Get Mystery Box with random crypto!

ቤተ ውዳሴ

የቴሌግራም ቻናል አርማ betetsadkanyeguzomahber — ቤተ ውዳሴ
የቴሌግራም ቻናል አርማ betetsadkanyeguzomahber — ቤተ ውዳሴ
የሰርጥ አድራሻ: @betetsadkanyeguzomahber
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 207
የሰርጥ መግለጫ

🙏 እንኳን በሰላም መጡ🙏
ሰላም የተዋህዶ ልጆች በዚህ የቴሌግራም ገጽ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዶግማ፣ቀኖና እና ትውፊትን የጠበቁ ስርዓተ አምልኮና ትምሕርቶች እንዲሁም ዝማሬዎች ይቀርቡበታል። ክርስቲያናዊ የሆኑ ማህበራዊ ጉዳዮችም ይነሱበታል።በተለይም በተለያዩ ጊዜያት የምናደርጋቸው የየአድባራትና ገዳማት ጉዞዎች ይተዋወቅበታል።

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-23 17:16:39
አስባ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን

ቤተክርስቲያኗ እምትገኘው በደቡብ ጎንደር ፎገራ ወረዳ ወጅ አውራንባ እና አለምበር መሀል መስመሩ አካባቢ እምትገኝ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ናት የተመሠረተችው በ2000 ዓ/ም ቢኾንም ግን እስካሁን ዋናው ቤተክርስቲያን በሚሰበሰበው ገንዘብ ቢሠራም ገና ቆርቆሮ መቀየር ይፈልጋል ግን ቅድሚያ ከዚህ በላይ እምታዩት ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ እሚዘጋጅበት ቤተልሔሙ ነውና እባካችሁ በኢትዮጵያ 150 ብር ብናወጣ ይሠራታልና እንተባበር አሁን ደግሞ እንደምታውቁት ክረምት ነው እናም መርዳት እምትፈልጉ ከታች የራሷ የቤተክርስቲያኗ አካውንት አለላችሁ

:1000322843977 አካውንት
አስባ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን
124 viewsእናት አለኝ የምታብስ እምባ, 14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 17:11:40
አስባ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን

ቤተክርስቲያኗ እምትገኘው በደቡብ ጎንደር ፎገራ ወረዳ ወጅ አውራንባ እና አለምበር መሀል መስመሩ አካባቢ እምትገኝ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ናት የተመሠረተችው በ2000 ዓ/ም ቢኾንም ግን እስካሁን ዋናው ቤተክርስቲያን በሚሰበሰበው ገንዘብ ቢሠራም ገና ቆርቆሮ መቀየር ይፈልጋል ግን ቅድሚያ ከዚህ በላይ እምታዩት ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ እሚዘጋጅበት ቤተልሔሙ ነውና እባካችሁ በኢትዮጵያ 150 ብር ብናወጣ ይሠራታልና እንተባበር አሁን ደግሞ እንደምታውቁት ክረምት ነው እናም መርዳት እምትፈልጉ ከታች የራሷ የቤተክርስቲያኗ አካውንት አለላችሁ

:1000322843977 አካውንት
አስባ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን
30 viewsእናት አለኝ የምታብስ እምባ, 14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 21:11:44
206 viewsBereket Damene, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 21:11:05 ከዚህም በኋላ ቅዱስ ላሊበላ የህንፃ ሥራውን ለመጀመር ቦታው ጫካ ስለነበር በሰፊው የማጽዳት ዘመቻ ካካሄደ በኋላ የት ቦታ መጀመር እንዳለበትና የማንን ቤተ መቅደስ መጀመሪያ እንደሚሰራ እንደገና በሱባኤ ለፈጣሪው ጥያቄ አቀረበ። በጥያቄው መሠረትም ቅዱስ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ እንዳየው የወርቅ መሰላል ከሰማይ እሰከ ምድር የብርሃን አምድ ተተክሎ ዛሬ ቤተ ማርያም ካለችበት ቦታ አርፎ መላእክት ሲወጡበት ሲወርዱበት ቅዱስ ላሊበላ አየ።

ቅዱስ ላሊበላ ሥራውን ከዚህች ቦታ እንደሚጀምርና መጀመርያ የእመቤታችንን ቤተ ክርስቲያን እንደሚሰራ አወቀ በዚህም መሰረት በመጀመርያ ደረጃ ቤተ ማርያም ሠራ። ከዚያም ቤተ መድኃኔዓለም፣ ቤተ መስቀልን፣ ቤተ ደናግል፣ ቤተ ጊዮርጊስ፣ቤተ ገብርኤል ወቤተ ሚካኤል፣ ቤተ መርቆሬዎስ፣ ቤተ አማኑኤል፣ ቤተ አባ ሊባኖስ። እነዚህን ቤተ መቅደሶች መንፈስ ቅዱስ ጥበብን ገልፆታልና ግድግዳውን፣ ጣራውን፣ በሩንና መስኮቱን፣ አእማዱን ቅኔ ማህሌቱን ልዩ ልዩ ቅርፅ እያመጣ እያስጌጠና እያሳመረ ከመላዕክት ጋር እመቤታችን እየተራዳችው በ 23 ዓመት በዚህ አጭር ግዜ ውስጥ እነዚህን አስደናቂ ቤተ መቅደሶች ሰርቶ አጠናቀቀ።

ቅዱስ ላሊበላ የአነፃቸው አብያተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ በውጭም አገር ብዙ እንደሆኑ ታሪኩ ይገልጻል። ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን እንደ ምሳሌ ብንመለከታቸው፦ አዲዲ ማርያም፣ አሸተ ማርያም ጀምሮ ነበር፣ ሶማልያ መቅደስ ማርያምን (መቃዲሾ ውስጥ) ብዙ የተጀመሩና ተሰብስበው አገልግሎት የሚሰጡ በኢትዮጵያ ብቻ 23 እንደሚደርሱ ታሪክ ያወሳል።

ቅዱስ ላሊበላ መዋዕለ ዘመኑን በሰላም፣ በፅኑ፣ በእምነት፣ በፍቅርና በአንድነት ከአሳለፈ በኋላ ንግስናውን ለወንድሙ ልጅ እንዲሁም ለአሳደገውና በረከቱን ለሰጠው ለቅዱስ ነአኵቶ ለአብ አስረክቦ በጾም በፀሎት ተወስኖ ኖረ። ከዚህም በኋላ የሚያርፍበት ጊዜ ሲደርስ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በብርሃን ሠረገላ ተቀምጦ የሚአስፈራ መብረቅን ተጐናጸፎ አእላፋት ሠራዊቶቹ ዙሪያውን ሁነው ወደርሱ መጥቶ እንዲህ አለው "ወዳጄ ላሊበላ ሆይ ሰላም ይሁንልህ እኔ በማይታበል ቃሌ እነግርሃለሁ ማደሪያህ ክብርር ሁሉ ከከበሩ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያቶቼ ጋራ ይሁን። በጸሎትህና በቃልኪዳንህ ለሚታመን እምነቱ እንደ ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ ደም መፍሰስ ይሆንለታል።

ወደ ቤተ መቅደስህም የሔደ በኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደሴ እንደ ሔደ ይሆንለታል መቃብርህንም የተሳለመ የሥጋዬን መቃብር እንደ ተሳለመ ይሆንለታል በዓመታቱ ወሮች ሁሉ የተራቡትን እያጠገበ፣ የተጠሙትንም እያጠጣ መታሰቢያህን የሚያደርግ እኔ የተሠወረ መና እመግበዋለሁ የሕይወት ጽዋንም አጠጣዋለሁ። በመታሰቢያህ ቀንም ዕጣን ወይም ስንዴ የሚያገባውን እኔ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት በውስጠኛው መጋረጃ አስቀምጬ ከተቆረሰው ሥጋዬ አቆርበዋለሁ፤ በአማላጅነትህም እየታመነ የገድልህንና የቃል ኪዳንህን መጽሐፍ የሚጽፈውን ያንተ ስም በተጻፈበት ቦታ እኔ ስሙን እጽፋለሁ፣ በፍጹም ልቡ ለሚያምን ይሁን የማይታበይ ቃል የተናገርኩ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ" አለው።

ቅዱስ ላሊበላም ይህን ቃል ኪዳን ስለ አጸናለት ክብር ይግባውና ጌታችንን እያመሰገነ በምድር ላይ ወድቆ ሰገደ። ጌታችንም ሰላምታ ሰጥቶት በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ። ከዚህም በኋላ ጥቂት ሕማም ታሞ ሰኔ 12 ቀን በ1197 ዓ.ም በ 96 ዓመቱ በሰላም ዐረፈ። ሲያርፍም ደገኛው ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጋር ነገራተ እግዚአብሔርን እየተነጋገሩ እንዳለ ድንገት እንደ እንቅልፍ ሸለብ አድርጎት እንደሆነ ታሪኩ ይገልፃል። ነፍሱንም የብርሃን መላእክት ተቀብለው የዘላለም ሕይወት ማደሪያ ወደሆነ ማረፊያው አስገቡት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ላሊበላ በጸሎቱ ይማረን!። ምንጭ፦ የሰኔ 12 ስንክሳርና ቅዱሳንና ድንቅ ሥራቸው የአራቱ ቅዱሳን ነገሥታት ታሪክ ከሚለው መጽሐፍ።

+ + +
"ሰላም ለላሊበላ ሐናፄ መቅደስ በጥበብ። በዕብን ይቡስ መሬት ርጡብ። ነሢኦ መባሕተ እምእግዚአብሔር አብ። በዘይትአመር ሎቱ ምስፍና ወምግብ። ወዝንቱ መዐር ተድላ ነገሥት ወሕዝብ። በዕለተ ተወልደ ተዐግተ በንህብ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ 12።
175 viewsBereket Damene, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 21:10:38 በመስማቱ "ምንድነው? የሚሰማው" ብሎ ባለሟሎቹን ሲጠይቃቸው "ቅዱስ ላሊበላ እየተገረፈ ነው" አሉት ንጉሡም ወዲያውኑ እንዲያመጡለት አዘዘ። ሲመለከተውም በሰውነቱ ላይ ምንም የግርፈት ምልክት አላየበትም ንጉሡም ጻጽቅና እውነተኛ መሆኑን ፈጣሪም ከግርፋትና ከጥፍት ከልሎታልና "እንኳንስ ሊሞት ግርፋቱ አልተሰማውም" በማለት እጅግ አደነቀ። ከባድ ሀዘንም ተሰማው። "አምላኬን በድያለሁ የማይገባ ሥራ ሰርቻለሁ" ብሎ ቅዱስ ላሊበላ በሕዝቡ መካከል "ከዛሬ ጀምሮ መንግሥት ለአንተ ይገባል በግፍ አስገርፌሀለሁ በድዬሀለሁም ይቅር በለኝ" በማለት ከጫማው ወድቆ ይቅርታ ከጠየቀው በኋላ መንግሥቱን አስረክቦ መንኖ ለመሔድ ወሰነ።

የእግዚአብሔር መንፈስ ያደረበት ቅዱስ ላሊበላም "ለይቅርታው ይቅር ብብያሁ ነገር ግነ መንግሥት የእግዚአብሔር ገንዘብ ናትና መንግሥትህን የምቀበለው ከእግዚአብሔር እንጂ ከአንተ አይደለም አንተም በዙፋንህ መቆየት አለብህ እኔ ግን መልካም ፈቃድ ከአምላኬ እስካገኝ ድረስ እጠይቃለሁ" ብሎ የዐፄ ገብረ ማርያም ጫማ ስሞ በፍቅር ተሰናብቶ ወጣ። በዚህ ጊዜ ሕዝቡና "መንግሥትን ያህል ነገር እንደ ቀላል ነገር ቆጥሮ አልነግሥም ብሎ በመሄዱ እንዴት የእግዚአብሔር መንፈስ ቢያድርበት ነው?" በማለት በችሎት ተቀምጦ ሁኔታውን በግብር ሲከታተል የነበረው ሁሉ እያለቀሱ ቅዱስ ላሊበላን ተከትሎ ወጣ። ቅዱስ ላሊበላ ግን በአላማው ፀንቶ በሰዎቹ ፍቅር ሳይታለል እግዚአብሔር የሰጠውን ረዳቱን ቅድስት መስቀል ክብራን ይዞ ወደ አክሱም ሄደ።

በአክሱም አካባቢ በአባ ጰንጠሌዎን ገዳም በጾምና በጸሎት ተወስነው ፈጣሪያቸውን እየተማፀኑ ሳለ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መጥቶ "ሰማያዊ ኢየሩሳሌምን እንዳየህ ምድራዊት ኢየሩሳሌምንም አይቶ ህንፃ ቤተ መቅደሱን በሰማያዊትና በምድራዊት ኢየሩሳሌም አምሳል ያንፅ ዘንድ ኢየሩሳሌም ሔዶ የተወለደበት ቤተልሔም፣ የተጠመቀበትን ዮርዳኖስ፣ የተሰቀለበትን ቀራንዮ፣ የተቀበረበትን ጎልጎታን፣ ደብረ ታቦርን ምስጢረ መለኮቱን የገለጸበትን አጠቃላይ ብዙ ተአምራት ያደረገበትን ሁሉ እንዲያይና እንዲሳለም መልአኩም እንደሚመራው መስቀል ክብራ ግን በዚሁ ከደናግሎች ጋር እንደምትቀመጥና ቅዱስ ሚካኤል እንደሚያጽናናት እንደሚጠብቃት መታዘዙን ነገረው።

በዚህም መሠረት ቅዱስ ላሊበላ ወደ ኢየሩሳሌም በፈቃደ አምላክ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ጠባቂነት በሱዳንና በግብጽ አድርጎ ኢየሩሳሌም ገባ። በዚያም ከላይ የተጠቀሱትን ቅዱሳን መካናትንና ሌሎችንም ቅዱሳት ስፍራዎች ለዐሥራ ሦስት ዓመታት በመዘዋወር ተመለከተ። ከዚህ በኋላ ቅዱስ ላሊበላ የጉብኝቱንና የተፈቀደለትን ጊዜ ሲፈጸም አሁንም መልአኩ ተገልጾ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ሄደ መንግሥትን ከዐፄ ገብረ ማርያም ተረክቦ የታዘዘውን እንዲሰራና በመንገድ በግብጽ ምድር የተበተኑትን ወገኖችን ወደ ኢትዮጵያ ይዞ እንዲሄድ የታዘዘ መሆኑን ገለጸለት። ቅዱስ ላሊበላም በፈቃደ አምላክ በግብጽ ያሉትን ክርስቲያኖች ሰብስቦ በጊዜው የነበረው የግብጽ መንግሥት የእስላም ሃይማኖት ተከታይ በመሆኑ እንዴት አድርጎ እንደሚያስተዳድራቸው ጠየቃቸው። ክርስቲያኖቹም እግዚአብሔርን ማምለክ እንደተከለከሉና በሀዘን በሰቀቀን የሚኖሩ መሆናቸውን ገለጹለት። በዚህ ዘመንም በመካከለኛው ምሥራቅ 3ኛው የመስቀል ጦርነት በመኖኑ ግብጻውያን ፊታቸውን ወደዚያ አዙረው ስለነበር ቅዱስ ላሊበላ በፈቃደ አምላክ በርካታ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ ኢትዮጵያ መጣ።

ዐፄ ገብረ ማርያም ወንድሙ ቅዱስ ላሊበላ ሕዝበ ክርስቲያንን ይዞ የኢትዮጵያ ምድር እንደረገጠ በሰማ ጊዜ በክብር የሚቀበሉት ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሰራዊት አሰልፎ ወደ ቤተ መንግሥቱ እንዲመጣ ላከበት። ቅዱስ ላሊበላም ከባለቤቱ ጋር እና ከሕዝቡ ጋር በአክሱም ስለነበር የእግዚአብሔር ፍቃድ እንደሆነና ጊዜም እንደደረሰ በማወቁ ልዋል ልደር ሳይል ወደ ቤተ መንግሥቱ መጥተ ከዐፄ ገበረ ማርያም ጋር ተገናኘ። ንጉሡ ዐፄ ገብረ ማርያም ቅዱስ ላሊበላ ወደ እርሱ መምጣቱን በሰማ ጊዜ በፍቅር እንባ ተቀበለውና ሕዝቡን ሰብስቦ አዋጅ ነግሮ "እንሆ የአምላክ ፈቃድ ደርሷል መንግሥት ለዚህ ቅዱስ ሰው ይገባል ብሎ ዙፋኑን ለቅዱስ ላሊበላ አስረክቦ ተሰናብቶ ዛሬ ቅዱስ ሐርቤ እየተባለ ወደሚጠራው ገዳም ዘግቶ በጾም፣ በጸሎት፣ በቀኖናና በንስሐ ሰውነቱን ለፈጣሪው አስገዝቶ በክብር የካቲት 16 ቀን ዐርፎአል።

ከዚህ በኋላ ቅዱስ ላሊበላ ንጉሥ ነኝ ብሎ ሳመካ ስልጣኑን ለሕዝቡ በመስጠት ሕዝቡን ይመራ ነበር። ሕዝቡም የቅዱስ ላሊበላን የሃይማኖት ጽናትና ደግነት እያየ "ይህን ጻድቅ ንጉሥ ዕድሜውን አርዝምልን" እያሉ ይጸልዩለት ነበር። የቅዱስ ላሊበላን ደግነት በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሕዝቦች ብቻ ሳይሆኑ በውጭም ያሉ ነገሥታትና ሕዝብ ጭምር ያውቁ ነበር በዚህም መሰረት እስላሙም ክርስቲያኑም ቅዱስ ላሊበላን አንስተው አይጠግቡም ነበር። በቅዱስ ላሊበላም ዘመነ መንግሥት ጊዜ ኢትዮጵያ በውጭው ዓለም ያላት ግንኙነት የሰላም፣ የፍቅር፣ የክብርና የደስታ ግንኙነት ነበራት ለዚህም ነበር 1189 ዓ.ም አካባቢ ሳላህ አዲን የተባለው የእስላም ንጉሥ በሦስተኛው የመስቀል ጦርነት ኢየሩሳሌምን በያዘ ጊዜ ከክርስቲያን ቅርሶች ዋና ዋናዎቹን በጎልጎታ በሚገኘው በጌታችን መቃብር አጠገብ ያለውን ዕሌኒ ንግሥት ቅዱስ መስቀሉን ያስወጣችበት ዋሻና በቤተልሔም ጌታ የተወለደበትን ጎል (በረት) ለቅዱስ ላሊበላ በስጦታ ያበረከተው።

የቅዱስ ላሊበላ ቤተ መቅደሶች አሰራርና ፍጻሜ፦ ቅዱስ ላሊበላ በዘመኑ ይህን ድንቅ ሥራ የሰራው ጮማ በመቆራረጥ ጠጅ በማማረጥ ልብስ መንግሥትን ለብሶ በመሽሞንሞን አልነበረም። ለአንዲት ደቂቃ መንፈስ እግዚአብሔር ያልተለየው ቅዱስ አባት ነበር። ፈጣሪው የሚመሰገንበትን የእርሱም ስም ለዘላለም የሚጠራበትን ቤተ መቅደስ ለማነፅም ሱባኤ ገብቶ ቦታው የት እንደሆነ ተረዳ። ነገር ግን የተገለጸለት ቦታ ቀይት የምትባል ባላባት ትኖርበት ነበር። ንጉሥ እንደመሆኑ መጠን ሌላ ቦታ ሰጥቶ መጠቀም ይችል ነበር። ግን የትሕትና አባት ነውና መብቷን ሳይነካ እራሱን ዝቅ አድርጐ "ቦታውን ለሥራ ፈልጌዋለሁና በገንዘብ ሽጭልኝ" አላት። እርሷም እጅግ ከፍ ያለ ገንዘብ ጠየቀችው። ይኸውም አርባ ጊደር ላም መግዛት የሚችል ገንዘብ ነበር የጠየቀችው እርሱም ምንም ምን ሳይል ወርቁን ከፈላት። ቀይትም ገንዘቧን ተቀብላ ሔደችና እንደገና ተመልሳ "የምኖርበት ቦታ ስጠኝ" አለችው። እርሱም "ወደፊት ሌላ ቦታ እስክሰጥሽ በዚህ ቆይ" ብሎ ዛሬ ቆይታ የምትባለውን ቦታ ሰጣት ከዚህም የተነሳ ከግዜ ብዛት የቦታው መጠራያ ስም ቆይታ ተባለች። ይህች ቦታ የምትገኘው ከላሊበላ ከተማ በስተ ምሥራቅ በግምት ሁለት ኪ.ሜ ርቀት ላይ ነው። ለዚህ ነበር አባቶቻችን ንጉሥ ላሊበላ በአንጡራ ገንዘቡ የገዛውን ቦታ ስለሆነ በቦታው የሃይማኖት ሸቃጮች የሃይማኖት ሸቀጥ አያካሂዱበትም በማለት ለመስዋዕትነት የተዘጋጁት አሁንም ቢሆን ወደፊትም በዚህ ዙሪያ ላይ መናፍቅ ቦታ እንደሌለው ሊያውቅ ይገባል።
114 viewsBereket Damene, 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 21:10:06 "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

ሰኔ ፲፪ (12) ቀን።

እንኳን ለተባረከና ለተመሰገነ በሰማያት ያለ ምሥጢርን ለአየ፤ ዐሥር አስደናቂ ቤተ መቅደስን ከዐለት ላይ ላነፀ፤ ክብሩ ልክ እንደ ሐዋርያት ለሆነ ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ ለካህኑ ለቅዱስ ላሊበላ ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን።

+ + +
ጻድቁ ካህኑ ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ፦ ቅዱስ ላሊበላ ከአባቱ ከዐፄ ዛን ስዩም ከእናቱ ከልዕልት ኪሪዮርና በ1101ዓ.ም ታኅሣሥ 29 ቀን በቤተ መንግሥ ተወለደ። ዐፄ ዛን ስዩም ከመንገሡ በፊት የዋግ ሹም ሆኖ ሲያስተዳድር ዑጽፍት ወርቅ የምትባል ሴት አግብቶ ንጉሥ ቅዱስ ገብረ ማርያምና ዮዲት የምትባል ልጅ (ርብቃም) የሚሉ አሉ ከወለደች በኋላ ዑጽፍተ ወርቅ ሞተች። ከዚህ በኋላ የክፍለ አገር ገዥ ከሆነው ረዳኢ ከተባለው የተወለደችውን ኪሪዮርናን አግብቶ ቅዱስ ላሊበላን ወለደው። ቅድስት ኪሪዮርና ማለት ቤተ ክርስቲያን ማለት ነው።

ቅዱስ ላሊበላ በተወለደ ጊዜ ነጫጭ ንቦች ሰፍረውበት እንደማር ሲልሱት እናቱ ስታይ በመደንገጥ "ላል ይበላል" በማለት ተናገረች። ይህም በአገውኛ ቋንቋ ልጄን ንብ በላው ማለት ነው። በዚህ መሰረቴ ላልይበላል ተብሎ እየተጠራ ሲኖር ከጊዜ ብዛት ላሊበላ ተብሏል። በነገራችን ላይ የተሳሳተ ትርጉም የያዙ አላዋቂዎች ላሊበላ ማለት ለማኝ እንደሆነ አድርገው በአንዳንድ አካባቢዎች ይናገራሉ። ላሊበላ ማለት ግን ጣፋጭ የንስሃ ጋሻ የጽድቅ አባት ማለት ነው እንጂ ለማኝ ለፍላፊ ማለት አይደለም።

ከዚህም በኋላ እናትና አባቱ ልጃቸው ወደፊት ንጉሥ ሆኖ ብዙ ሰራዊት የሚከተለው ትልቅ ሰውና መንፈሰ እግዚአብሔር ያደረበት መሆኑን በንቦች መክበብ በመረዳታቸው በ 40 ቀኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሰራዊትና ካህናት ታጅበው በእልልታና በደስታ ዐፄ ካሌብ በአሰሩዋት ማይ ማርያም በተባለችው ቤተ ክርስቲያን የክርስትናውን ሥነ-ሥርዓት አስፈጽመዋል። የክርስትና ስሙም ገብረ መስቀል ተብሏል። ቅዱስ ላሊበላ በቤተ መንግሥት ውስጥ ለነገሥታት ልጆች እንደሚሰጥ እንክብካቤና ሥነ-ሥርዓት በጥበብና በሞገስ አደገ። ዕድሜውም ለትምህትተ ሲደርስ መምህር ተቀጥሮለት ከፊደል እስከ ዳዊት የሚሰጠውን ትምህርት ያለማዳገም ከፈጣሪ በተሰጠው ፀጋ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተማረ።

በዚህም ላይ እንዳለ የበለጠ ፈጣሪውን ማገልገል በመፈለጉና በመምረጡ ቤተ መንግሥቱን ትቶ ትምህርቱን ለማሻሻል ወደ ምድረ ጎጃም ሄዶ አሉ ከተባሉ መምህራን በተለይም መምህር ኬፋ ከተባሉ ምሁር አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ተምሮ ወደ ደብረ ሮሃ ተመልሶ ሥርዓተ መንግሥትን ወንድሙ ቅዱስ ገብረ ማርያም እያስተማረው ሳለ ለምቀኝነት የሚያርፈው ሰይጣን በንጉሥ ባለሟሎች(አማካሪዎች) ላይ አድሮ የሁለቱን ፍቅር በጠሰው። ሰዎቹ ወደ ንጉሥ ቀርበው "ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ንገሥ እነሆ ላሊበላ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን በማግኘቱ አስተባብሮ ንጉሥነትዎን መንግሥቱ ሊቀማዎት ነውና እወቁበት" በማለት ነገሩት። ንጉሡም በነገሩ እጅግ ተቆጥቶ ወደ ማረፊያ ቤቱ ገብቶ እንጀራ አልበላም ውሃም አልጠጣም ብሎም እንደ ንጉሥ ዓክአብ ተጨንቆ ተጠቦ ሳለ እህቱ "ንጉሥ ሆይ ልብህ አይዘን አትጨነቅ ነገሩን ለእኔ ተወው" ብላ አረጋጋችው። ላሊበላ ግን ይህን ሁሉ ነገር አላወቀም ነበርና በንጹህ ልቦናው በቤተ መንግሥቱ እንደ ተቀመጠ ከዕለታት አንድ ቀን ኮሶ ታይቶት መድኃኒት እንድታጠጣው ቂመኛ እህቱን ጠየቃት እሷም የምታጠምድበትንና የምትገድልበትን ስታስብና ስትፈልግ ስለ ነበር ይህን አጋጣሚ በማግኘቷ ሀሳቡን ደስታ ተቀብለችውና ኮሶውን አዘጋጅታ መርዝ ቀላቅላ አቀረበችለት። ከእርሱ ጋራ የሚኖር የማለየው አንድ ዲያቆን ነበር። በባህሉም መሠረት ዲያቆኑ ቀምሶ ስለሚሰጥ ያንን ሲቀምሰው አስታወኮት ሞተ። የዲያቆኑንም ትውኪያ አንድ ውሻ በመላሱ ሞተ። ከዚህም በኋላ ላሊበላ መንፈሱ ታወከ። ከባድ ሀዘንም አደረበት። "እናንተ ንጹሐን ለእኔ በታዘዘው መቅሰፍት በመሞታችሁ እኔም የእናንተን መንገድ እከተላለሁ እንጂ ወደ ኋላችሁ ቀርቼ ነፍስ ገዳይ አልሆንም" አለና በውስጡ ፍቃደ እግዚአብሔር ስላለበት ፈጣሪ ሚስጥር ሊገልጽለት በመፍቀዱ በጽዋው የተረፈውን መርዝ አንስቶ ጠጣው። እርሱም ወዲያው ተዘረረና ወደቀ። በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት መጥተው ነፍሱን ወደ ፈጣሪ ወስዷት። ሥጋው ግን ሙቀት ስላልተለየው ሰዎች ለመቅበር ቢሞክሩ እንደእሳት እየፈጃቸው ሦስት መዓልትና ሌሊት በሚደንቅ ሁኔታ ተቀመጠ።

ቅዱሳን መላእክት ሰባቱን ሰማያት አንድ በአንድ እያሳዩ ወደ ፈጣሪ ነፍሱን ከአቀረቧት በኋላ እግዚአብሔር አምላክ "ወዳጄ ላሊበላ ሆይ የጠራሁህ እኔ ነኝ በማለት ወሰን የሌለውን ፍቅሩን ከገለጸለት በኋላ ሀይሉንና ጥበቡን በእርሱ ላይ አሳድሮ "ከከርሰ ምድር አብያተ ክርስቲያናትን እንደሚያንጽና በኢትዮጵያ አገር ላይ አርባ ዓመት እንደሚነግሥ ሕዝበ እግዚአብሔር ድንቅ ሥራውን በመመልከት ድኅነትን፣ በረከትን፣ ፀጋን፣ እንደሚያገኙ በተለይም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ኢየሩሳሌምን ለማየትና ለመሳለም ሲሔዱ የሚደርስባቸው መከራና ሞት ደማቸው ከፊቴ በመጮሁ በእርሱ ሥራ ኢየሩሳሌምን እንደሚያንፅና ለምን እንደሚሰራ ጥቅሙን በመግለጽ ይሰራ ዘንድ መመሪያ ሰጠው። ቅዱስ ላሊበላ ግን ይህን ማድረግ እንማይቻለው ቢገልጽም አምላክ ከእርሱ ጋራ እንደሚሆን ብቻ "ስሙ በአንተ ይሁን እኔ ነኝ የምሰራው" በማለት ገለጸለት። ከላይ እንደተገለጸው በድኑ መንፈስ ቅዱስ ሳይለየው እንደ እሳት ሰዎችን እየፈጃቸው ተጨንቀው ተጠበው በሁኔታው በመገረም ለሦስት ቀንና ሌሊት እንዳሉ በሦስተኛው ቀን ነፍሱ ከሥጋው ተዋሕዶ ተነሳ።

ቅዱስ ላሊበላም ከሰው ተለይቶ ከዘመድ ርቆ የሰው ድምጽ ከማይደርስበት ቦታ ሄዶ ሌት ከቀን በመጸለይ በጾምና በጸሎት ተወስኖ ከአምላኩ ጋር በበለጠ ግንኙነቱን እያጠናከረ እንዳለ አንድ ቀን ፈጣሪ ቅዱስ ገብርኤልን ላከውና መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ላሊበላን "የእግዚአብሔር አገልጋይ ላሊበላ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን እንሆ እግዚአብሔር አምላክ በኢትዮጵያ ላይ ካህንና ንጉሥ ሆነህ ሰዎችን ለመንግሥተ ሰማያት የምታበቃ ነህና በህገ አብርሃም ትወሰን ዘንድ ወዳንተ መጣሁ ስለሆነም ነገ በአሁኑ ሰዓት የምትመጣ በድንቅ ሥራዋ አምላክን ያስደሰተች አንዳንተ የተመለጠች ቅድስት ሴት ትመጣለችና እርሷን አግብተህ ልጅ ትወልዳለህና በሚያስደስት ቃል ተቀበላት" አለው። ቅዱስ ላሊበላ ግን ፍቃዱ እንዳልሆነ ቢገልጽም የእግዚአብሔር ትዕዛዝ እንደሆነ በድጋሚ ሲነግረው ቃሉን ተቀበለው።

እንደተባለውም በማግስቱ ቅድስት መስቀል ክብራ እንደ ብርቱካን፣ መዝ፣ የመሳሰሉትን ፍራፍሬዎች ይዛ ወደ ቅዱስ ላሊበላ ሄደች እርሱም በደስታ ተቀበላት። ከዚያም ነገረ እግዚአብሔርን ተነጋግረው ወደ ቤተሰቦቿ ወሰደችው። ለቤተሰቦቿ መልአኩ በህልም ነግሯቸው ስለነበር በደስታ ተቀበሉት። በዚያም በፈቃደ እግዚአብሔር በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጋብቻቸውን ፈጽመው በጾምና በጸሎት ተወስነው በመኖር ላይ ሳሉ ለምቀኝነት የማያርፈው ሰይጣን አሁንም ፈተናውን አዘጋጅቶ ሶስናን በሐሰት ዝሙትን ፈጽማለች ብለው እንደወነጀሏት ሁሉ ቅዱስ ላሊበላንም "ከቤተ መንግሥት ጠግቦ ወጥቶ የሰው እጮኛ ያባልጋል" በማለት ለንጉሡ ሹክተኞች ነገሩት። ንጉሡም ወታደሮችን ልኮ አስመጣውና ቀኑም ዐርብ ቀን በመሆኑ እንዲገረፍ አዝዞ ወደ ቅዳሴ ሄደ። ዘጠኝ ሰዓት ላይ ወደ ቤቱ ሲሄድ የጅራፍ ጽምጽ
90 viewsBereket Damene, 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 21:10:05
82 viewsBereket Damene, 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 21:08:43 ባሏም ከዐረፈ በኋላ ባሏ ያዘዛትን መሥራት ጀመረች ሰይጣንም ግን ቀናባት በመበለት ሴት መነኵሲት ተመስሎ ከእርሷ ጋራ ተነጋገረ እንዲህም አላት "እኔ አዝንልሻለሀለ እራራልሻለሁም ገንዘብሽ ሳያልቅ የልጅነትሽም ወራት ሳያልፍ አግብተሽ ልጅ ትወልጂ ዘንድ እመክርሻለሁ ባልሽም መንግሥተ ሰማያት ወርሷል ምጽዋትም አይሻም"። አፎምያም እንዲህ ብላ መለሰችለት "እኔ ከሌላ ሰው ጋራ ላልገኛኝ ለእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አድርጌያለሁ ርግቦችና መንጢጦች እንኳ ሌላ ባል አያውቁም በእግዚአብሔር አርያ ከተፈጠሩ ሰዎች ይህ ሊሆን እንዴት ይገባል"። ምክሩንም ባልሰማች ጊዜ አርያውን ለውጦ በላይዋ ጮኸባት እንዲህም አላት እኔ በሌላ ጊዜ እመጣለሁ" እርሷም የከበረ የመላኩ የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ይዛ አሳደደችው።

ከዚህም በኋላ ሰኔ ዐሥራ ሁለት የከበረ የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል በዓል በሚከብርበት ዕለት እርሷም የበዓሉን ዝግጅት ስታዘጋጅ ሳለች ብርሃናዊ መልአክ መስሎ ሰይጣን መጣ "አፎምያ ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን እኔ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ነኝ ጌታ ወደ አንቺ ልኮኛልና እርሱም ይህን መመጽወትሽን ትተሽ ለአንድ ምዕመን ሚስት ትሆኚ ዘንድ ጌታ አዞሻል ባል የሌላት ሴት መልሕቅ የሌለውን መርከብ እንደምትመስል ዕወቂ እንደ አብርሃምና ያዕቆብ እንደ ዳዊትም እንደእነርሱ ያሉ ብዙ ሴቶችን እንዳገቡ እግዚአብሔርንም ደስ እንዳሰኙት" ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ጥቅሶችን ያመጣላት ጀመረ።

ቅድስት አፎምያም መልሳ "አንተ የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ የመስቀል ምልክት ከአንተ ጋራ ወዴት አለ የንጉሥ ጭፍራ የሆነ ሁሉ የንጉሡን ማሕተም ሳይዝ ወደ ሌላ ቦታ አይሔድምና" አለችው። ሰይጣንም ይህንን በሰማ ጊዜ መልኩ ተለውጠና አነቃት እርሷም ወደከበረው መልአክ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ጮኸች ወዲያውኑም ደርሶ አዳናት። ያንንም ሰይጣን ይዞ ይቀጣው ጀመረ ሰይጣኑም ጮኸ "ማረኝ ያለ ጊዜዬ አታጥፋኝ እግዚአብሔር እስከ ዓለም ፍጻሜ ታግሦናልና" እያለ ለመነው ከዚያም ተወውና አበረረው። የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልም እንዲህ አላት "ብፅዕት አፎምያ ሆይ ሒደሽ የቤትሽን ሥራ አዘጋጂ አንቺ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ትለዪአለሽና እነሆ እግዚአብሔርም ዐይን ያላየውን ጆሮም ያልሰማውን በሰው ልብም ያልታሰበውን አዘጋጅቶልሻል"። ይህንንም ብሎ ሰላምታ ሰጣት ወደ ሰማያትም ዐረገ።

የበዓሉንም ዝግጅት እንደሚገባ ከፈጸመች በኋላ ወደ ኤጲስቆጶሱና ወደ ካህናቱ ሁሉ ላከች ወርሷም በመጡ ጊዜ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ይሰጧቸው ዘንድ ገንዘቧን ሁሉ አስረከበቻቸው። ከዚህም በኋላ ተነሥታ ጸለየች የከበረ የመላአኩ የቅዱስ ሚካኤልንም ሥዕል አንስታ ታቅፋ ሳመችው ያን ጊዜም ሰኔ 12 ቀን በሰላም አረፈች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት አፎምያ በጸሎቷ ይማረን የዚህም የከበረ መልአክ የቅዱስ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችን የክርስቲያን ወገኖችን ይጠብቀን ለዘላለሙ አሜን።

+ + +
ቅዱስ እለእስክድሮስ የቅዱስ ሚካኤል በዓል እንዳከበረ፦ የሚከብሩበትም ምክንያት እንዲህ ነው። እስክንድርያ በምትባል ከተማ "አክሊወባጥራ" የተባለች የንግሥት የንጉሥ በጥሊሞስ ልጅ ዙሐል በሚባል ኮከብ ስም ያሠራችው ታላቅ ምኵራብ ነበርና በየዓመቱ ሰኔ በባተ በዐሥራ ሁለት ቀን በዚያ ምኵራብ ሕዝቡ ተስብስቦ ታላቅ በዓል ያደርጉ ነበር። በዚያም ምኵራብ ውስጥ ዙሐል የሚሉት ታላቅ የነሐስ ጣዖት ነበርና በዓሉ በሚከበርበት ዕለት ብዙ ፍሪዳዎችን ያርዱለት ነበር።

አባ እለእስክንድሮስም እስከተሾመበት ዘመን ድረስ ለዚያ ጣዖት እንዲህ ሲያደርጉ ኖሩ። ይኸውም ሦስት መቶ ዓመተ ምሕረት ተፈጽሞ በአራተኛው ምዕት ውስጥ ነበር። አባ እለእስክንድሮስ በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ጻድቅ ቈስጠንጢኖስም በነገሠ ጊዜ የክርስትና ሃይማኖት ስለ ተስፋፋች ያን ጣዖት ሊሠብረው ወድዶ ሳለ ጐስቋሎች ሰዎች ከለከሉት እንዲህም አሉት "እኛ በዚህ ቦታ ይህን በዓል ማክበርን ለምደናል እነሆ ከአንተ በፊት ዐሥራ ስምንት ሊቃነ ጳጳሳት አልፈዋል ይህን ልማዳችንንም አልለወጡብንም"።

አባ እለእስክንድሮስ ግን ገሠጻቸው አስተማራቸውም ስሕተታቸውንም በመግለጥ እንዲህ ብሎ አስተማራቸው "ይህ ጣዖት የማይጎዳና የማይጠቅም ነው እርሱንም የሚያመልክ ሰይጣናትን ያመልካቸዋል ምክሬንስ ብትሰሙ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ ይህን በዓል እሠራላችኋለሁ ይኸውም ጣዖቱን እንድንሰብረው ምኵራቡንም እንድንባርከውና በከበረ መልአክ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ስም ቤተ ክርስቲያን አድርገን እንድንሰይመው ነው እኛም ይህን ታላቅ በዓል እንሠራለን። የሚታረዱትም ላሞችና በጎች ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች፣ ለችግረ ኞችም በከበረው መልአክ ስም ምግብ ይሁኑ። እርሱ እግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነት ያለው ስለሆነ ስለእኛ ይማልዳልና" ይህንንም ብሎ በዚህ በጎ ምክር አስወደዳቸው እነርሱም ታዘዙለት።

ከዚህም በኋላ ያንን ምኵራብ አድሰው በዚህ የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ስም ቤተ ክርስቲያን አደረጉት በዚችም ዕለት ሰኔ12 አከበሩዋት። እርሷም የታወቀች ናት። እስላሞችም እስከ ነገሡበት ዘመን ኑራ ከዚያ በኋላ አፈረሱዋት። ይህም በዓል ተሠራ እስከ ዛሬም ጸንቶ ይኖራል። ምንጭ፦ የሰኔ 12 ስንክሳር።

+ + +
የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦"ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዓውዶሙ። ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ። ጠዐሙ ወታምእሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር"። መዝ 33፥7-8 ወይም መዝ 48፥10-11 ። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 24፥30-36 ወይም ማቴ 25፥14-31።

+ + +
የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ሠረገላቲሁ ለእግዚአብሔር ምዕልፊተ አዕላፍ ፍሡሐን። እግዚአብሔር ውስቴቶን በሲና መቅደሱ። ዐረገ ውስተ አርያም ጼዊወከ ፄዋ"። መዝ 67፥11-18። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 3፥14-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 3፥15-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 1፥6-12። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 22፥31-37። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ሚካኤል በዓል፣ የጻድቁ ንጉሥ የቅዱስ ላሊበላ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
86 viewsBereket Damene, 18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 21:07:49 ከዚህም በኋላ ያ ባለጸጋ ምክንያት አዘጋጅቶ "የሚያገለግለኝ ልጅ ይሆነኝ ዘንድ ልጅሽን ስጪኝ እኔም እየመገብኩና እያለበስኩ አሳድገዋለሁ ለአንቺም ሃያ ወቄት ወርቅ እሰጥሻለሁ" አላት። ይህንንም ነገር ከበለጸጋው በሰማች ጊዜ ስለችግራ እጅግ ደስ አላት ልጅዋንም ሰጠችው እርሱም ሃያውን ወቄት ወርቅ ሰጣት ልጅዋንም ወሰደው የምሻው ተፈጸመልኝ ብሎ ደስ አለው።

ከዚህም በኋላ በልጁ ቁመት ልክ ሣጥን አሠርቶ ሕፃኑን በሳጥኑ ውስጥ አስገብቶ ዘጋበት እስከ ባሕርም ተሸክመው ወስደው በባሕር ጣሉት ክብር ይግባውና በጌታችን ፈቃድ ያ ሣጥን ሳይሠጥም ከዚያች አገር የሃያ ቀን መንገድ ያህል ርቃ ወደምትገኝ ወደ አንዲት አገር ወደብ እስከ ሚደርስ ባሕሩ ላይ ተንሳፈፈ። በባሕሩም አካባቢ በጎቹን አሰማርቶ የሚጠብቅ አንድ ሰው ነበርና ሣጥኑን በውኃ ላይ ተንሳፎ አየው እርሱም ከባሕሩ አውጥቶ ወደ ቤቱ ወሰደው ይህንም ሣጥን እንዴት እንደሚከፍተው ያስብ ጀመረ ይህንም ሲያስብ ወደ ባሕሩ ይሔድ ዘንድ ጌታችን በልቡናው ኃሳብ አሳደረበት ወዲያውኑም ተነሥቶ ወደ ባሕሩ ሔደና አንድ ዓሣ የሚያጠምድ ሰው አገኘ። ዓሣ አጥማጁንም "መረብህን በኔ ስም ጣል ለሚያዘውም ዓሣ ዋጋውን እሰጥሃለሁ" አለው። አጥማጁም እንዳለው አደረገ ያን ጊዜም ታላቅ ዓሣ ተያዘ ዋጋውንም ሰጥቶ ዓሣውን ተቀበለ ዓሣውንም ይዞ ወደቤቱ ሔደ ለራትም ይጠብሰው ዘንድ አረደው በሆዱም ውስጥ መክፈቻ አገኘ። በልቡም ይህ መክፈቻ ይህን ሣጥን ይከፍተው ይሆን" አለ በሣጥኑ ቀዳዳም በአስገባው ጊዜ ፈጥኖ ተከፈተ በውስጡም ይህን ታናሽ ብላቴና አገኘ። ልጅ የለውም ነበርና ታላቅ ደስታም ደስ አለው ጌታችንንም አመሰገነው። ሕፃኑንም በመልካም አስተዳደግ አሳደገው ሕፃኑንም አድጎ ጐልማሳ ሆነ።

ከብዙ ዘመናትም በኋላ ያ ባለ ጸጋ ተነሥቶ ወደ ዚያ አገር ሔደ በመሸም ጊዜ ወደ በግ ጠባቂው ደጅ ደረሰ በግጠባቂውን "እስከ ነገ የምናድርበት ማደሪያ በአንተ ዘንድ እናገኛለን? ኪራዩንም እሰጥሃለሁ" አለው በግ አርቢውም "እንዳልክ ይሁንና እደር" አለው ባለጸጋውም በዚያ አደረ። ራት በሚቀርብም ጊዜ ሕፃኑን ባሕራን ብሎ ጠራው ባለጸጋውም ሰምቶ "ልጅህ ነውን?" ብሎ ጠየቀው በግ ጠባቂውም "አዎን ታናሽ ሕፃን ሆኖ ሳለ ከባሕር አግኝቼዋለሁና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጄ ነው" አለው ባለጸጋውም "በምን ዘመን አገኘኸው" አለው እርሱም "ከሃያ ዓመት በፊት" ብሎ መለሰለት። ያን ጊዜም እርሱ ወደ ባሕር የጣለው መሆኑን አውቆ አጅግ አዘነ።

በማግሥቱም ጎዳናውን ሊጓዝ በተነሣ ጊዜ ሰይጣናዊ ምክንያት አመካኝቶ በግ ጠባቂውን እንዲህ አለው "ዕገሊት ወደምትባል አገር በቤቴ የረሳሁት ጉዳይ ስለ አለ እንድልከው ልጅህን ትሰጠኝ ዘንድ እሻለሁ እኔም የድካም ወጋውን ሃያ ወቄት ወርቅ እሰጥሃለሁ" አለው። የብላቴናውም አባት ስለገንዘቡ ደስ ብሎት ልጁ ባሕራንን ሰጠው እንዲህም ብሎ አዘዘው "ልጄ ባሕራን ይህ የከበረ ሰው ስለ ጉዳዩ ወደ ቤቱ ይልክህ ዘንድ ና ወደ ቤትህም በሰላም ትመለሳለህ"። ባሕራንም "አባቴ ሆይ እሽ በጎ ያዘዝከኝ ሁሉ አደርጋለሁ" አለ።

ያን ጊዜም ባለጸጋው ወደ መጋቢው እንዲህ ብሎ ደብዳቤ ጻፈ "ይችን ደብዳቤ በምታነባት ጊዜ ደብዳቤዋን ይዞ የመጣውን ገድለህ በጒድጓድ ውስጥ ጣለው ማንም አይወቅ" በመካከላቸውም የሚተዋወቁበትን ምልክት ጽፎ አሸጋት። ለባሕራንም ሰጠው ለመንገዱም የሚሆነውን ስንቅ ሰጠው ባሕራንም ተነሥቶ ጉዞውን ጀመረ ሲጓዝም ሰንብቶ የአንዲት ቀን ጉዞ ሲቀረው እንሆ የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ "አንተ ጐልማሳ የያዝኸው ምንድነው?" አለው "ወደ ዕገሌ አገር ወደ ቤቱ ለማድረስ ከአንድ ባለጸጋ የተጻፈች መልክት ናት" አለው "ያቺን ደብዳቤ አሳየኝ" አለው እርሱም ስለ ፈራ ሰጠው።

በዚያን ጊዜም የከበረው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ያቺን የሞት መልክት ደመሰሳት በእርሷ ፈንታም በንፍሐት ለውጦ እንዲህ ብሎ ጻፈ "ይቺን ደብዳቤ ይዞ ለመጣ ባሕራን ለሚባል ሰው ይቺ ደብዳቤ ደርሳ በምትነበብበት ጊዜ ልጄ ዕገሊትን አጋቡት በውስጥና በውጭ ያለ ንብረቴንና ጥሪቴን ወንዶችና ሴትች ባሮቼን ጠቅላላ ንብረቴንም አውርሼዋለሁና የፈለገውንም ሊያደርግ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁና እኔን አትጠብቁኝ። እኔ ብዙ እዘገያለሁ የኔ ሹም ዕገሌ ሆይ በእኔና በአንተ መካከል ይቺ ምልክት እነኋት" ከዚህ በኋላ አሽጐ ለባሕራን ሰጠውና "ወደ ባለጸጋው ቤት ሒደህ ይቺን ደብዳቤ ለሹሙ ስጠው በጎዳናም እኔ እንደ ተገናኘሁህ አትንገረው እንዳይገድልህም ይህን የሞት ደብዳቤ ለውጨልሃለሁ" አለው። ባሕራንም እሺ ጌታዬ ያዘዜኸኝን ሁሉ አደርጋለሁ" አለ።

ባሕራንም ወደ ባለጸጋው ቤት በደረሰ ጊዜ ያቺን ደብዳቤ ለሹሙ ሰጠው በአነበባትም ጊዜ በመካከላቸው ያለውን ምልክት አገኘ አስተውሎም እርግጠኛ እንደሆነ አወቀ። ከዚህም በኋላ ለባሕራን ሠርግ አዘጋጅቶ እንደሚገባ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በተክሊል የባለጸጋውን ልጁ አጋቡት። አርባ ቀን ያህልም ደስታና ሐሴት እያደረጉ ኖሩ።

ከዚህ በኋላ ባለጸጋው ከሔደበት መመለሻው ጊዜ ሁኖ በደስታ የሆነውን የመሰንቆና የእንዚራ ድምጽ ሰምቶ "ይህ የምሰማው ምንድነው?" ብሎ ጠየቀ እነርሱም "ስሙ ባሕራን ለተባለ የአንተን ደብዳቤ ላመጣ ጐልማሳ ሰው ልጅህ ዕገሊትን አጋቡት እንሆ ለአርባ ቀናት በሠርግ ላይ ነው። ገንዘብህንና ጥሪትህን ሁሉ ወንዶችና ሴቶች ባሮችህን አንተ እንዳዘዝክ ሰጥተውታል" አሉት። ይህንንም በሰማ ጊዜ ደንግጦ ከፈረሱ ላይ ወድቆ በድንገትም ሞተ።

ባሕራንም በጎ ሥራዎችን የሚሠራ ሆነ የተገለጸለትና ከመገደል ያዳነው የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ሊገድለው የሚሻውን የባለጸጋውን ጥሪቱን ሁሉ ያወረሰውም እርሱ እንደ ሆነ ተረዳ የዚህንም የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ በየወሩ ያደርግ ጀመረ ቤተ ክርስቲያንም ሠራለት የቅዱስ ሚካኤልንም ሥዕሉን አሥሎ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ አደረገው ከእርሱም ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ ባሕራንም ቅስና ተሹሞ እስከ ዕለተ ሞቱ በዚያች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል ሁኖ ኖረ በዚህ በከበረ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ከእናቱና ከአባቱ ከልጆቹም ጋራ የዘላለም ሕይወትን ወረሰ።

+ + +
ቅዱስ አስተራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አፎምያ፦ ይህም ሰው በየወሩ ሦስት በዓላቶችን እያከበረ ኖረ እሊህም ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ መታሰቢያ በየወሩ በሃያ ዘጠኝ፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓል መታሰቢያ በየወሩ በሃያ አንድ የከበረ የመላእክት አለቃ የሆነ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል መታሰቢያም በየወሩ በዐሥራ ሁለት ናቸው።

የሚሞትበትም ጊዜው ሲቀርብ እርሱ ሲሠራው የነበረውን ምጽዋት ይልቁንም እሊህን ሦስቱን በዓላት እንዳታስታጉል ሚስቱን ቅድስት አፎምያን አዘዛት። እርሷም የከበረ የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባሏን ለመነችው እርሱም አሠርቶ ሰጣትና በቤቷ ውስጥ በክብር አኖረችው።
82 viewsBereket Damene, 18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 21:07:35 "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

ሰኔ ፲፪ (12) ቀን።

እንኳን ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ለሚበር ንሥረ አርያም ለሚባል ውዳሴው እንደ ማር ለጣፈጠ ንዑድ ክቡር ለሆነ ለከበረ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር ለተሾመበት፣ የባሕራንን የሞት ደብዳቤ ቀዶ እርሱን ለታላቅ ክብር ላበቃባት ቅድስት አፎምያን ለአዳነበት (ለረዳበት)፣ ቅዱስ እለእስክንድሮስ አንድን ቤተ ጣዖት አፍርሶ ከቦታው ላይ ቤተ ክርስቲያን ሠርቶ ታቦተ ቅዱስ ሚካኤልን አግብቶ በዓሉን በደስታ በሐሴት ላከበሩበት ዕለት በዓል፣ ለቅዱስ አስተራኒቆስ ለሚስቱ ቅድስት አፎምያ ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል፣ ለእስክንድርያ ስድስተኛ ሊቀ ጳጳሳት ለአባ ዮስጦስና ለስልሳ ሰባተኛ ሊቀ ጳጳሳት ለአባ ቄርሎስ ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

+ + +
የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፭ "ወረደ እግዚእነ ውስተ ሲኦል ወይቤሎሙ ለእለ ውስተ ደይን በእንቲአክሙ ተሰቀልኩ ዲበ ዕፅ ወተረግዘ ገቦየ በኵናት አንትሙኒ በዝኒ ኢነሣሕክሙ በእንቲአክሙ ተቀነዋ እደውየ ወእገርየ ወተጸፍዓ መልታሕቴየ፤ አዝ፣ በእንቲአክሙ አስተዩኒ ብሂዓ ከርቤ ቱስሐ ዘምስለ ሐሞት በቅድመ ጲላጦስ ወሊቃነ ካህናት፤ አዝ፣ ናሁ ወሀብኩክሙ ሰንበተ ክርስቲያን ዕረፍተ ትኩንክሙ በእንተ ሚካኤል መልአክ ምክርየ ወጳውሎስ ፍቁርየ ወኵሎሙ ቅዱሳንየ አእኰትዎ ኵሎሙ እለ ውስተ ደይን ወዘንተ ብሂሎ ዐርገ ኢየሱስ ሰማያተ አብሖሙ አሁሆሙ ሀገረ ቅድስት ኢየሩሳሌም አግዓዚት"። ትርጉም፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሲዖል ወረደ በሲዖል ውስጥ ላሉት ነፍሳት ስለእናንተ በእንጨት ላይ ተሰቀልኩ፤ ጎኔን በጦር ተወጋ፤ እናንተን በዚህ አልተመለሳችሁም፤ ስለእናንተ እጆቼና እግሮቼ ተቸነከሩ፤ ጉንጮቹ በጥፊ ተመቱ፤ ስለእናንተ በካህናትና በጲላጦስ ፊት ሐሞትና ከርቤ የተቀላቀለበትን መፃፃ ጠጣሁ፤ የምክሬ ባለሟል ስለሆነው ስለ ቅዱስ ሚካኤል ስለወዳጄ ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ስለቅዱሳኖቼ እነሆ ዕረፍት ትሆናችሁ ዘንድ ሰንበተ ክርስቲያንን ሰጠኋችሁ። በሲዖል ውስጥ ላሉት ነፍሳት ሁላቸውም አመሰገኑት ነጻ በምታወጣ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም አባታቸው ሥልጣን ሰጣቸው ኢየሱስ ይህን ብሎ ወደ ሰማይ ዐረገ።

+ + +
የዕለቱ አንገርጋሪ፦ "አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ ፀሓይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ ወሪዶ እመስቀሉ አብርሃ ለኵሉ"። ትርጉም፦ ጌታችንን አይሁድ በሰቀሉት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ዝም አለ፤ ቅዱስ ገብርኤልም ተደነቀ፤ ፀሓይ ጨለመ ፤ ጨረቃም ደም ኾነ፤ ከመስቀሉ ወርዶ ለኹሉ አበራ።

+ + +
"ክብረ ሚካኤል ናሁ ተዐውቀ በትሕትናሁ ዐብየ ወልሕቀ ዲበ አእላፍ ዘተሰምየ ሊቀ ዘይትዐፀፍ መብረቀ ይተነብል ጽድቀ"። ትርጉም፦ የሚካኤል ክብረ እነሆ አኹን ታወቀ፤ በትሕናውም ፈጽሞ ላቀ ከፍ ከፍ አለ፤ በአእላፍ ነገደ መላእክት ላይ አለቃን የተባለ መብረቅን የሚጐናፀፍ ርሱ ጽድቅን ይለምናል። ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።

+ + +
በዚች ዕለት እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን በነገዱ ውስጥ በላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር ሾመው። ይህም የከበረ መልአክ ክብር ይግባውና በጌታችን ፊት ስለ ሰው ልጆችና ስለ ፍጥረቱም ሁሉ ይለምናል ይማልዳል።

መድኃኒታችን በተነሣባትም ቀን ይህ ክብር መልአክ ሚካኤል ከውስጠኛው መጋረጃ ውስጥ ገብቶ በክብር ባለቤት ፊት እንዲህ እያለ ይለምናል "እውነት ስለሆነ ቃል ኪዳንህ በምድር መታሰቢያዬን የሚያደርገውን ትምርልኝ ዘንድ ፈጣሪዬ ሆይ እኔ አገልጋይህና መልአክተኛህ ከቸርነትህ እለምናለሁ አንተ መሐሪና ይቅር ባይ ነህና"። የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ ብሎ ይመልስለታል "የመንፈሳውያን ሰማያውያን መላእክት አለቃቸው ሚካኤል ሆይ መታሰቢያህን የሚያደርገውን ሁሉ መሸከም እንደሚችል ከሲዖል ሦስት ጊዜ በክንፈሸችህ ተሸክመህ እንድታወጣ እንሆ እኔ አዝዤሃለሁ"። ይህንንም ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ብሎት የበዓሉን መታሰቢያ ከሚያደርጉት በክንፎቹ ተሸክሞ የእሳትን ባሕር አሳልፋቸው እነርሱንም ከብቻው ጌታ በቀር የሚቆጥራቸው የለም።

ስለዚህም የዚህን ታላቅ የከበረ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ለማድረግ መታገል ይገባናል እርሱ ከሰይጣን ወጥመድ ያድነን ዘንድ በዘመናችን ሁሉም ይጠብቀን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይ ዘንድ መከራችንንም ያርቅ ዘንድ የምድራችንንም ፍሬ ይባክ ዘንድ ከእኛ ወገን የሞቱትን ዕረፍተ ነፍስ ይሰጥ ዘንድ ወደ መንገድ የሔዱ አባቶቻችንና ወንድሞቻችንን ወደ ቤቶቻቸው በሰላም በጤና ይመልሳቸው ዘንድ በመካከላችንም ፍቅር ያደርግልን ዘንድ እስከ መጨረሻዪቱም ሕቅታ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ ይለምናልና።

የክርስቶስ ወገኖች የሆኑ መኳንንቶቻችንንም ጠብቆ በወንበሮቻቸው ላይ ያጸናቸው ዘንድ የሳቱትንም ወደ ቀናች ሃይማኖቱ ይመልሳቸው ዘንድ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚካኤል አማላችነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ12 ስንክሳር።

+ + +
ቅዱስ ሚካኤል ባሕራንን እንደረዳው፦ እግዚአብሔር የሚፈራ አንድ ሰው ነበር እርሱም የከበረ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉን መታሰቢያ በየወሩ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ይልቁንም በሰኔና በኅዳር ወር አብልጦ ያከብር ነበር። በጐረቤቱም ርኅራኄ የሌለው አንድ ባለጠጋ ሰው ነበረ። ይህም እግዚአብሔርን የሚፈራውን ሰው የከበረ መልአክ የቅዱስ የሚካኤልን በዓል በሚያደርግበት ጊዜ ይጠላውና ያቃልለው ነበር ለድኆች ስለ መራራቱም ይዘባበትበት ነበር። የሕይወቱ ዘመንም ተፈጽሞ የሚሞትበትና ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ድካምም የሚያርፍበት ጊዜ ሲቀርብ የክብር መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ታደርግ ዘንድ ምጽዋት ሰጭም ትሆን ዘንድ ሚስቱን አዘዛተሰ።

ከዚህም በኋላ ዐረፈና ገንዘው ቀበሩት ሚስቱም ፀንሳ ነበረች የመውለጃዋ ጊዜም ደርሶ ምጥ ያዛት በታላቅ ጭንቀት ውስጥ ሳለችም እንዲህ ብላ ጸለየች "የእግዚአብሔር መልአኩ ሆይ ራራልኝ በእርሱ ዘንድ ባለሟልነት አለህና በእግዚአብሔር ዘንድ ስለ እኔ ለምንልኝ"። ይንንም በአለች ጊዜ በቤቷ ውስጥ ብርሃን በራ ከችግርም ዳነች መልኩ ውብ የሆነ ወንድ ልጅንም ወለደች የእግዚአብሔርም መልእክተኛ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወርዶ ሕፃኑን እንዲህ ብሎ ባረከው "ርኅራኄ የሌለውን የዚህን ባለጸጋ ገንዘብና ሀብት ጥሪቱንም ሁሉ ይህ ሕፃን እንዲወርስ እግዚአብሔር አዝዟል" ባለጸጋውም በቤቱ በዐልጋው ላይ ሳለ ጌታ ጆሮውን ከፍቶለት ይህን ነገር ከመልአኩ ሰማ። ይህንንም በሰማ ጊዜ ታላቅ ኀዘን ደረሰበት ሕፃኑንም የሚገድልበትን ምክንያት ይፈልግ ጀመር ነገር ግን ክብር ይግባውና ጌታ ይጠብቀው ነበር።
112 viewsBereket Damene, 18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ