Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ጊዜ ጅማ ዩንቨርስቲ ዋናው ግቢ ጉባኤ ግእዝ ቋንቋ ስንማር የተፈተናት ፈተና ትዝ አለችኝ። ፈ | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

አንድ ጊዜ ጅማ ዩንቨርስቲ ዋናው ግቢ ጉባኤ ግእዝ ቋንቋ ስንማር የተፈተናት ፈተና ትዝ አለችኝ። ፈተናው
"ብየ አክሊል ዲበ ርእስየ
መዓልተ እውዕል ታኅተ ሰብእ
ወሶበ በጽሐ ጊዜሁ ለምሴት አኀድር ላዕለ ሰብእ
መኑ አነ"
የሚል ነበር። "በራሴ ላይ አክሊል አለኝ፣ ቀን ቀን ከሰው በታች እውላለሁ፣ በምሽት ጊዜ ደግሞ ከሰው በላይ አድራለሁ። እኔ ማን ነኝ" የሚል እንቆቅልሽ ተጠይቆ። አንዱ ጓደኛችን ሲመልስ "ሱሪ" ነው አለ። ገረመንና አክሊሉ ምንድን ነዋ? ስንለው "ቀበቶው ነዋ" ብሎን አረፈ። ነገር ግን መልሱ አውራ ዶሮ ነበር። ዶሮ ቆጥ ላይ ስለሚያድር ማታ ከሰው በላይ ያድራል።

በይሁዳ ራስ ስለዞረው ዶሮ የሚናገር እና በጸሎተ ኃሙስ ስለታረደው ዶሮ የሚናገር መጽሐፍ መጽሐፈ ዶርሆ የሚባል አለ። ነገር ግን ያንን ሳነበው ፲፪ቱ ብልት የ፲፪ቱ ሐዋርያት ምሳሌ የሚል አላገኘሁም። ብቻ ያው ዶሮ ወጥ በፍስክ ሲበሉት ደስ ይላል። እንቁላልም ገንቢ ምግብ እንደሆነ ሐኪሞች ይነግሩናል። ከዚህ ውጭ የማውቀው ነገር እንደሌለኝ ስነግራችሁ በደስታ ነው።

መጋቤ ዶርሆ ወእንቁላል በትርሽ