Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ከመላእክት ጋር የሚዘምር ማሕሌታዊ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሚያጥን ካህን የምታፈራ ሀገር ና | ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ኢትዮጵያ ከመላእክት ጋር የሚዘምር ማሕሌታዊ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሚያጥን ካህን የምታፈራ ሀገር ናት። ለሰማይ አገልጋዮችን ገና ሳይሞቱ የምትልክ፣ ከተዋጊዎች መካከል ወደ ድል ነሺዎች መልእክተኛ የምትልክ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ያለች ናት?

ቅዱስ ያሬድ በትሕትናው ከትል ተማረ። ትሑታንን ከፍ የሚያደርግ ፈጣሪም ከፍ አደረገውና ከመላእክት ጋር ዘመረ። ትልዋን ከዛፍ አውርዶ ቢጨፈልቃት ኖሮ ለአንድ ሺህ አምስት መቶ ዓመታት ያልነጠፈው የምስጋና ጅረት በሀገራችን ባልፈሰሰ ነበር። ኃይል አለኝ ብለህ የምትጨፈልቃቸው ትሎች ሰማይ የሚያደርሱህ መምህራኖችህ እንዳይሆኑ ተጠንቀቅ ይላል የታሪኩ ተግሣፅ።

ቅዱስ ያሬድ እግሩን በጦር እየተወጋ እንኩዋን ዝማሬው ሰማያት ወስዶት አልተሰማውም ነበር። የእኛው ሲላስ የእኛው ጳውሎስ ቅዱስ ያሬድ ሆይ በዘመርክባት ሀገርህ ዛሬ ብዙ ጦር ተሰክቶባታል። ከአንተ ዜማ በቀር ዛሬም መጽናኛ የለንምና በምልጃህ አስበን።

ጥዑመ ልሳን ያሬድ: ሊቀ ጠበብት ያሬድ: ሊቀ ሊቃውንት ያሬድ የቤተ ክርስቲያን ጌጥ!!

(Deacon Henok Haile)