Get Mystery Box with random crypto!

الم (ሱረቱ አል-ሩም - 1) አ.ለ.መ (አሊፍ ላም ሚም)፡፡ غُلِبَتِ الرُّومُ | ♡በረካ♡ መልቲ ♡ሚድያ♡

الم

(ሱረቱ አል-ሩም - 1)
አ.ለ.መ (አሊፍ ላም ሚም)፡፡


غُلِبَتِ الرُّومُ

(ሱረቱ አል-ሩም - 2)
ሩም ተሸነፈች፡፡

فِي أَدْنَى الْأَرْضِ وَهُم مِّن بَعْدِ غَلَبِهِمْ سَيَغْلِبُونَ

(ሱረቱ አል-ሩም - 3)
በጣም ቅርብ በሆነችው ምድር፡፡ እነርሱም ከመሸነፋቸው በኋላ በእርግጥ ያሸንፋሉ፡፡


فِي بِضْعِ سِنِينَ ۗ لِلَّهِ الْأَمْرُ مِن قَبْلُ وَمِن بَعْدُ ۚ وَيَوْمَئِذٍ يَفْرَحُ الْمُؤْمِنُونَ

(ሱረቱ አል-ሩም - 4)
በጥቂት ዓመታት ውስጥ (ያሸንፋሉ)፡፡ ትዕዛዙ በፊትም በኋላም የአላህ ነው፡፡ በዚያ ቀንም ምእመናን ይደሰታሉ፡፡


بِنَصْرِ اللَّهِ ۚ يَنصُرُ مَن يَشَاءُ ۖ وَهُوَ الْعَزِيزُ الرَّحِيمُ

(ሱረቱ አል-ሩም - 5)
በአላህ እርዳታ (ይደሰታሉ)፡፡ የሚሻውን ሰው ይረዳል፤ እርሱም አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡


وَعْدَ اللَّهِ ۖ لَا يُخْلِفُ اللَّهُ وَعْدَهُ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

(ሱረቱ አል-ሩም - 6)
አላህ እርዳታን ቀጠረ፡፡ አላህ ቀጠሮውን አያፈርስም፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡


*መልካም አዳር*


http://t.me/barkamaltmadya

http://t.me/barkamaltmadya