Get Mystery Box with random crypto!

✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

የቴሌግራም ቻናል አርማ betgubae — ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠
የቴሌግራም ቻናል አርማ betgubae — ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠
የሰርጥ አድራሻ: @betgubae
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.73K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰንበት ትምህርት ቤት የሚሰጠውን ተከታታይ ትምህርት በጉባኤ ተገኝተው መማር ላልቻሉ በሃገር ውስጥም ከሃገራችንም ውጪ ለሚኖሩ ምዕመናን መማማሪያ የተከፈተ ነው።
t.me/betgubae
የፌስቡክ ኣድራሻዬንም ይጎብኙ https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-25 16:15:06
✥ ሥዕሉን ከሥዕሏ አጠገብ ይሥላሉ ✥
✥ ምስለ ፍልሰትኪ ደምርኒ እሙ ✥

. ነሐሴ 16 የሰማዕታት አለቃ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋው ከፋርስ ሃገር ወደ ሃገሩ ልዳ በክብር የፈለሰበት ነው። ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ እመቤታችንን ዕረፍተ ሞቴን በዕረፍተ ዕለትሽ አድርጊልኝ ይህም ባይሆን በዚህ አሕዛብ ሃገር ተቀብሬ አልቅር ከሚያምኑት ሃገር እቀበር ዘንድ ፍልሰተ ሥጋዬን ከፍልሰተ ሥጋሽ ዕለት አገናኝልኝ ብሎ ተማጽኗት ነበር።

. ይህም የዕለቱ አርኬ « ሰላም ለጊዮርጊስ ተውላጠ ፃማሁ ወሕማሙ። እንተ ተለዓለ ሞገሰ ስሙ። በፍልሰትኪ ድንግል ዘተቶስሓ ፍልስተ ዐፅሙ። እንዘ ይብል ሶበ ጸለየ ኀቤሃ ቀዲሙ። ምስለ ፍልሰትኪ ደምርኒ እሙ። » ተብሎ ተገልጿል ልመናውንም ተሰምቶለት የሥጋውም ፍልሰት ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የሥጋ ፍልሰት ጋር አንድ ሁኗልና ስለዚህም እርሷን መውደዱን የሚያውቁ ሥዕሉን ከሥዕሏ አጠገብ ይሥላሉ በስሙ ለሚማፀኑ የድኅነት ወደብ ይሆን ዘንድ።

ከፍልሰተ ሥጋዋ ሰማዕቱን ያሳተፈች እመሰማዕታት እኛንም ከበረከቷ ለመሳተፍ የበቃን ታድርገን።
(ስንክሳር ነሓሴ ፲፮)

አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ

https://t.me/betgubae (የቴሌግራም ቻናል )

https://t.me/fikarehayimanoti (የቴሌግራም ግሩፕ)

https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71

https://youtube.com/channel/UC8v52_jNY156sxZtplafDtw (የዩቱብ አድራሻ)
2.0K viewsAmha Silase ( Mekuria Tesfaye), 13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 09:07:17
እንኳን ለ መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት
60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳቹ
ነሐሴ 22 ከቀኑ 7:00 ጀምሮ ተገናኝተን
የሰ/ት/ቤት በዓል በጋራ እንዘክር

የዘመናችን አብነት፤
የትውልዱ የለውጥ ሐዋርያ፤
የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ምርኩዝ፤
ገነተ ጽጌ
2.4K viewsAmha Silase ( Mekuria Tesfaye), 06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 09:06:01
✥✥✥ ሰማይ ተገረመች ✥✥✥


➛ አስቀድሞ አባቷ ዳዊት « አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት» (መዝ 131፥8) ብሎ እንደዘመረው ድንግል እንደልጇ ባለትንሣኤ ከሙታን ተለይታ በልጅዋ ሥልጣን ተነስታ "ሰማይ ዳግሚት" ወደ ሰማይ ጉዞ አደረገች። ሰማይም ተገረመች አማናዊቷን ሰማይ ማርያምን ስላየች።
አስቀድሞ ሰማይ በምስራቅ መስኮቷ ወጥታ በምዕራብ መስኮቷ በመግባት በምትመላለሰው በብርሃኗ ፀሓይ ትመካ ነበረ፤ ከፀሓይ ይልቅ ሰባት እጅ የምታበራን እመኣምላክን ወደርሷ ስትመጣ ዓይታ ግን ግርማዋን አድንቃ « ይህች ሰማይ እንደዚህ ካበራች ከርሷም የተገኘው ፀሓየ ጽድቅማ እንደምን መንክር ነው ብላም ተደመመች »።

ጌታን መሸከም የማይችለው ኣቅሟንም አስባ፣ ሰማያውያን ኪሩቤል ሱራፌል ሊያዩት የማይደፍሩት አቅፋ ያሳደገች የዚች ታላቅ እናት ክብሯንም ተረድታ እንደ ቅድስት ኤልሳቤጥም አንደበቷም በምስጋና ተመልታ የእንግዳዬ ክብር ከማንም ይለያል የጌታዬ እናቱ ወደኔ ልትመጣ እንደምን ይሆንልኛ እያለች በትህትና ሆና በደስታ ዝማሬ ኣቀረበች። ፍጡራን በሙሉ የኔን ፀሓይ ሳይሆን ያንቺን ፀሓይ ይሙቅ ዳግሚት ሰማይ ሆይ « የጽድቅ ፀሓይ ይወጣላችኋል » የተባለለትን ወልደሽላቸዋልናም ኣለች። (ት ሚል 4፥2)

የንጉሥ እናት በቤተመንግሥት በክብር እንደሚያኖራት፤ ንጉሥ ክርስቶስም የከበረች እናቱን በመላእክት ዝማሬ በክብር አጊጣ በመንግሥተ ሰማያት ይኸው አንግሷት።

አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ

https://t.me/betgubae (የቴሌግራም ቻናል )

https://t.me/fikarehayimanoti (የቴሌግራም ግሩፕ)

https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71

https://youtube.com/channel/UC8v52_jNY156sxZtplafDtw (የዩቱብ አድራሻ)
2.3K viewsAmha Silase ( Mekuria Tesfaye), 06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 11:38:12 ✥✥✥ የተከደነች መጽሐፍ ✥✥✥

☞ አረጋዊው ጻድቅ ዮሴፍ በመንፈስ ቅዱስ ግብር የሆነውን የእመቤታችንን መጽነስዋን ባለመረዳቱ የጽንሱን ማደግ (የሆዷን መግፋት) ተመልክቶ ተደነቀ፡፡ እርሷንም ‹‹ኦ ወለተ እስራኤል መኑ ቀረጸ አክናፈ ድንግልናኪ ወእምኀበ መኑ ጸነስኪ - የእስራኤል ልጅ ከክብረ ድንግልናሽ ያሳጣሽ ፅንሱን የፀነሽ ከማን ነው? ›› በማለት የመጽነሷን ነገር ጠየቃት፡፡ እመ አምላክም መልኣኩ አክብሮ ከነገረኝ በቀር ምንም ምን ሌላ የማውቀው የለም በማለት በመንፈስ ቅዱስ ግብር መጽነስዋን ነገረችው፡፡

☞ አረጋዊውም ይሆንን? አይሆንን? በማለት ተጠራጠረ እንዲህ ያለውን ነገር ሰምቶት አያውቅምና ነገሩ ረቀቀበት ምስጢሩንም ሊረዳው ከበደው፡፡ ስለዚህም ነው ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹ መጽሓፍ ለማያውቅ ሰው የተከደነች መጽሐፍ ሰጡት እርሱም ማንበብ አይቻለውም›› አለ፡፡ (ት.ኢሳ. ፳፱ ፥ ፲፩)

☞ የተከደነች መጽሓፍ የተባለች ቅድስት ድንግል ናት፡፡ መጽሓፍ ሰጡት ማለቱ ጻድቅ ዮሴፍ እመቤታችንን ከቤተ መቅደስ ከካህናት እጅ እንደተቀበላት ያሳያል፡፡ ማንበብ አለማወቅ ጻድቁ ዮሴፍ በሥጋዋ አለመቀራረብ ጽንሷንም ባለማወቁ ይተረጎማል፡፡

☞ ጌታን ከወለደችው በኋላ ግን ሰብኣ ሰገል እጅ መንሻን ይዘው ከሩቅ ምስራቅ መጥተው መገበራቸውና መስገዳቸው፣ እረኞችና ይህን የመሰለውን ምልክት ዓይቶ በሕልምም ተረድቶ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች›› (ት. ኢሳ ፯፥፲፬) በማለት የተናገረው ድንግል የተባለች እርሷ ወንድ ልጅ (ኣማኑኤል) የተባለ ከእርሷ የተወለደ መሆኑን ኣወቀ፡፡ ስለዚህም ወንጌላዊው ማቴዎስ‹‹የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም›› ሲል ተናገረ፡፡ (ማቴ.፩፥፳፭ ) ይቆየን

አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ

https://t.me/betgubae (የቴሌግራም ቻናል )

https://t.me/fikarehayimanoti (የቴሌግራም ግሩፕ)

https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71

https://youtube.com/channel/UC8v52_jNY156sxZtplafDtw (የዩቱብ አድራሻ)
2.4K viewsAmha Silase ( Mekuria Tesfaye), 08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 07:38:01 ደብረ ታቦር የተባለው ጌታ ክብሩን የገለጠበት ስፍራ ደብረ ታቦር ስለሆነ በዚሁ በዓሉ ስያሜውን አግኝቷል፡፡

ቡሔ ይባላል ፡- ቡሄ ብርሃን ማለት ነው በደብረታቦር ቧ ብሎ የተገለጠውን የጌታችንን የፊቱን ብርሃን ጸዳል፤ የልብሱንም እንደ ነጭ በረዶ ጸዓዳ መሆን ያስረዳል፡፡
• አንድም፡- ቡሔ ማለት መላጣ (ገላጣ) ማለት ነው፡፡
ይኸውም በበዓሉ ዋዜማ ልጆች ‹‹ ቡሔ በሉ፤ ቡሔ መጣ ፣ ያ መላጣ፣ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ›› ይላሉ እዚህ ላይ ቡሄ ያለው ዳቦውን ነው፡፡
• አንድም፡- ‹‹ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለምሌሊት›› እንደሚባል ወቅቱ በሃገራችን የጸዓተ ክረምት ዋዜማ ስለሆነ የክረምቱ አፈናው ተወግዶ /ተጋምሶ/ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት ፤ በዶፉና በጎርፉ ተሸፍና የነበረች መሬት የምትገለጥበት በመሆኑ ነው፡፡
• አንድም፡- ቡሔ (ቡሔእየ) ተብሎ ይተረጎማል ይኸውም
የደብረታቦር እለት እርሾ ሳይገባበት ተቦክቶ የሚጋገረውን
ኅብስት ያሳያል፡፡

4. ችቦ የመብራቱ ፣ የሙልሙል ዳቦ የመጋገሩና የጅራፍ ማጮኽ ምክንያት፡-

መብራት የሚበራው 12 ለ13 ዋዜማ ሌሊት በ3 ሰዓት ነው ።
• የጌታችን ክብሩ በተገለጠበት ጊዜ ብርሃኑ የሌሊቱን ጨለማ ገፍቶት እስከ አርሞንዔም ደርሶ ነበርና በዚያ አካባቢ የነበሩ እረኞች በሁኔታው ተገርመው ቀንም መስሎኣቸው ሌሊቱም ተዘንግቷቸው በዚያው ቆይተው ነበርና ቤተሰዎቻቸው ምን አግኝቷቸው ይሆን በማለት መብራት አብርተው (ችቦ ይዘው)፣ የሚመገቡትን ይዘው ወገኖቻቸውን ፍለጋ ወጥተዋል እረኞችም ያሉበትን ቦታ ለቤተሰዎቻቸው ጅራፍን በማጮኸ አመልክተዋቸዋልና ይህን ለማሰብ ነው፡፡
• ዋናው ምሥጢሩ ግን፡- የችቦው ብርሃን የጌታ ክብር
መገለጡን፣ የጅራፋ ጩኸት ሓዋርያትን ያስደነገጣቸው የአብ የምስክርነቱ ቃል ምሳሌ ሲሆን፣ ኅብስቱ ጌታችን በመስቀል ላይ መሥዋዕት የመሆኑ (የሥጋወደሙ) ምሳሌ ነው፡፡
• ማስታወሻ፡- ከላይ እናዳየነው ጅራፋ መጮኹ የአብ የምስክርነቱ ቃል ምሳሌ ነው ይኸውም በታቦር ተራራ ላይ እንደሆነም ተገልጧል ስለዚህ ዛሬም ምሳሌነቱን ለማጉላት ጅራፍ የማጮኹን ሥርዓት በተራራ ማድረግ የተሻለ ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ ግን በርችትና በመሳሰሉት ማክበሩ ሃይማኖታዊ ትውፊት የለውም ይልቁንም ሰውን ለማስደንገጥ ተብሎ ርችትን በሰው ቦርሳ፣ ኪስ …. በመክተት ማስደንገጥ የበዓሉን ሥርዓት ማሳደፍም ከመሆኑም በላይ ከሃይማኖተኛ ሰው የማይጠበቅ የሰውንም መብትና ክብር መንካት ነው፡፡ ጌታችን በብርሃን ንስሓ እንመላለስ ዘንድ ዓይነ ልቡናችንን ብሩህ ያድርግልን፡፡ ይቆየን

አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ

https://t.me/betgubae (የቴሌግራም ቻናል )

https://t.me/fikarehayimanoti (የቴሌግራም ግሩፕ)

https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71

https://youtube.com/channel/UC8v52_jNY156sxZtplafDtw (የዩቱብ አድራሻ)
2.1K viewsAmha Silase ( Mekuria Tesfaye), 04:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 07:38:01 ✥✥✥ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚኣከ ይትፌስሑ✥✥✥
(መዝ.88÷12)

በዚህ ርዕስ ሥር

1. በዓሉ የሚከበርበትን ምክንያት/
ከሐዋርያት ሦስቱ ሓዋርያት ብቻ መመረጣቸው ፤ ከነቢያት ሙሴና ኤልያስ መገለጣቸው ስለምን ነው?
2. ደብረታቦር የተመረጠበት ምክንያትና ምሳሌነቱ
3. የበዓሉ መጠሪያ ስሞች (ደብረ ታቦር / ቡሄ/ ቡሔ መባሉ ስለምንድ ነው?)
4. ችቦ የመብራቱ ፣ ሙልሙል ዳቦ የመጋገሩና የጅራፍ ማጮኽ ምክንያት እንመለከታለን፡፡

1. ይህ በዓል ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ሲሆን የሚከበረው ጌታችን የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅነቱን ያስመሰከረበት፣ ጌትነቱን እና ክብሩን የገለጠበት በመሆኑ ነው፡፡ (ማቴ.17÷1 ማር.9÷2 ሉቃ.9÷28 2ጴጥ.1÷16-18)፡፡

ጌታችን ሐዋርያትን ‹‹ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ብለው ይሉታል? ›› ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ ቅድስናህን ዓይተው ሙሴ ነህ ይሉሃል፤ የኃይል ሥራህን ድንግልናውንም ዓይተው ኤልያስ ነህ የሚሉህ አሉ ……… ብለውት ነበረና እግዚኣ ሙሴ ወኤልያስ (የነቢያት ጌታ) መሆንኑን ለመግለጥ፤ አንድም ጌታችንም መልሶ ‹‹ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ? ›› አላቸው ቅዱስ ጴጥሮስም እስከ ክርቶስ ተብሎ የተነገረልህ ‹‹ አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ ›› አለው (ማቴ.16÷13-20/ ትን.ዳን.9÷25) ይህን በፍጡር አንደበት የተመሰከረውን ጌትነቱን በአብ ምስክርነት ለማጽናት እና በተግባር ለመግለጥ የሐዋርያትንም እምነታቸውን ለማጽናት አዕማደ ሓዋርያት የሆኑትን ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ቅዱስ ያዕቆብ፣ ቅዱስ ዮሐንስን ይዞ ወደ ቅዱሱ ተራራ ኣወጣቸው፡፡

ስለምን እነዚህን ብቻ አወጣቸው ቢሉ ለፍቅሩ ይሳሳሉና በፍቅሩ ይናደዳሉና ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታ እሞታለሁ ቢለው " አንተስ አትሞትም እኔ እሞታለሁ እንጂ " ማለቱ እኒም እኔ የምጠጣውን ጽዋ (ሞት) ልትጠጡ ትችላላችሁን? ቢላቸው " አዎ እንችላለን " (ስለኣንተ እንሞታለን) ማለታቸው እጅግ ቢወዱት ነው ስለዚህ ሦስቱን መረጣቸው፡፡

ቀሪዎችን ስምንቱ ሐዋርያትንና ይሁዳን ከእግረ ደብር አቆይቷቸዋል ከይሁዳም በስተቀር ከላይ ላሉት የተገለጠ ምሥጢር ከሥር ላሉትም ተገልጦላቸዋል፡፡ ይሁዳን ‹‹ያእትትዋ ለኃጥእ ከመ ኢይርአይ ስብሓተ እግዚአብሔር›› (የእግዚአብሔርን ክብር እንዳያይ ኃጢአተኛው ያስወግዱታል፡፡) (ትን.ኢሳ.26÷10) እንዲል ኋላ የሚሠራት ኃጢአት ይህን ምሥጢር እንዳያይ አድርጋዋለች ምሥጢር የማይገልጥለት ከሆነ ከሌሎች ሐዋርያት ጋር አበብሮ እንዲሆን
ለምን አስፈለገ ቢሉ ከእነርሱ ቢለየኝ በሞቱ ገባሁበት ብሎ ምክንያት እንዳያገኝ ነው፡፡

መልኩም በፊታቸው ተለወጠ፤ ፊቱም ከፀሓይ ይልቅ አበራ፤ ልብሱም ልብስ አጣቢ ከሚያነጻው ይልቅ እንደ በረድ ፀዓዳ ሆነ፡፡ ‹‹ እነሆ ሙሴና ኤልያስም ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው›› ቅዱስ ጴጥሮስም ጌታን ‹‹ አቤቱ በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ ሦስት ቤቶችን በዚህ እንሥራ፤ አንዱን ለአንተ÷ አንዱንም ለሙሴ÷ አንዱንም ለኤልያስ አለው›› በዚህ ቃል የትህትና እና የደካማነት ምልክት አለበት፡፡ ትህትና ያልነው ቅዱስ ጴጥሮስ ለራሱና ለባልንጀሮቹ ሓዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሰበ ነው ራሱንና ባልንጀሮቹን እንደ ባሮች፤ ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች (የጌታ ባለማሎች) አድርጎ አስቧልና፡፡ ደካማነት የተባለው ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን (ሰው የሆነበት) ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና
ራሱን የሚሰውርበትን ቤት ይሠራለት ዘንድ የተናገረው ነው፡፡ ስለዚህም ጌታችን ምድራዊ ቤት እንደማያስፈልገው ያስረዳው ዘንድ የክብሩ መገለጫ የሆነ ብሩህ ደመና መጥቶ እንደቤት ሁኖ ጋረዳቸው፡፡ ‹‹እነሆ በደመናው ውስጥም የምወደው በእርሱም ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል ቃል
መጣ፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው ደንግጠው በግንባራቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር፡፡ ጌታችን ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸው ተነሡ አትፍሩም አላቸው፡፡ ዓይናቸውንም አቅንተው ዓዩ ነገር ግን ከጌታችን ከኢየሱስ ብቻ በቀር ያዩት ማንም አልነበረም፡፡ ››

ከነቢያት ሁሉ ለይቶ ሙሴና ኤልያስ እንዲገለጡ ማድረጉ ስለምንድን ነው ቢሉ ሙሴ ከአምላክ ጋር 570 ጊዜ ያህል ቃል ለቃል ተነጋግሮት ነበርና ባለማልነቴ ይገለጥ ዘንድ ባይህ እወዳለው አለው፡፡ አምላክም ፊቴን ዓይቶ አንድ ሰዓት ስንኳ መቆም የሚቻለው የለም ብሎ መለሰለት ሙሴም ይህ ካልሆነማ ባለሟልህ መባሌ ምኑ ላይ ነው በቃልማ ሌሎቹንስ ታናግር የለምን ቢለው አምላክም " ድኅረሰ ትሬኢ ገጽየ " መሥዋዕት ሁኜ በምቀርብበት ጊዜ (በዘመነ ሥጋዌ) እታይሃለሁ ብሎት ነበርና ይህ እንዲፈጸም፡፡ (ዘጸ.33÷18-23)፤ ኤልያስ ስለአምላክ እጅግ በመቅናቱ ተስፋ ተሰጥቶት ነበርና፡፡ ክብሩ በተገለጠ ጊዜ ግን ሙሴ ‹‹ትኄይሰኒ መቃብርየ›› (መቃብሬ ትሻለኛለች ብሏል)፤ ኤልያስም ወደ እሳት ሠረገላው ተመልሷል፡፡
• አንድም፡- ሙሴ ኤልያስ ይሉሃል ብለውት ነበረና እግዚኣ ሙሴ ወኤልያስ መሆኑን በራሳቸው አንደበት ለማስመስከር፡፡
• አንድም፡- የሕያዋን (ሞት ያላገኛቸው) የሙታን (ሞት
ያገኛቸው) አምላክ መሆኑ ለማጠየቅ ነው ከእርሱ በቀር
የሙሴን መቃብር (ይሁ.ቍጥ.9)፤ ኤልያስም የተሰወረባት (ብሔረ ሕያዋንን) የሚያውቅ የለምና፡፡
• ፍጻሜው ግን፡- ደብረ ታቦር የቤተክርስቲያንና የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ እንድትሆን ነው፡፡

2. ደብረታቦር የተመረጠበት ምክንያትና ምሳሌነቱ፡-
• ደብረ ታቦር ማለት ደብር ተራራ ሲሆን ታቦር የቦታው ስም ነው ከኢያቦር ወገን የነበረ ቦር የሚባል ሰው ነበረና በሱ ስም ታቦር አሉት ታቦር ማለት ትልቅ ማለት ሲሆን "ታ" ን ጨምረው ታቦር ብለውታል።

በደብረ ታቦር ያደረገው በሌላ ያላደረገው ስለም ነው ቢሉ ትንቢቱ ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ ትንቢቱ ‹‹ ታቦር ወኣርሞንዔም በስመ ዚኣከ ይትፌሥሑ ›› (መዝ 88÷12)ያለው ነው። ምነው ክብሩን የገለጠ በታቦር አይደለምን አርሞንዔምንም አነሳ ቢሉ ብርሃኑ እስከ አርሞንዔም ደርሷልና ነው፡፡
ምሳሌው ፡- በዚህ ተራራ ላይ ነቢያቱ ዲቦራ ከባርቅ ጋር በመሆን የከነዓናውያን ንጉሥና የጦር መሪ ሲሳራንና ኢያቡስን በጦርነት ድል አድርገውበታል (መሳፍንት 4፥5–24) ጌታም በልበ ሓዋርያት ያደረ ሰይጣንን ድል ነሥቶበታልና፡፡
• ደብረ ታቦር የቤተክርስቲያን ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ ተራራ ላይ ብሉይን የሚወክሉ ነቢያት፤ ሓዲስንም የሚወክሉ ሐዋርያት እንዲሁም ሓጋጌ ሕግ የሆነም ጌታ እንደተገኙ በእግዚአብሔር ቤትም ብሉይና ሓዲስ እንደሚነገሩ ምእመናንም በእነዚህ ሕግ እንደሚመሩ ያስረዳል፡፡ መምህር ጳውሎስም ስለዚህ ነገር ሲያስረዳ ‹‹በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ ታንጻችኋልና፤ የሕንጻው የማዕዘን ራስ ድንጋይ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ እርሱም ሕንጻ ሁሉ የሚያያዝበት÷ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግንብ የሚያድግበት ነው፡፡ እናነተ በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ልትሆኑ በእርሱ ታነጻችሁ፡፡›› አለ፡፡ (ኤፌ.2÷20-21)
• አንድም፡- የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ናት ነቢያትም
ሐዋርያት አንድ ሁነው እንዲወርሷት፤ ከመዓስባን ሙሴን
ከደናግላን ኤልያስን አመጣ መዓስባንና ደናግላን አንድ ሁነው እንደሚወርሷት፤ ከምዉታን ሙሴን ከሕያዋን ኤልያስ አመጣ ሁሉም በትንሣኤ እንደሚወርሷት ለማጠየቅ፡፡

3. የበዓሉ መጠሪያ ስሞች (ደብረ ታቦር / ቡሄ/ ቡሔ መባሉ ስለምንድ ነው?)
1.3K viewsAmha Silase ( Mekuria Tesfaye), 04:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 20:17:36 ✥ ትውልድ ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ ✥

ርዕሳችን ላይ ያስቀመጥነው ቃል በተኣምረ ማርያም መቅድም ላይ የሚገኝ ሲሆን ብዙዎች የዚህን ቃል ትርጉም ባለመረዳት ሲጠራጠሩ ይታያል፡፡ በቤተክርስቲያን ያሉትም ሆነ ያላመኑትም ይህንን ቃል ሲያነቡና ሲሰሙ «ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ ሊባል እንዴት ይቻላል?» በማለት ጥያቄ ያቀርባሉ

መጽሐፍት ሊያስተላልፋ የፈለጉትን መልእክት መረዳት የምንችለው ቃል በቃል ያለውን በመመልከት ሳይሆን የቃሉን ፍቺ ወይም ትርጓሜውን ስንመረምር ነው፡፡

«ፍጥረት» የሚለው ቃል ትውልድ ሁሉ (ሰው ሁሉ) እንደ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ኦሪት ዘፍጥረትን ኦሪት ዘልደት ቢል አንድ ነው፡፡እንደዚሁም ‹‹ ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ » ሲል ሰውን የሚያመለክት ነው ኣመስጋኝ ፍጥረት ሰው ነውና፡፡ ስለዚህ ፍጥረት ሁሉ የሚለው ቃል በንባብ በንግግር ሊያመሰግን የሚችለው ፍጥረት ሰው ስለሆነ ሰውን ለመወከል እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ከዚህም ሁለት ነጥቦችን እንይዛለን ኣንደኛው ፍጥረት የሚለው በዘይቤያዊ ቋንቋ ስንተረጉመው ትውልድ እንደሚባል፡፡ ሁለተኛው ፍጥረት ሁሉ ያመሰግናል ሲል ኣመስጋኝ ሰውን የሚመለከት እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ይህን ከተረዳን ወደቀጣዩ ጥያቄ እናምራ፡-

→ ሰውስ ቢሆን ትውልድ ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ ሲባል እንዴት ነው ከተባለ :: ትውልድ ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን መፈጠሩ ምን የሚያሻማ ነገር ኣለው? እንደውም የሚገርመው ይህ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ያለው የቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ሆኖ ነው የምናገኘው፡፡ «ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል» /ሉቃ 1፤39/ ይላልና፡፡

→ ትውልድ የሚለው ቃል ከዚህ በኋላ የሚመጣውን ብቻ ሳይሆን ያለፈውንም ትውልድ ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ቃል እንደምንረዳው ያለፈውም ትውልድ ያመሰግናታል የሚመጣውም ትውልድ ያመሰግናታል፡፡ በመሆኑም ሰው ሁሉ እመቤታችን ማመስገኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ከተመሰከረና እንዲህ ከታመነ እመቤታችንን ለማመስገን ትውልድ ሁሉ ተፈጠረ መባሉ ምን ያስደንቃል፡፡

→ ሰው ለእመቤታችን ሲባል እንዴት ተፈጠረ ከሆነ ጥያቄው ፡፡ እኛ ሰዎች እግዚኣብሔር ይህንን ልጅ ባይሰጠኝ፣ ይህንንም ልጅ ባልወልድ ለእኔም ባይፈጥርልኝ ኖሮ... ኣንልምን ከዚህም በተረፈ ማስረጃችንንም መጽሓፍ ቅዱሳዊ ስናደርገው ሔዋን ለማን ተፈጠረች ብለን ስንጠይቅ ምላሻችን ለኣዳም የሚል ነው፡፡ ማን ፈጠራት ሲባል ደግሞ እግዚኣብሔር የሚለውን ጥርጥር የሌለበትን ምላሽ እንሰጣለን፡፡ ስለምን ለኣዳም ተፈጠረች ስንል ትረዳው ዘንድ ነው/ዘፍ 2፤18/፡፡

→ ስለዚህ እግዚኣብሔር ኣንዱን ለሌላው እንደሚፈጥር እንረዳለን፡፡ ኣዳም ሔዋንን ፈጠረ ማለት ታላቅ ክህደት ነው፡፡ ሔዋን ለኣዳም ተፈጠረች ማለት ግን ፈጣሪዋ ሌላ ነውና ክህደት ኣይሆንም፡፡ እንዲሁም ሔዋን ሌላ ምንም ተግባር ኃላፊነት ሳይኖራት እግዚኣብሔርን ሳታመልክ ፣ሳታመሰግን፣ ኣዳምን ብቻ እንድትረዳው ተፈጠረች ማለት ክህደት ነው፡፡ ለኣዳም መፈጠሯ ለእግዚኣብሔር መፈጠሯን ኣያፈርሰውም፡፡ እግዚኣብሔርን ታመሰግናለች፣ ታመልካለች፣ ትታዘዛለች ስለዚህ ለኣዳም ተፈጠረች መባሉ ችግር የለውም፡፡ ይህም በመጽሓፍ ቅዱስ ላይ ባለቤቱ ልዑል እግዚኣብሔር ሔዋንን ለአዳም ረዳት እንድትሆነው እንፍጠርለት ነው ያለው፡፡ ለእኔ ልፍጠር እንኳ" ኣላለም፡፡ ስለዚህ ሔዋን ኣዳምን ስለምትረዳው ለእርሱ ተፈጠረች ተባለ፡፡ እንደዚሁም ትውልድም ሁሉ ለእመቤታችን የሚያደርገው በጎ ነገር ኣለ ይኸውም ማመስገን ነው፡፡ ስለሆነም ትውልድ ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጥሯል፡፡

→ ኣስቀድሞ እንደተመለከትነው «ትውልድ ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ» የሚለው ቃል ጋር የሚመሳሰል በመጽሓፍ ቅዱስ በሉቃስ ወንጌል ላይ «ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል» ኣለ፡፡ ሆኖም በዚህ ላይ ምንም ጥያቄ ኣልተፈጠረም፡፡ በተኣምረ ማርያም መጽሓፍ ላይ ግን በሚገኝበት ጊዜ መናፍቃን ጥያቄ ፈጠሩ ፡፡

→ የተኣምር የገድላት የድርሳናት በኣጠቃላይ ኣዋልድ መጽሓፍትን ስለማያምኑ መጽሓፍ ቅዱስ ላይ ያለው ቃል እንኳን ኣዋልድ መጽሓፍት ላይ ቢታይ ጥያቄ ይፈጥርባቸዋል፡፡ ለምን ግን መጀመሪያ መጽሓፍ ቅዱስን ኣይጠይቁም ኣምነናል ብለው ስለሚያስቡ ነው፡፡ ማመናቸው በመጽሓፍ ቅዱስ ላይ እንዳይጠይቁ ያደርጋቸዋል ኣለማመናቸው ደግሞ ባለመኑት መጽሓፍ ላይ ጥያቄ ይፈጥርባቸዋል፡፡ እኛ ግን በተኣምረ ማርያም እናምናለን እግዚኣብሔር በእመቤታችን ኣማላጅነት የሠራቸው ተኣምር የተጻፈበት መጽሓፍ ነውና፡፡


→ ሌለው እግዚኣብሔርን ላናመሰግነው እርሷን ብቻ ልናመሰገን ነው እንዴ የተፈጠርነው እንዳይባል ሔዋን ለአዳም ተፈጠረች መባሉ እግዚአብሔርን ኣታመልክም ማለት እንዳልሆነ ሁሉ እኛም እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠርን መባሉ ለእግዚአብሔር የምናጎድለው ምንም ነገር የለም፡፡ ተኣምረ ማርያምን የጻፈው ጻድቅ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ በሉቃስን ወንጌል «ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል» የሚለውን ቃል መሰረት በማደረግ «ትውልድ ሁሉ እመቤታችን ለማመስገን ተፈጠረ» በማለት ጽፏል፡፡ የሉቃስን ወንጌልን ቃል ከተቀበሉ የተኣምረ ማርያም ቃልንም መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡ ስለዚህ ፍጥረት ሁሉ ለእመቤታችን ተፈጠረ ተባለ፡፡

አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ

https://t.me/betgubae (የቴሌግራም ቻናል )

https://t.me/fikarehayimanoti (የቴሌግራም ግሩፕ)

https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71

https://youtube.com/channel/UC8v52_jNY156sxZtplafDtw (የዩቱብ አድራሻ)
2.1K viewsAmha Silase ( Mekuria Tesfaye), edited  17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 15:46:17
✥ማኅደረ ስብሓት ✥ የምስጋና ማደሪያ✥

ጥያቄ፦ እመቤታችን ማኅደረ ስብሓት መባልዋ ስለምንድ ነው?

መልስ፦ ማኅደር የተባለች እመቤታች ስትሆን ስብሓት የተባለው ጌታችን ነው። ጌታችን ስብሓት(ምስጋና) መባሉ ምስጋና የባህርይ ገንዘቡ በመሆኑ ነው። ምስጋና የባህርይ ገንዘቡ የሆነን ጌታ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህፀንዋ የያዘች እመብርሃን ማኅደረ ስብሐት ትባላለች። (ሉቃ 2፥13–14)

2— እመብርሃን ጌታችንን በመፅነስዋ ቅዱሳን መላእክት ማህፀንዋን ዓለማቸው አድርገው ምስጋናን ያቀረቡባት አማናዊት መቅደስ በመሆንዋ ማኅደረ ስብሓት ትባላለች።

3– "ታዓብዮ ነፍስየ ለእግዚኣብሔር" ነፍሴ እግዚኣብሔርን ታላቅ ታደርገዋለች እንዳለችው ምስጋናው ዘወትር ከአንደበቷ ኣታቋረጥምና ማኅደረ ስብሓት ትባላለች። (ሉቃ1፥47)

አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ

https://t.me/betgubae (የቴሌግራም ቻናል )

https://t.me/fikarehayimanoti (የቴሌግራም ግሩፕ)

https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71

https://youtube.com/channel/UC8v52_jNY156sxZtplafDtw (የዩቱብ አድራሻ)
1.9K viewsAmha Silase ( Mekuria Tesfaye), 12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 17:01:19 #፯ቱ_ዕለታት_ለእመቤታችን_ምሳሌዋ_ናቸው

በዕለተ እሁድ ትመሰላለች

- በዕለተ እሁድ አሥራወ ፍጥረታት አራቱ ባሕርያት ተገኝተዋል። ከሷም ዘኮነ ምክንያተ ፍጥረት በህላዌሁ እንዲለው አሥራወ ፍጥረት ጌታ ተገኝቷልና ።

በዕለተ ሠኑይ ትመሰላለች

- በዕለተ ሠኑይ ከዚህ ምድር እስከ ብሩህ ሰማይ መልቶ የነበረውን ውሀ ከሶስት ከፍሎታል፣አንዱን እጅ ከላይ ሰቅሎታል ሐኖስ ነው አንዱን እጅ በዙሪያው ወስኖታል አንዱን እጅ አጽንቶ የብርሃን ማኅደር አርጎታል። ዕለቲቱ የሱዋ ጠፈር ከሱዋ የነሣው ሥጋ ብርሃን የጌታ ምሳሌ።

በዕለተ ሠሉስ ትመስላለች

- በዕለተ ሠሉስ ለታብቀል ምድር ሐመልማለ ሣዕር ዘይዘራዕ በበዘርዑ ወበበዘመዱ በበአርአያሁ ወበአምሳሊሁ ባለ ጊዜ በእጅ የሚለቀሙ አትክልት በማጭድ የሚታጨዱ አዝርዕት በምሳር የሚቆረጡ ዕፀዋት ለሥጋውያን ምግብ የሚሆኑ ተገኝተዋል። የመንፈሳውያን ምግብ የሚሆን ጌታም ከሱዋ ተገኝቷልና ።

በዕለተ ረቡዕ ትመሰላለች

- በዕለተ ረቡዕ በይቁሙ ብርሃናት በገጸ ማይ ካለ ጊዜ ለሥጋውያን ምግብ የሚሆኑ ፀሓይ ጨረቃ ከዋክብት ተገኝተዋል ። ለመንፈሳውያን ምግብ የሚሆን ጌታ ካሱዋ ተገኝቷልና ።

በዕለተ ሐሙስ ትመሰላለች

- በዕለተ ሐሙስ ለታውጽዕ ባሕር ዘቦ መንፈሰ ሕይወት ባለ ጊዜ በልባቸው የሚሳው በእግራቸው የሚሽከረከሩ በክንፋቸው የሚበሩ በደመ ነፍስ ሕያዋን ሁነው የሚኖሩ ፍጥረታት ተገኝተዋል። በልባቸው የሚሳቡ የሰብአ ዓለም በእግራቸው የሚሽከረከሩ ከትሩፋት ወደ ትሩፋት የሚሄዱ የባሕታውያን በክንፋቸው የሚበሩ ተመስጦ ያላቸው የሰማዕታት ምሳሌ።
ዕለቲቱ የሱዋ ባሕር የጥምቀት ምሳሌ ።

በዕለተ ዓርብ ትመሰላለች
ከዕለተ ዓርብ በኵረ ፍጥረት አዳም ተገኝቷል ዳግማይ አዳም ጌታም ከሱዋ ተገኝቷልና ።

በዕለተ ቀዳሚት ትመሰላለች በዕለተ ቀዳሚት ሥጋዊ ዕረፍት ተገኝቷል ወአእረፈ እግዚእነ እምኩሉ ግብሩ ዘአኃዘ ይግበር እንዲል ከሱዋም የመንፈሳውያን ዕረፍት ጌታ ተገኝቷልና ። ለወደፊቱ በሰፊው እንመለከታቸዋን ይቆየን።
አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ

https://t.me/betgubae (የቴሌግራም ቻናል )

https://t.me/fikarehayimanoti (የቴሌግራም ግሩፕ)

https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71

https://youtube.com/channel/UC8v52_jNY156sxZtplafDtw (የዩቱብ አድራሻ)
2.2K viewsAmha Silase ( Mekuria Tesfaye), edited  14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 16:32:26 ✥✥✥ እህቶሙ ለመላዕክት ✥✥✥

ጥያቄ:- እመቤታችን እህቶሙ ለመላዕክት (የመላዕክት እህት) የምትባለው ለምንድን ነው?

መልስ ፡-

፩ - እመቤታችን የመላእክት እኅት የተባለችበት ምክንያት የመጀመሪያው በንጽሕና በቅድስና የምትመስላቸው ስለ ሆነ ነው፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያን የእመቤታችንን ድንግልና ስትናገር ንጽሕት የሚለውን ቃል በማስቀደም ንጽሕት ድንግል በማለት ነው የምትጠራት፡፡ ብዙዎች ድንግልና ቢኖራቸውም ንጽሕና የታከለበት አይደለም፡፡ ከነቢቡ ከገቢሩ ቢነጹ ከኀልዮ ( ከማሰብ ) ኣይነጹም፡፡ ዝሙትን ለመፈጸም ጊዜ፣ ሰዓት፣ ቦታ ይህን የመሰለው ሁሉ ስላልተመቻቸላቸው ብቻ በድንግልና የሚኖሩ ኣሉ፡፡ በሌላም ጎኑ በበጎ እንኳን ብንመለከተው ኣንድ ሰው በትዳር ተወስኖ ለመኖር ኣጋር ይሆነኛል ብሎ ያሰበውን ሰው በትዳር ኣብሮ ለመኖር ጥያቄውን ሲያቀርብ ‹‹ እኔ እጮኛ ኣለኝ ›› ወይም ‹‹ ፈቃደኛ አይደለሁም ›› የሚለውን መልስ በሚያገኝበት ጊዜ ኃሳቡን ይለውጥና ሌላ የትዳር አጋር ፍለጋ ይጀምራል፡፡ እንዲህ ባለ መልኩ ብዙዎችን በኃሳቡ አግብቶ ይፈታል፡፡

- እመቤታችን ግን ይህን የመሰለው ምኞት እንኳ የለባትም፡፡ ለዚህም መላአከ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችን በዮሴፍ ቤት ሳለች አካላዊ ቃልን እንደምትጸንስ ባበሰራት ጊዜ ከዮሴፍ ቤት እንደመሆኗ ምንኣልባት ከዮሴፍ ሊሆን ይችላል ብላ ኣላሰበችም ይልቁንም ‹‹ ወንድ ሳላውቅ እንዴት ይሆንልኛል ›› በማለት ነበር መልስ የሰጠችው ይህም እመቤታችን ንጽሕት ድንግል በመሆኗ ነው፡፡ ይህ ቅድስናዋና ንጽሕናዋ የመላእክት እኅት አሰኝቷታል፡፡

- ቅዱሳን መላእክት ከኣዳም ውድቀት በኋላ በንጽሕና እነርሱን የሚመስላቸው አጥተው እጅግ ያዝኑ ነበር ኋላ ግን በንጽሕና እነርሱ የመስለች ከእነርሱም የምትበልጥ እመቤታችን በመገኘትዋ ደስ ተሰኝተውባታል ስለዚህም የመላእክት እህታቸው ተባለች።


፪ - ምክንያት ስንመለከት ቅዱሳን መላእክት ‹‹ እኅትነ ነያ ›› እያሉ ያመሰግኗታልና ነው፡፡

፫ - አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው ስለእመቤታችን ሲያስረዳን በመላእክት እየተጎበኘች ሰማያዊ መብልና ሰማያዊ መጠጥን በመላእክት እየተመገበች ያደገች በመሆኗ የመላእክት እኅት አሰኝቷታል፡፡ በአማላጅነቷ አትለየን ። ይቆየን

አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ

https://t.me/betgubae (የቴሌግራም ቻናል )

https://t.me/fikarehayimanoti (የቴሌግራም ግሩፕ)

https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71

https://youtube.com/channel/UC8v52_jNY156sxZtplafDtw (የዩቱብ አድራሻ)
2.4K viewsAmha Silase ( Mekuria Tesfaye), edited  13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ