Get Mystery Box with random crypto!

ሲቲ የ24 ዓመት ታሪክ ተጋርቷል ማንቺስተር ሲቲ በሻምፒየንስ ሊጉ ፍጻሜ ኢንተር ሚላንን አንድ ለ | 16.09.2018

ሲቲ የ24 ዓመት ታሪክ ተጋርቷል

ማንቺስተር ሲቲ በሻምፒየንስ ሊጉ ፍጻሜ ኢንተር ሚላንን አንድ ለዜሮ በመርታት በውድድር ዘመኑ የሶስትዮሽ ክብርን በማሳካት ማጠናቀቁን ተከትሎ የከተማ ተቀናቃኙ ለ24 አመታት በእንግሊዝ የሶስትዮሽ ዋንጫን በማሳካት ብቸኛው ክለብ ሆኖ የቆየበትን ታሪክ መጋራት ችሏል።

የማንቺስተር ዩናይትድ እና ማንቺስተር ሲቲ የሶስትዮሽ ክብር ውድድር ዘመን ሲነጻጸር

ዩናይትድ የሶስትዮሽ ዋንጫን ባሳካበት የውድድር ዘመን ሽንፈት ያስተናገደው ሶስት ጊዜ ብቻ ነው። በሁሉም ውድድሮች ካደረጋቸው 57 ጨዋታዎች ግን በሚያስገርም መልኩ በ21 አቻ ተለያይቷል።

የሊግ ካፕ ውድድርን ሳያካትት የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን 42 ጨዋታዎችን ሲያሸንፍ 73.7 % የማሸነፍ መቶኛ አለው ።

ዩናይትድ በበኩሉ 33 ሲያሸንፍ 57.9% የማሸነፍ ንጻሬ አለው።

ሲቲ 145 እና ዩናይትድ 121 ጎሎችን ተጋጣሚዎቻቸው መረብ ላይ ሲያሳርፉ ሲቲ በ26 እና ዩናይትድ በ21 ጨዋታዎች መረባቸውን ሳያስደፍሩ ወጥተዋል።

ሲቲ 39 ዩናይትድ ደግሞ 56 ጎሎችን ሲያስተናግዱ ሲቲ በጨዋታ 2.54 ጎሎችን በአማካይ በጨዋታ ሲያስቆጥር  0.68 ደግሞ ጎል በጨዋታ አስተናግዷል።

ዩናይትድ በአንጻሩ 2.12 በአማካይ በጨዋታ ሲያስቆጥር 0.98 ጎል ደግሞ በጨዋታ በአማካይ ጎል  አስተናግዷል።

ሲቲ በጨዋታ አራት እና ከዚያ በላይ ጎል በ16 ጨዋታዎች ላይ ተጋጣሚው መረብ ላይ ሲያሳርፍ  ካደረጋቸው ጨዋታዎች አንጻር ደግሞ 28.1% ይሸፍናል።

በዚህ በኩል ከከተማ ተቀናቃኙም በእጥፍ የሚበልጥ ቁጥር አለው።

አርሊንግ ሀላንድ በውድድር ዘመኑ 51 ጎሎችን በማስቆጠር ለሲቲ የሶስትዮሽ ዋንጫ ክብር ትልቁን ድርሻ ይወስዳል።

በዩናይትድ በኩል በዚህ ደረጃ የጎል ሸክሙን በወቅቱ የወሰደ ተጫዋች አልነበረም።

ድዋይት ዮርክ 29 እና አንዲ ኮል 24 በሁሉም ውድድሮች ለዩናይትድ በማስቆጠር ከፊት የተቀመጡ ተጫዋቾች ነበሩ።

አስደናቂው ኦሊጉናር ሶልሻየር በሊጉ በዘጠኝ ጨዋታዎች ብቻ በቋሚነት  ጀምሮ ዘጠኝ ጎሎችን ሲያስቆጥር  በሁሉም ውድድሮች ደግሞ በአስራ አምስቱ በቋሚነት  ጀምሯል።

በሀያው ደግሞ ከተጠባባቂ ወንበር ተነስቶ ጀምሯል።

በፍጻሜው የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ከሼሪንግሀም ጋር በመሆን የሰራው ገድል የማይዘነጋ ነው።

ፖል ስኮልስ እና ሪያን ጊግስ ባለ ሁለት አሀዝ ጎሎችን ከመረብ ማገናኘት የቻሉ ተጫዋቾች ናቸው።


Website : www.hattricksportofficial.com

Website : www.bestsportet.com

Facebook : facebook.com/hattricksportofficial

Facebook : facebook.com/bestsportet

Telegram : t.me/bestsportet

Twitter : twitter.com/bestsportet

#ሀትሪክ_ስፖርት_ኦፊሺያል
ስፖርትን እንመግባለን !!
We Feed Sport...