Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ Techツ Reviews

የቴሌግራም ቻናል አርማ beki_apps_and_techs — ኢትዮ Techツ Reviews
የቴሌግራም ቻናል አርማ beki_apps_and_techs — ኢትዮ Techツ Reviews
የሰርጥ አድራሻ: @beki_apps_and_techs
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 189
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የተለያዩ:-
🎯የቴክኖሎጂ ፕሮግራሞች
🎯አዳዲስ እና ጠቃሚ አፖችን(apk)
🎯ስለ hacking መረጃዎች
🎯አዳዲስ እና ታዋቂ የpc & የmobile ጌሞች
ያገኛሉ።
☑Technological reviews !!!

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-04-24 10:22:51
#Techs_News
#Netflix

ባደረገው የዋጋ #ጭማሪ ምክንያት 200ሺ አባላቱን ለማጣት ተገዷል፤ በቅርቡም እስከ 2 #ሚሊዩን የሚሆኑትን ተጠቃሚዎቹን ሊያጣ እንደሚችል ተገምቷል።

#Share
50 viewsedited  07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-13 15:18:08
#WhatsApp

አንድን ቴክስት ከላካችሁ በኋላ #ከሁለታችሁም_ለማጥፋት የሚፈቅደውን ከ1ሰአት ወደ 2 ቀን አሳድጎታል.
99 viewsedited  12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-05 16:55:57
ሰላም ሰላም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ይህን ያውቁ ኖሯል?

የጃፓን ሳይንቲስቶች በተሳካ ሁኔታ ህልምን ቀርትፆ በማስቀመጥ ስትነሱ ህልሙን ኣንድ ላይ በማዋሃድ ማሳየት የሚችል የ MRI ማሽን መስራት ችለዋል።

ለሚቃዡ ወዳጆዎ share ማድረግ እንዳይረሱ
185 views13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-14 19:28:03 SD(Secure Digital) Card ሜሞሪ
የዘመናችን አስደናቂ ፈጠራዎች ከሆኑት መካከል ስለ ሜሞሪ_ካርድ ወይም SD(Secure Digital) CARD በጥቂቱ:

ይህች SD(Secure Digital) Card የምንላት መሳሪያ ኤሌክትሮኒክ የመረጃ ማከማቻ ስትሆን ዲጅታል ኢንፎርሜሽኖችን ለማስቀመጥ ወይም Store ለማድረግ ያገለግላል፡፡ ይቺ ዳታ ማከማቻ በዲጅታል ካሜራዎች፣ በተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ በላፕቶፖችና በኮንፒውተሮች፣ በታብሌቶች ፣በmp3 ማጫዋቻዎችና በቪድዮ ጌም ኮንስሎች ትገኛለች፡፡

የሚሞሪ ካርድ በመጀመሪያ ወደ አለም ብቅ ያለው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1995 ሲሆን ይሄውም PC Card (PCMAIA) የሚል ስያሜ ነበራቸው፡፡ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ሚሞሪዎች አሁን በስፋት ተሰራጭተው ከሚገኙ ሚሞሪዎች በመጠን ከፍ ያሉ ሲሆን መረጃ የመያዝ አቅማቸውም በጣም አነስተኛ ነበር፡፡

በአሁኑ ወቅት እነዚህ ቀደምት ሚሞሪዎች በስፋት እያገለገሉ ያሉት በእንዱስትሪያል አፕልኬሽኖችና እንደ ሞደም ያሉ ኤሌክትሪካል ዲቫይሶችን ለማገናኘት ብቻ ነው፡፡ አብዛሃኞቹ ሚሞሪ ካርዶች መረጃዎችን እንደገና መላልሶ ማጥፋትና መጫን የሚያስችሉ ሲሆን መረጃዎችንም የሚይዙት ያለምንም ፓዎር ነው፡፡

ከአመታት በኋላ መሻሻሎችን በማሳየት የተላየዩ ሚሞሪዎች ገበያውን መቀላቀል ጀመሩ በተለይ ከመጀመሪያዎቹ PC Card በመጠን አነስ ያሉና መረጃ የመያዝ አቀማቸው ከፍ ያሉ በመሆናቸው ተቀባይነት ለማገኘት ብዙ ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ ከነዚህም ውስጥም Compact Flash, Smart Media, እና Miniature Card ይገኝበታል፡፡

በ2001 (እ.ኤ.አ) Smart Media ሚሞሪ ካርድ 50% የዲጅታል ካሜራ ገበያውን ተቆጣጥሮ ነበር፡፡ Compact Flash, የተባለው የሚሞሪ ካርድ አይነት ደግሞ በአብዛኛው የፕሮፌሽናል ዲጅታል ካሜራዎች ላይ ነግሶ ነበር፡፡ እነዚህ የሚሞሪ ካርድ አይነቶች ተፈላጊነታቸው ጥያቄ ውስጥ የገባው በ2010 (እ.ኤ.አ) Micro SD ሚሞሪ ካርዶች መምጣታቸውን ተከትሎ ሲሆን በብዙ የሞባይል ብራንዶች ላይ እና ታብሌቶች ላይ በመገጠም ተፈላጊነታቸው በጣም ሊንር ችሏል፡፡

እስከ 2010 (እ.ኤ.አ) የሶኒ ካምፓኒ ለምርቶቹ ሚሞሪ እስቲክን ብቻ ይጠቀም ነበር በተመሳሳይ ታዋቂው የዲጅታል ካሜራዎች አምራች Olympus ኩባንያ sd CARD ብቻ የሚጠቀሙ ካሜራዎችን ያመርት የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ሶኒም ሆነ ኦሎምፐስ በምርቶቻቸው ላይ SD MEMORY CARD እንደተጨማሪ የሚያስገቡ ካሜራዎችን ማምረት ግድ ብሏቸዋል፡፡

አሁን ላይ በብዛት የምንጠቀምባቸው Micro SD ሚሞሪ ካርድ 1.4 mm ቲክነስ ያላቸው ሲሆን በቅርቡ ይፋ በተደረገው መረጃ መሰረት እስከ 1 TB ወይም 1000 GB መረጃን የመሸከም አቅም እንዲኖራቸው ተደርጎ ለመስራት ተችሏል፡፡ ልብ በሉ የመጀመሪያዎቹ ሚሞሪ ካርዶች መረጃ የመሸከም አቅም 32 MB ነበረ ይህ ማለት ከ30 ፎቶዎች በላይ የመያዝ አቅሙ ያልነበረው ነው፡፡ ለ25 አመታት የፍላሽ ስቶሬጅ (Flash Storage) ገበያውን እየመራ ያለው San የተባለው እውቅ ካንፓኒ አሁን ላይ ባለው ቴክኖሎጂ 128 GB SDXC Memory Card (1.4 mm) ማምረቱን ያስታወቀ ሲሆን መረጃን በስሌት ለማስርዳት ያህል አዲሱ ሜሞሪ፡-
16 ሰዓት HD ቪድዮዎች
7500 ሙዚቃዎችን
3200 ፎቶዎችን
ከ125 በላይ አፕልኬሽኖችንም በዛች ጉደኛ SDXC ሚሞሪ ካርድ (1.4mm) ከላይ የተጠቀሱትን ሚዲያ ፋይሎች በሙሉ በአንድ ላይ ማስቀመጥ ተችሏል ይለናል፡፡
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩ
187 views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-07 11:16:28 ሳምንታዊ ዜናዎች | ከቴክኖሎጂው አለም

የSony Company አናውስ እንዳደረገው ከሆነ PlayStation 5 በወጣ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በአለም ደረጃ ለ10 ሚሊዮን ሰወች እንደቸበቸቡ ተናግረዋል በPlaystion ሽያጭ ታሪክ ውስጥ በአጭር ግዜ በከፍተኛ ፍጥነት ከፍተኛ ሽያጭ ያስመዘገበ ነው ተብልዋል.

➲ Gamerሮች አረጋጉት

''AbstractEmu'' የተባለ አደገኛ Malware በ Google Playstore ላይ መገኘቱ ተዘገበ Malwareሩ ከ7 በላይ በGoogle Playstoreላይ የተጫኑ አፕሊኬሽኖች አጥቅቷል Google በ Malwareሩ የተጠቁትን አፕሊኬሽኖች ወዲያው ያስወገደ ቢሆንም Remove ከመደረጉ በፊት በተጠቃሚዎች ዘንድ Download ተደርጓል
Malwareሩ አደገኛ ያደረገው አንዴ ስልካችን ላይ ከጫንን ቦሀሏ ራሱን ይደብቃል መረጃዎች ይሰርቃል Locationናችንን ይከታተላል.

በMalwareሩ የተጠቁት 7ቱ የአፕሊኬሽኖች ዝርዝሮች
Anti-ads
BrowserData Saver
Life Launcher
My Phone
Night Light
All Passwords
Phone Plus

በMalware የተጠቁ መተግበሪያዎች በተደጋጋሚ Google Playstore ላይ መገኘታቸው የAndriod ተጠቃሚወችን ስጋት ውስጥ እየከተታቸው ነው

የGoogle Map አፕሊኬሽን በ 10Billion ስልኮች ላይ install እንደተደረገ Google ዘግቧል

በአሜሪካ San Francisco የሚገኘው RiskIQ የተባለው የCyber Security Company ባደረገው ምርመራ Discord የተሰኘው የSocialmedia Platform ለተለያዩ ተንኮል አዘል አላማ ና ለMalicious Purposes ማለትም እንደ Hosting Malicious Botnet Malware Development ለመሳሰሉት ነገሮች ሃከሮች እየተጠቀሙ እንደሆነ RiskIQ ዘግቧል


አንድ የCoinbase Crypto-currency ተጠቃሚ ከ አካውንቱ ውስጥ በ10 ደቂቃ ብቻ 11.6
ሚሊዮን $ መዘረፉ ተነገረ ባለቤቱ እንዳለው ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በተላከለት የScam Popup Notification እንደሆነ ና የCoinbase አካውንቱ እንደሚዘረጋ በማስጠንቀቅ በፍጥነት እንዲያመለከት በሚል Password እንደተሰረቀ ተናግሯል

የተላከው Notification ከትክክለኛው የCoinbase Company እንዳልሆነ ተረጋግጧል


በHwang Dong-hyuk Directed ና Write የተደረገው በፈነጆቹ September 17 2021
የወጣው የSouth Koreaው Squid Game የተሰኘው Film በ Netflix ላይ ለእይታ በተለቀቀ በመጀመሪያ 4ሳምንት ውስጥ ብቻ ከ142 ሚሊዮን በላይ በአለምአቀፍ ደረጃ ተመልካቾቻችን ቀልብ ና ትኩረት የሳበ ሲሆን በNetflix በጣም ከፍተኛ Most Watched Series Movie ተብሏል
ፊልሙን ለተመልካች ለማድረስ 21.4 million የአሜሪካ Dollar አንጠፍጥፈዋል

የSquid Game Directed ና Write የሆነው
Hwang Dong-hyuk እንደተናገረው
Squid Game Season 2 ለመመልከት ምናልባትም እስከ 2023 መጠበቅ እንዳለባቸው ለተመልካቹ አሳዉቋል.
ፊልሙን የጀመራችሁ እንግዲህ ተንቆራጠጡ

Tech በ አማርኛ
150 views08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-30 23:37:47 insufficient storage
የሞባይል ስልካችን ሜሞሪ
ሞልቷል የሚል መልእክት


አብዛኞቻችን በስልካችን ላይ ቪድዮ፣ ሙዚቃ፣ አፕልኬሽን.. ስንጭን ሜሞሪ ሞልቷል (Insufficient storage) የሚል መልእክት እየመጣ የፈለግነውን እንዳንጭን ይከለክለናል።እንዲህ ዓይነት ችግር ሲገጥመን እንዴት ሚሞሪያችንን ነፃ( free) ማድረግ እንደምንችል እንመልከት።
ከዚያ በፊት ግን ሜሞሪ ሞልቷል (Insufficient storage) የሚል መልእክት ለምን ይመጣል?

የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም አንዱ ስራ አፕልኬሽን install ስናደርግ አፕሊኬሽኖችና ከነሱ ጋር የተያያዙ ፋይሎችን ለማስቀመጥ ነው።አፕሊኬሽኖችና ከነሱ ጋር የተያያዙ ፋይሎችን ማስቀመጬ ቦታ ሲያጣ ሜሞሪ ሞልቷል ይለናል።
አፕልኬሽኖች የሞባይላችንን storage ይጠቀማሉ።እንዴት?
1ኛ፦ አፕሌክሽኖቹ ለራሳቸዉ የሚወስዱት ቦታ አለ።
2ኛ፦ የአፕልኬሽኖቹ data ማስቀመጫ የሚጠቀሙበት ቦታ አለ።
3ኛ፦ የአፕልኬሽኑ ካሽ(ጊዜያዊ ፋይል) ማስቀመጫ ቦታ ይፈልጋል።
እነዚህ ካሽ(ጊዜያዊ ፋይሎች) ጣም ብዙ ቦታ ሊይዙ ይችላሉ።
መፍትሄ
ከመፍትሔው በፊት መጀመራያ እስቶሬጃችሁን ምን ምን እንደሞላዉ እዩት።

የስልካችሁ ስቶሬጅ መረጃ ለማየት ከታች ያሉትን ስፔፖች ይከተሉ
Setting ዉስጥ ይግቡ
ከዛ Storage የሚለዉ ዉስጥ ይግቡ ።
ከዚያ የ RAM ፤ Internal Storage ፤ SD Card የያዙትን መጠን በ% ያሳያችሗል።
Internal Storage የሚለዉን ይጫኑት ።
Avaliable ፦ የሚለው ላይ አሁን ያላችሁ ነፃ የሆነ የሚሞሪ መጠን ነው። System ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ለራሱ እና ከስልኩ ገር ለሚመጡ ለአንዳንድ አፕልኬሽኖች(እንደ Setting ፤ Chrome ፤ Phone ፤GMail ፤Google ፣Contacts ፤ Photo. ..) ለማስቀመጥ የተጠቀመበት memory ያሳየናል።
Owners የሚለው ላይ እኛ የጫንናቸዉን አፕሌኬሽኖች፣ፎቶዎች፣ ወዘተ በዝርዝር ያሳየናል።
አሁ ከላይ ካያችኋቸው ፋይሎች ዉስጥ ብዙ ቦታ ይዞ ሚሞራያችሁን የሞላዉን ትመርጣላችሁ።
አፕልኬሽን ከሆነ ብዙ ጊዜ የማትጠቀሙበትን uninstall ማድረግ።

Uninstall ለማድረግ Setting->Apps ከዛ uninstall ለማድረግ የፈለጋችሁትን አፕልኬሽን መርጣችሁ ስትጫኑት uninstall የሚል ሲመጣ አሱን ይጫኑት።
ፎቶ ከሆነ የማትፈልጉትን ፎቶ አየመረረጣችሁ ማጥፋት አለባችሁ።Video ከሆነ የማትፈልጉትን Video እየመረጣችሁ ማጥፋት።Audio ከሆነም ምረጡና ያጥፉ።
ከዚያም Clear data የሚለዉን በመጫን ሚሞሪ ላይ ያሉትን ፋይሎችያጥፉ

SD Card የስልኩ default ማስቀመጫ ለማድረግ ከፈለጋችሁ፦Setting-> Storage->default write disk የሚለዉጋ Phone Storage የሚለዉን ተመርጦ ታገኙታላችሁ አናንተ ግን SD card የሚለዉን ምረጡ።
120 views20:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-29 16:57:03 አጠገባችሁ ያለው ሰው Wifi Connect አድርጎ ፓስወርዱን ሁለታችሁም አታውቁም እንበል፤ በጣም በቀላሉ ያለምንም APP ብቻ ኮኔክት ምታደርጉበትን ዘዴ ልጠቁማቹ....

◉ Step 1. በመጀመሪያ አንዱ ስልክ ኮኔክት መደረግ አለበት መጠቀም ምትፈልጉት ዋይፋይ ላይ...
◉ Step 2. በዛዉ ስልክ Setting WiFi ከዛ Conect ያደረጋችሁትን Wifi ያሳያችኋል።

◉ Step 3. የ Setting ምልክቷን ይጫኑ...

◉ Step 4. QR Code የሚለዉን ይምረጡ...

◉ Step 5. በእርስዋ ስልክ Setting WiFi ይግቡ...

◉ Step 6. በስተቀኝ ወደላይ ያለዉን Icon በመንካት በሌላ ስልክ እስክሪን ላይ ያለዉን QR Code Scan ያድርጉ።

QR Code ሁላችሁም ስልክ ላይ ሊኖርም ላይኖርም ይችላል፤ እንደየስልካችሁ አይነትና Android Version ይለያያል።

#ሁሌም_ከኛ_ጋ_ወደ_ፊት
113 views13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-26 17:39:24
Telegram hits 1 Billion downloads on Google Play Store

@Telegram #Android
113 views14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-24 08:14:43 ኮምፒውተርዎን ፈጣን የሚያደርጉ 9 ዘዴዎች


-1. ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፎቶዎች ዎልፔፐር አይጠቀሙ፡፡
-2. ሁሌም ኮምፒዩተሩ ከፍቶ ሳይጨርስ አፕሊኬሽን ለመክፈትም ሆነ ለመነካካት አይሞክሩ፡፡
-3. አፕሊኬሽን ከዘጉ በሁዋላ ዴስክቶፑን ሪፍሬሽ ያድርጉ፤ ይህም ራም ሜሞሪን ነፃ ያደርጋል፡፡
-4. የማይጠቀሙበት ሶፍትዌር ካለ ከኮምፒውተሩ ይሰርዙ (አን-ኢንስታል) ያድርጉት)፡፡
-5. ዴስክቶፕ ላይ ፋይል አያስቀምጡ፤ ሾርትከትም መብዛት የለበትም፡፡
-6. ኮምፒዩተሩ ሲከፈት በራሳቸው የሚከፈቱ ለምሳሌ: ስካይፕ አይነት አፕሊኬሽኖች ካሉ disable ያድርጉ
7. Recycle binን ሁሌም ባዶ ያድርጉ::
8. ሀርድ ዲስኩን ሁለት ፓርቲሽን ይፍጠሩለት፡፡
9. ብዙ ሶፍትዌሮችን ባንዴ አይክፈቱ::


@Beki_apps_and_techs
113 views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-22 23:27:29 በቫይረስ የተጠቃ ፍላሽ ዲስክ እንዴት ያለአንቲ ቫይረስ እንደምናጸዳውና ስንገዛው እንደነበረው አዲስ እንደምናደርገው እናያለን።
እባክዎ ከመጀመርዎ በፊት ፍላሹ ላይ ጠቃሚ ፍይል ካለዎት ወደ ሌላ ቦታ ኮፒ ያድርጉ። ምክንያቱም ፋይሉ ሙሉ በሙሉ ስለሚጠፋ!
በመጀመሪያ ኮምፒዩተራችን ላይ '#command_prompt' ወይም '#cmd' እንከፍታለን።
( '#cmd'ን ለመክፈት በመፈለጊያችን ላይ #cmd ብለን #search እናደርጋለን. #Cmd
ሲመጣልን right click አድርገን run as #administrator የሚለውን በመጫን cmdን
እንከፍታለን)
Cmd ከከፈትን በኋላ የሚከተሉትን ትእዛዞች በቅደም ተከተል እናስገባለን። እያንዳንዱን
ትእዛዝ ከጻፍን በኋላ ENTER ቁልፍን እንጫናለን
1. #DISKPART

2. #LIST DISK

(አሁን በኮምፒውተሩ ላይ ያሉትን ዲስኮች ይዘረዝርልናል. ለማጽዳት
የፈለግነውን ፍላሽ ቁጥር ከለየን በኋላ ወደ ሶስተኛው ትእዛዝ እንሄዳለን። ምሳሌ.disk 1)

3. SELECT DISK *

(በኮከቡ ፋንታ ሁለተኛው ትእዛዝ ላይ የለየነውን የፍላሽ ቁጥር እናስገባለን)

4. CLEAN

(በዚህ ጊዜ ፍላሹ ላይ ያለውን ማንኛውም ነገር ያጠፋዋል)
5. CREATE PARTITION PRIMARY

(ለፍላሹ ይዘት ይፈጥራል)

6. SELECT PARTITION 1

7. ACTIVE

(ይህ ፍላሹን ዝግጁ ያደርገዋል)

8. FORMAT FS=FAT32 Quick

(ይህ ፋላሹን በጥልቀት በመሰረዝ በውስጡ ያሉትን
ማንኛውም ቫይረስ ወይም ሌላ ችግር ያጠፋል። ሂደቱ የተወሰነ ጊዜ ስለሚወስድ
እስከሚጨርስ ወይም 100 % እስኪሞላ በትዕግስት እንጠብቀዋለን)

9. ASSIGN

(አዲስ ለፈጠርነው ፍላሽ የፊደል ስም ይሰጥልናል)

10. EXIT

(ፕሮሰሱን ይጨርስልናል)
አሁን አዲሱን ፋላሻችንን መንቀልም ሆነ መጠቀም እንችላለን። ይህንን መንገድ በመጠቀም
ማንኛውንም ቫይረሱ ያለበት ፍላሽ
ማስተካከል እንችላለን።
120 viewsedited  20:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ