Get Mystery Box with random crypto!

 ዛሬ የኮምፒዩተሮች በተለይም የlaptop ኮምፒዩተሮች #CPU ስያሜ ላይ ነው የምናወራው፡፡   | Beteseb Media

 ዛሬ የኮምፒዩተሮች በተለይም የlaptop ኮምፒዩተሮች #CPU ስያሜ ላይ ነው የምናወራው፡፡  

❖አብዛኞቻችን በኮምፒዩተሮቻችን CPU ላይ ያለን እውቀት ውስን ነው፡፡

ለምሳሌ Core i3, Core i5 እና Core i7 #CPU አይነቶች ስናይ እላያቸው ላይ ባለው ቁጥር ብልጫ ብቻ እናወዳድራለን፡፡ ከዛሬ በኃላ ግን በትክክለኛው ስያሜ እንገመግማለን፡፡

በኮምፒዩተሮቻችን #CPU ላይ የምናየው ስሞች እላያቸው ላይ ፊደላት ይገኛሉ፡፡ እነሱ ለምን ተቀመጡ? እንዲሁ በዘፈቀድ የተቀመጠ ፊደላት ናቸውን?

እነዚህ ፊደላት ዝም ብለው የተቀመጡ አይደሉም የራሳቸው የሆን ትርጉም አላቸው፡፡

የኮምፒዩተሮቻችን #CPU ስም እነዚህን ፊደላት ከያዘ፡

“K” – Unlocked፡- ያልተቆለፈ CPU ይህ ማለት በቀላሉ Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበት መጠን መጨመር ‹በቀጣይ ዘገባዎች ላይ እናየዋለን›) የሚደረግ CPU ናቸው፡፡ እላያቸው ላይ “K” የሚል ፊደል የሌለበት የCPU አይነቶች የOverclock የመደረግ ሁኔታ አምብዛም ነው፡፡

ምሳሌ፡ Intel Core i5-8600K

“H” – High Performance Graphics: - እነዚህ CPU ለኮምፒዩተር ጨዋታዎች(Gaming) እና ፎቶ እና ቪዲዮ ለማቀናበር ይመረጣሉ ማለትም ብዙ ሀይል ተጠቀሚ እና የተሻለ አቅም ያላቸው #CPU ናቸው።

“Q” – Quad Core:- አራት Core ወይም አንድን ስራ ለአራት አካላት የሚከፋፈል #CPU  ናቸው፡፡

በዚህም መሰረት “HQ” ሚል ፊደላት ካሉ በጣም ውድ እና ምርጥ ከሚባሉት CPU አይነቶች  ወስጥ አንዱ ነው፡፡

ምሳሌ፡ Intel Core i7-7700HQ

”M” – Mobile CPU:- በተንቀሳቃሽ(Portable) ኮምፒዩተሮች ላይ የምናገኘው ሲሆን በቀላሉ ለመቀዝቀዝ ትንሽ ሀይል ይጠቀማል፡፡ በተጨማሪም ብዙ ጊዜ እንዲተኙ(Sleep mode capability) የደረጋል፡፡

“Y” - Extremely low Power

“U” – Ultra low Power

ከለይ ያሉት ሁለቱም የሚያመለክቱት ሀይል ቆጣቢ ወይም ዝቅተኛ አቅም ያላቸው CPU ናቸው፡፡

ምሳሌ፡ Intel Core i5-7200U

በቀጠይ ዳስሳዎቻችን ላይ ስለ ኮር(Core)፣ የ CPU ስም ላይ ያሉት ቁጥሮች ምንነት እና ስለ Core i3, Core i5 እና Core i7 ከሌሎቹ  #CPU የሚለያቸው አንዲሁም እርስ በእርስ ሚያለያያቸውን ነገሮች በሰፊው እናያለን፡፡

https://youtube.com/@Betseb_Media
https://t.me/BetsebMedia