Get Mystery Box with random crypto!

2014 ለእኔ ልዩ አመት ነበር።አንድ ቀን በትንሽዬ ማስታወሻ ላይ 10 ምርጥ የኢትዮጵያ ደራሲዎችን | Bemnet Library

2014 ለእኔ ልዩ አመት ነበር።አንድ ቀን በትንሽዬ ማስታወሻ ላይ 10 ምርጥ የኢትዮጵያ ደራሲዎችን ለማግኘት ዕቅድ ያስኩኝ።

ከነዚህ ምርጥዬ ደራሲዎች ውስጥ፦ ምህረት ደበበ፤ዳዊት ወንድማገኝ፤አሌክስ አብርሃም፤ዓለማየሁ ገላጋይ፤ኤልያስ ገብሩ፤አለማየሁ ዋሴ፤መለሰ ወጉና ደሞዝ አበበ ይገኙበት ነበር።

በጊዜው እንዴት ላገኛቸው እንደምችል ባላውቅም እንደማገኛቸው ግን 100% እርግጠኛ ነበርኩ።ከዛ እንዳቀድኩት ለመጀመሪያ ጊዜ ምህረት ደበበን አገኘሁት፤ከእሱ በኃላ ከ8ቱ ደራሲዎች ጋር ተወዳጀው።ባጠቃላይ ከ10ሩ ምርጥዬ ደራሲዎች ውስጥ 9ቱን የማግኘት ዕድል አጋጠመኝ።ከዛ ጮቤ ረገጥኩኝ፤በጣም ደስ አለኝ።

ነገር ግን እስካሁን ያላገኘሁትና ያልተወዳጀሁት ደራሲ ቢኖር አሌክስ አብርሃምን ነው።እሱን ለማግኘት በየትኛው መንገድ መራመድ እንዳለብኝ አላውቅም።ሁሌ በህልሜ ይመጣብኛል።የምነቃው አሌክስ አብርሃም ብዬ ጮሄ ነው።ከዕለታት ግማሽ ቀን የሚለው መጽሐፉ ይመቸኛል።ለነገሩ ሁሉም መጽሐፉቹ ተነበው ተነበው የማይጠገቡ ናቸው።ለማንኛውም አሌክስዬ አንድ ቀን እንደምንገናኝና ሻይ ቡና እንደምል ይታወቀኛል።

#በነገራችን ላይ ከትላልቅ ደራሲዎች ጋር ተገናኝቶ ማውራት እንዴት እንደሚያስፈራ ልነግራችሁ አልችልም።እኔ ከምህረት ጋር ስገናኝ በጣም ፈርቼ ነበር።እንደውም ምን ማለት እንዳለብኝ ግራ ከመጋባቴ የተነሳ በራሴ ዛቢያ ውስጥ ለደቂቃዎች በሃሳብ ተሸከርክሬያለሁ፤ከዛ ቀስ በቀስ ብዬ እየተጨዋወትን አመሸን።አሁን ምንም አይነት ፍርሃት የለብኝም፤ምክንያቱም ሁሉም ጓዶቼ ሆነዋል።

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@Bemnet_Library