀሳብ መስጠት ካልፈለግን ዝም ብለን ማለፍ!

የማይሆን እና ትክክለኛ ያልሆነ ቪዲዮ በመልቀቅ የሰውን ጊዜ ማቃጠል! ይህ ስኬት አይሆንም በቃ በትክክለኛው መንገድ መስራት ብቻ!

ምርጥና ትክክለኛ ነገር ለሚሰሩ ዩቲዩበሮች በYoutube ላይ Copy Paste አይቻልም፡

ለምሳሌ እኔ ከ2 ሰዓት በፊት ቪዲዮ ለቀቄ አንዱ መጥቶ ቪዲዮውን ዳውንሎድ አድርጎ መልሶ በራሡ ቻነል ላይ ቢለቀው Even ቻናሉ እስከመጨረሻው ማስጠፋት እችላለሁ! REPORT በማድረግ ብቻ! የCopy Right መብቴን ተጋፍቷል ብዬ Report ሳደርግ YouTube ያንን ነገር በማጣራት ትክክል ከሆነ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል እምቢ ካለ Delete The Channel. በተመሳሳይ ሁኔታ በምቀኝነት ተነሳስቼ ይህ ቪዲዮ የኔ ነው ብዬ Report ባደርግ የራሴኑ ቻናል ያጠፉታል።

ሽልማት
የዩቲዩበሮች ሽልማት የዩቲዩብ Play Button ነው ሽልማቱ ግን የተለያየ አይነት ደረጃ አለው!

ጥቅም፡

Graphite - ከ1,000 በታች subscribers ላለው ቻነል
Opal - 1,000 እና ከዚያ በላይ subscribers ላለው
Bronze - ከ10,000 በላይ subscribers ላለው

ሽልማት፡

The Silver Creator Award - ከ100,000 በላይ Subscribers ላገኘ
The Gold Creator Award - ከ1 million በላይ Subscribers ላለው
The Diamond Creator Award - ከ10 million በላይ Subscribers ላገኘ
The Custom Creator Award - ከ50 Million በላይ Subscription ላለፉ
The Red Diamond Creator Award - ከ100 Million በላይ Subscribes ላላቸው


https://t.me/BetsebMedia
https://youtube.com/@Betseb_Media