Get Mystery Box with random crypto!

ቤርያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ beryya — ቤርያ
የቴሌግራም ቻናል አርማ beryya — ቤርያ
የሰርጥ አድራሻ: @beryya
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 214
የሰርጥ መግለጫ

" ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤"
(ወደ ቲቶ 2:11)

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-15 17:51:57 ብዙ ነገስታት በራሳቸው አለም ነው የኖሩት ሲሞቱ ግን ቤተ ክርስቲያን ነው የሚቀበሩት ።ብዙ ዝነኞች አለምን ዞረው ሲጨርሱ የሚመጡት ወደ መቃብር ነው ።
መጨረሻችን እርሱ ከሆነ ለምን መጀመሪያችን እርሱ አልሆነም።የመጨረሻው ድል ያገኘ ማነው ቢባል በክርስቶስ ያመነ ነው ።
1.9K views14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 18:16:26 የፋሲካው በግ

ፈሲካ ማለት በእብራይስጥ ቋንቋ ማለፍ ፣መሻገር፣መዳን ማለት ነው።የሚያልፉት ከበሽታ፣ከድህነት አይደለም ከሞት ነው። ሞት በእስራኤል ልጆች ደጃፍ ደሙን አይቶ ባለፈ ጊዜ ቀኑ ፈሲካ ተባለ፣ ሞት በደጄ አለፈ ማለት ነው።የሚያሳልፈው አለፈ ማለት ነው።በግብጽ ሀገር ሆነው የእስራኤል ልጆች ለመጀመሪያ ጊዜ ያከበሩት የፈሲካን በአል ነው።ባሉበት የጨለማ መንግስት ውስጥ ሆነው መዳናቸው ታወጀላቸው።እዚያው በደስታ አክብረው በደስታ ወጡ።ቤተ መንግስትን የደፈረ ያ መቅሰፍት ግን የባሪያዎቹን ፣የድሆቹን፣ የእስራኤልን ደጃፍ መድፈር አልቻለም፤ በእስራኤል ማንነት የተነሳ ሳይሆን በደሙ ሀይል የተነሳ ነው ።የሞት በረኛው የክርስቶስ በር ነው። እግዚአብሔር ብርቱ ነን የሚሉትን በተናቀ ነገር ይጥላቸዋል።ዘጸ 12–12።
"ብርና ወርቅ ትበዘብዛላችሁ" አላቸው። በግብፅ ሀገር ላይ እንደ ሙሴ የከበረ ሰው አልነበረም።የመሴ ክብር እግዚአብሔር በሙሴ ላይ በመስራቱ ነው።ጌታ ከእናንተ ጋር ከሰራ ማንም አይነካችሁም። እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር ሲያወጣ የሰራተኝነታቸውን ደሞዝ አስከፍሎ ነው። አንዱ አስራኤልን ፈርኦንም እግዜር ይገባናል እያሉ ነው። የተፈጠረው የሚገዛ ነው ፈርኦን፣ እግዚአብሔር ግን ፈጥሮ የሚገዛ ነው።
በዚህ ክፍል ላይ ይሰዳቹሃል አለ እግዚአብሔር።ይሄ መሰደድ ምንድን ነው ? አንዱ አባት ለአካለ መጠን የደረሰች ልጅ ለታጨችለት ሚስት ትሆነው ዘንድ ብርና ወርቅ አስታጥቆ እንደሚሰዳት፣ እስራኤልም ለእውነተኛ ገዢዋና አሳዳሪዋ ብርና ወርቅ ሰጥቶ እንደሚሰዳት መሆኗን እግዚአብሔር ተናገረ።ስለዚህ የፈሲካ በአል እስራኤል የሙሽሪት ቀኗ ነው።ከግብጽ ምድር ሲወጡ ብርና ወርቃቸውም ወጣ፤ ብርና ወርቃቸው ለእግዚአብሔር አዋሉት።


የእስራኤል ልጆች ከሞት የዳኑት በፋሲካው በግ ነው።የፋሲካው በግ እግዚአብሔር ለህዝቡ ያዘጋጀው መፍትሔ ነው።ከእግዚአብሔር ቁጣ የምናመልጠው በምን ውስጥ ነው ስንል በራሱ በእግዚአብሔር ውስጥ ነው። በዘመናት ሁሉ እግዜር ለልጆቹ የማዳን አማራጭ አለው።ሰው ከእግዚአብሔር ቁጣ በራሱ ዘዴ መዳን አይችልም። ከእግዚአብሔር ቁጣ የምናመልጠው በራሱ በእግዚአብሔር ነው።ስለዚህ የፋሲካው በግ የእግዚአብሔር መፍትሔ ነበር።ከግብፅ ሀገር፣ከፈርዖን እጅ ለመዳን እግዚአብሔር ያደረገው የመጀመሪያ የመጨረሽያ መፍትሔ ነው ።የፋሲካው በግ አልተደገመም። የፋሲካው በግ አንድ ጊዜ የተከናወነ ነው ።ከፋሲካው በግ በኋላ የእስራኤል ልጆች በብዙ ውድቀትና በብዙ ምርኮ አልፈዋል ።አንዱ መስዋዕት በተለያየ ረድኤት ይገለጥ ነበር።የፋሲካው በግ ክርስቶስ አንድ ጊዜ ተሰውቷል።እኛ በደከምን ጊዜ ፣በዛልን ቁጥር ደጋግሞ መሞት አያስፈልገውም፤አንዱ መስዋዕት ግን ለገባንበት ነገር ሁሉ፣ለወደቅንበት ነገር ሁሉ እንደ ገና መፍትሔ ነው።ዕብ 9–28 :–"ክርስቶስ ደግሞ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁ ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል። ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት እንከን የለሽ ሆኖ ይታይላቸዋል።
ይቀጥላል
……………………………………………
2.4K views15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 22:59:15
"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል ። ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና ። ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና" 1ቆሮ 15: 20-22

❀ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ ❀
2.3K views19:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 14:47:37
ስለ ሁሉ ሞተ

ስለ ሁሉ ሞተ ሲሉን ይህም ቀላል እንዳይመስለን
አንድ ልጁን ሰጠ ሲሉን ይህም ቀላል እንዳይመስለን
ትጥቅ ያስፈታል ያሸንፋል ያቆየልን ብድራቱ

ጀርባውን ተመልከቱ እስራቱን ሕማሙን
እኛን አዝሎ ተሸክሞ የቆሰለ መሆኑን
መዳፎቹን ተመልከቱ የችንካሩን ምልክት
ይናገራል እስከ ትውልድ ያንን ፍቅር ምህረት

የእግ/ር ክንድ መገለጡ ማን አመነ ከትውል
ዮሐንስን ስሙትና ልባችሁን አሰናዱ
ይሙት ብለው ሲፈርዱበት እዳችንን ተሸከመ
ሳምራዊውን ተመልከቱ ቁስሎቹን እያከመ

የጠፋው ልጁ ኢየሱስ መጥቶ መጣ ከአባቱ
ሁሉን ሰጥቷል ምስክርን ነው መስቀሉ ላይ መራቆቱ
ጠማኝ አለ ድሀ ሆነ ባለጠጋ ሊያደርገን
ሰበሰበን ምርኮ አድርጎ ወደ ክብር መለሰን


በዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም
በዝምታ የንስሀ መዝሙር
1.8K views11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-10 07:55:54
1.4K views04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-19 16:59:22 የመስቀሉ ጩኸቶች
ክፍል አራት
ሰዎች የሞት አዋጅ ተፈርዶባቸው የመጨረሻ ዕድል ይሰጣቸዋል ፤ጌታ ኢየሱስ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት ዕድል ተሰጦት የተናገረው አይደለም በሞትና በርሱ መካከል ሳልሞት ልንገራቸው ብሎ የነገረን የምስራች ድምጽ ነው።ህመሙን ወደ እርሱ ደስታና የምስራቹን ወደ እኛ አድርጎ የተነገረበት ቃል ነው። በዚህ አለም ላይ የተደነቁ ፍቅሮች አሉ አንዱ ፍቅር እስከ መቃብር ሲሆን ከሞት ባሻገር አንድ ፍቅር አለ እስከ ሞት የወደደን ዛሬም የሚወደን ጌታ ኢየሱስ ነው።
ራሳችን ይቅር ማለት ሲያቅተን ራሳችን ይቅር ማለት ባለመቻላችን ልናዝን አይገባም ምክንያቱም አንዱ በዳይ አንዱ ይቅርታ ሰጪ መሆን አይችልም።ይቅርታ፣ምህረት ከስልጣን ውስጥ ነው የሚወጣው ስለዚህ ለአጢአታችን ይቅርታ በምንፈልግበት ጊዜ ስልጣን ካለው አካል መምጣት አለበት። እነዚህ የምህረት ድምጾች ህሊና፣ህግ ጠላት ለሚያሳድዳቸው መልካም መጠጊያ ናቸው።
ጌታ ወደ መንግስቱ በማስገባት ቀዳሚ ያደረገው ወንበዴው ነው እግ/ር ከመጨረሻው ክፉ ለምን ጀመረ ስንል በዘመናት ሁሉ ለሚነሱ አጢያተኞች ለእኔ ተስፈ አለኝ እንዲሉ ነው።ጻድቅ እንዲጸድቅ እውቅት ነው የሚፈልገው፣አጢያተኛ እንዲጸድቅ ግን እምነት ነው የሚፈልገው። " ነገር ግን ለማይሠራ፥ ኃጢአተኛውንም በሚያደድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።" (ወደ ሮሜ ሰዎች 4:5)።

በብሉይ ኪዳን ዘመን ለእስራኤል ልጆች የመማጸኛ ከተማ እንዳዘጋጀ።ሕሊና፣ህግ ለሚያሳድዳቸው፣የሰውች ክስ፣የጠላት ክስ ለሚያዳድዳቸው የመማጸኛ ከተሞች ናቸው። የኢየሱስ ክርስቶስ ቁስሎች የመማፀኛ አንቀጾች ናቸው።በጦር የተበሳ ጎኑ ለእኛ የመኖርያ ከተማችን ነው።

ከእግ/ር ቁጣ የምንድንበት በራሱ በእግ/ር ውስጥ ነው ይሄ ማለት በክርስቶስ ቁስል ውስጥ በመሸሸግ ነው።

ጌታችን ቀዳሚውን ጩኸት ይቅርታ አደረገ ለምን ስንል ቀዳሚውን ይቅርታ ያስተማረው እርሱ ነው።ለጨረሱት በደላቸው ብቻ ሳይሆን ላልጨረሱት በደላቸውን ይቅርታን አወጀ። በትልልቅ ችግሮች ውስጥ ማምለክ ይቻላል በትንሽ ቅሬታ ውስጥ ማምለክ አይቻልም።
ይቅርታ የምናደርገው ሰዎች ክፋታቸውን ስለጨረሱ አይደለም በዘለቄታው ልባችን ለመጠበቅ ነው

ማቴ 5–23–24:–እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፥ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ፥ በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፥ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ:–
መባ ማለት ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የምስጋና ስጦታ ማለት ነው።መባ ይዘህ ወደ እግ/ር ቤት ስትሄድ ያስቀየምከው ወንድምህ ትዝ ቢልህ አስቀድመህ ይቅርታ ጠይቀው። ላንተ ምንም ላይመስልህ ይችላል ግን ወንድምህ ተቀይሞሃል።የወንድምህ ትንሽ ቅሬታ የጸሎት መንገድህን ዘግቶታል በተዘጋ ሰማይ መጮ ጥቅም የለውም።መጀመሪያ መንገድህን አስለቅቅ ከዛ መባህን አቅርብ። ጌታ ከአምልኮ በፊት ይቅርታ ቀደሜ አደረገ

ይቀጥላል።
1.9K views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-26 21:52:47 " በደቀ መዛሙርትም ደስታና መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው።
"
(የሐዋርያት ሥራ 13:52)
2.0K views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-06 12:58:59 #ሜምፊቦስቴ
==========================
ንጉስ ዳዊት እና ሜምፊቦስቴ ፦
2ሳሙ 4፡4, 9፡4-13
ሜምፊቦስቴ የሳኦል የልጅ ልጅ የዮናታን ልጅ ነው፡፡እግሩም ሽባ ነበር
ሽባ የሆነበትም ምክንያት የአያቱን እና የአባቱን ሞት የሰማች ሞግዚት ይዛው ለመሸሽ ስትሞክር ከእጇ በመውደቁ ነው፡፡
2ሳሙ 4፡4
የሜምፊቦስቴ አያት የሆነው ሳኦል የንጉስ ዳዊት ቀንደኛ ጠላት እንደነበር ይታወቃል፡፡
እንዲሁ የሰው ልጆች ምንጭ የሆነው አዳም በሀጥያት ምክንያት የእግዚአብሔር ጠላት ሆነ፡፡ ሮሜ 5፡9
የሜምፊቦስቴ ሞግዚት ይዛው ልትሸሽ ስትሞክር ነው በ 5 አመቱ ወድቆ ሽባ የሆነው፡፡
እንዲሁ የሰው ልጅ በክርስቶስ በማመን በፀጋ ብቻ እንጂ ሞግዚት በሆነው በሙሴ ህግ ህይወት ሊያገኝ እና ከፍርድ ሊያመልጥ አይችልም፡፡
ገላ 2፡16, 3፡17-21,ሉቃ 14፡15
የሜምፊቦስቴ አባት ዮናታን የንጉስ ዳዊት የልብ ጓደኛ ከመሆኑ የተነሳ ንጉሱ ስለ ዮናታን ቸርነት እና ምህረት ማድረግ ፈለገ፡፡
2ሳሙ 9፡7
እግዚአብሔር ለሀጢያተኛው ሰው በክርስቶስ በኩል ምህረት ማድረግ እና ከቁጣው ሊያድነው ፈለገ።
ዮሐ 3፡14-18,ሮሜ 3፡21,ሮሜ 4፡22- ,5:1, ኤፌ 2፡4-6
ሜምፊቦስቴ ይኖር የነበረው ሎዶባር (ምድረበዳ) በሚባል ቦታ ነበር፡፡ 2ሳሙ 9፡4
የሰው ልጅም በሀጥያቱ ምክንያት ከእግዚአብሔር መገኝት እና መግቦት ርቆ ይኖር ነበር፡፡ ኤፌ 2፡11, 1ጴጥ 2፡25
ሜምፊቦስቴ ካለበት ቦታ ወደ ንጉስ ወደ ዳዊት እንዳይሄድ እግሩ ሽባ ነው ንጉስ ዳዊት ግን መልዕክተኛ በመላክ ወደ እርሱ እንዲመጣ አደረገው፡፡ 2ሳሙ 9፡1-2
ሀጥያተኛ የሆነውም የሰው ልጅ በራሱ መልካም ስራ ወደ እግዚአብሔር መሄድና በአምላክ ፊት ተቀባይነት ማግኘት ስለማይችል እግዚአብሔር ግን በክርስቶስ ወደ ራሱ ማቅረብ ፈለገ፡፡ ኤፌ2፡8, 18, ሮሜ 3፡21-24,ሮሜ 5፡6-10,
ንጉስ ዳዊት ስለ ዮናታን ሲል ለሜምፊቦስቴ ቸርነትን አደረገለት ሜምፊቦስቴም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ
2ሳሙ 9፡7
1) እንደ ንጉስ ልጅ ሆነ
2) ከንጉሱ ጋ በማእድ ተቀምጦ ንጉሱ የሚበላውን በላ
3) በኢየሩሳሌም ከንጉሱ ጋር መኖር ጀመረ
4) የአያቱን ምድራዊ ርስት መለሰለት
እንዲሁ እግዚአብሔር በክርስቶስ የቤዛነት ስራ ያመነውን ሀጥያተኛ ሰው በክርስቶስ ምክንያት
1) ልጅ አደረገው
2) በክብር በክርስቶስ በቀኙ አስቀመጠን
3) የሕይወት እንጀራ የሆነው ክርስቶስ ምግቡ ሆነለት
4) በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም በክርስቶስ መኖር ጀመረ
5) በአዳም ምክንያት ካጣነው በላይ በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ ባረከን ፡፡ ኤፌ 1፡3, ዮሐ 1፡12,1ዮሐ 3፡1-,ዮሐ 6
ኤፌ 2:6-7,ዕብ12:22-24
ቅዱሳን ልብ ሊሉት የሚገባ፦
===========================
ሜምፊቦስቴ በንጉስ ዳዊት ቸርነት እንዲህ ቢሆንም አሁንም ግን #እግሩ #ሽባ #ነው፡፡
ሰው በክርስቶስ አምኖ ከዳነ በኃላ ለመኖር መፍጨርጨር የለበትም ይልቅስ ጻዲቅ በእምነት በሕይወት ይኖራል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ወደ ሕይወቱ የጠራን እንድንኖርለት ሳይሆን ክርስቶስ በእኛ እንዲኖር ነው።
ገላትያ 2 (Galatians)
20፤ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።
ፀጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ።
የወንጌል እውነት አገልግሎት ጅማ
1.4K views09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-31 10:06:44 " እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።
"
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:18)
1.4K views07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-24 20:11:53 " እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:12)
1.7K views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ