Get Mystery Box with random crypto!

አይ ሰው መሆን ተሰርቶ መፍረስ! አያቴ፡ ትልቁ ሰው! የተከበረው ዳኛ፤ ጡረተኛ። መኝታ ቤቱ ፍርድ | All Slots Free Spins How To Play Roulette Game Casino Free Slots Games Bet 25

አይ ሰው መሆን ተሰርቶ መፍረስ!

አያቴ፡ ትልቁ ሰው! የተከበረው ዳኛ፤ ጡረተኛ። መኝታ ቤቱ ፍርድቤቱ
የሚመስለው፣ በቀን ሰባት፣ ስምንት ጊዜ እንቅልፉ የሚወስደው በነቃ ቁጥር .. የነጋ እየመሰለው ፡ “ቁርሴን አልሰጠሽኝም” ብሎ፥ ከእኔ ጋር የሚጨቃጨቀው።
ቁርሱን ስሰጠው፥ በእጁ መንቀጥቀጥ ጉርሻው ግንባሩንና ጉንጮቼን ካልተሳለመ
አፉን ፈልጎ ማግኘት የሚከብደው።

እንድ ሰው! ወይ አንድ ሰው! የነበረውና አሁን የሆነው የማይገጥም። እድሜ ልኩን
ሁሉ በአፉ ሲያወራና ሲፈርድ የነበረ ሰው፥ እዚያው ፊቱ ላይ ያለ እና የነበረ አፋን
ፈልጎ ማግኘት ሲያዳግተው አይገርምም?

አይ ሰው መሆን ተሰርቶ መፍረስ:
ሰውነት ተረትነት። እየተሰራ የሚፈርስ ቤት።

ወደ ሞቱ እየሄደ “እየኖርኩ ነው!” የሚል ቂል። ማንነቱ ግልፅ ሆኖ የማይታየው ልበ-ዕውር። “ነህ” ሲሉት ነኝ!” ብሎ፤ አይደለህም ሲሉት “እ..ነው እንዴ?” የሚል ጅል። “ለምን?”ን የማያውቅ - ሰው።



አለማወቅ