Get Mystery Box with random crypto!

ባለ ራዕይ ትውልድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ balerai_wetat — ባለ ራዕይ ትውልድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ balerai_wetat — ባለ ራዕይ ትውልድ
የሰርጥ አድራሻ: @balerai_wetat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 703
የሰርጥ መግለጫ

ውድ የሀገሬ ልጆች ሠላም ሁሉ ከእናንተ ጋር ይሁን!!!!!
የሀገሬ ወጣቶች ከጭንቀት፤ ከድብርት እንዲሁም ከተለያዩ ሱሶች ተላቀውና ነፃ ሆነው ባለራዕይ ወጣት እንዲሆኑ የው

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-28 17:12:58
112 viewsሌዊ, 14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 09:42:38 2, ባለራዕይ ወጣት የአጉል ፍቅር እስረኛ አይደለም።
# የአጉል ፍቅር እስረኛ የሆኙ ሰዎች ለስሜታቸው ነው የሚገዙት።
አንድ ነገር ላይ ከመጠን በላይ እንድትጣበቅ እና እንድትደጋግም የሚያደርግህ ነገር ቢኖር ስሜትህ ነው።
ለስሜታቸው የሚገዙ ሰዎች ደግሞ አቋም የላቸውም ወላዋይ ናቸው።
ምክንያቱም ስሜት ድስት ነገር ነው ድስትን ስትጥደው እንደሚግል ስታወርደው እንደሚቀዘቅዝ ልክ እንደዛ ስሜትም ነገሮች ሲግሉ ይግላል ሲቀዘቅዙ ይቀዘቅዛል፤ ወጥ የሆነ አቋም የለውም።
# የአጉል ፍቅር እስረኛ የሆኑ ሰዎች በችግራቸው ይደሰታሉ፤ በደስታቸው ይሰቃያሉ።
# የአጉል ፍቅር እስረኛ የሆኑ ሰዎች የህይወት ሚዛናቸው የተሰረቀባቸው ናቸው። ነገሮችን የሚመዝኑት ስሜታቸውን ባነቃቃው ነገር ልክ ነው። ስሜታቸውን ያነቃቃው ነገር የ15,000ብር ሞባይል መግዛት ከሆነ እነሱም ቤተሰባቸውም የሚበሉት ምግብ ሳይኖር የሚያመዝኑት እንዴት እንደሚገዙት የሚጨነቁት ስለሞባይሉ ነው።
የናትና ያባታቸውን አልጋ እስከ 6ስአት እየተኙና እየሰበሩ ከእንቅልፋቸው ሲነሱ የመጀመሪያ ስራቸው ሞባይል መጎርጎር በቃ እነሱ የአጉል ፍቅር እስረኞች ናቸው።
# ባለራዕይ ወጣት የአጉል ፍቅር እስረኛ አይደለም።
#የአጉል ፍቅር እስረኞች ህይወት በመነፅር እንጂ ህይወት በመሥታዎት አይደሉም።
ወደውጭ እንጂ ወደራሳቸው አይመለከቱም ለዚህ ነው የህይወት ሚዛናቸው ባፈቀሩት የተሰረቀባቸው ናቸው የሚባለው።
ያገሬ ልጆች እወዳችኋለሁ
@Balerai_wetat
@Balerai_wetat
@Balerai_wetat
310 viewsሌዊ, 06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 09:32:17 Channel photo updated
06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 18:30:07 ጥበብ እና አስማት
ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን

ጥበብ ማለት የምናደርገውን ነገር አስቀድመን የምንመረምርበት ልባችንን በማስተዋል የምናሰፋበት ማለት ነው።
1ኛ ነገሥት 4÷29
"እግዚአብሔርም ለሰሎሞን ጥበብና ማስተዋልን እደ ባህርም ዳር እዳለ አሽዋ የልብ ስፋትን ሰጠው"።
2ኛ ነገሥት 21÷6
"ልጁንም በእሳት አሳለፈ÷ ሞራ ገላጭም ሆነ÷ አስማትንም አደረገ÷ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠቋዮችንም ሰበሰበ፤ ያስቆጣውም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገረ አደረገ"።
በዚህ የመጽሀፍ ቅድስ ጥቅስ የምንረዳው አስማት የሚያደርጉ ሰዎች መናፍስትን እደሚጠሩ እና እደ ጠቋዮች ለሰይጣን ተገዚ የሆኑ ሰዎች መሆናቸውን ነው።

ያገሬ ልጆች ስሙኝ ልንገራችሁ ሰይጣን ሁሌም የእግዚአብሔርን ተቃራኒ ነው የሚያደርገው።
እግዚአብሔር የዋህነትን፤ አዛኝነትን፤ ደግነትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባህርያትን ለመግለጽ በግን ሲጠቀም
ሰይጣን ደግሞ በባህሪ የበግ ተቃራኒ የሆነችውን ፍጀል ይጠቀማል።
እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን በእጣን እና በከርቤ መቅደሱ እንደ ሚታጠን እንደሚጨስለት
ሰይጣን ደግሞ ሲጋራ አሺሽ የመሳሰሉት ነገሮች እዲጨሱለት ይፈልጋል።

ልክ እደዚሁ ሁሉ መንገዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር ላደረጉ ሰዎች በእውነት መንገድ እዲመላለሱ የሚሰሩትን፤ የሚጠቀሙትንና የሚያደርጉትን ነገር በመመርመር(አስቀድሞ በማሰብ) ከስህተት እና ከክፉ እዲጠበቁ እግዚአብሔር ለነዛ ሰዎች ጥበብን ይሰጣል።

ሰይጣን ደግሞ ብዙ ሰዎች ከእግዚአብሔር ስራ ይልቅ በሰይጣን ስራ እዲያደንቁ፤
ከእግዚአብሔር ትአምራት ይልቅ በሰይጣን አስማት እዲገረሙ፤ ብዙ ሰዎችን ወደራሱ ለማምጣት በጨለማው ባሉ መናፍስት በስውሩ መንፈስ ለሰይጣን ተገዢ ለሆኑ ሰዎች የሚሰጣቸው ስውር አሰራር ነው።

ያገሬ ልጆች አስማትን በጥበብ መተካት ማለት
መጥምቁ ዩሃንስ የእግዚአብሔር በግ ያለውን ክርስቶስ በሰይጣን ፍጀል መተካት እደማለት ነውና ጥበብን በአስማት እዳትተኩ ተጠንቀቁ።

ጥበበኛ ለመሆን እግዚአብሔር በመፍራት መንገድህን ከእግዚአብሔር ጋር ማድረግ እንጂ አሰማትን ተከትሎ የሰይጣን ተገዚ መሆን አይደለም።

ከሰይጣን አስማት የእግዚአብሔር ጥበብ እጅግ ሀያል ነው። ለዚህ ደግሞ በብሉይ ኪዳን ያሉ ትልልቅ አስማተኞ እግዚአብሔር ጥበብን ባበዛላቸው በአገልጋዮቹ መውደቃቸው በቂ ማስረጃ ነው።

ያገሬ ልጆች አስማት ምድራዊ ስራ ነው። ጥበብ ግን ሰማያዊ ስራ ነው።
ዘላለማዊ ህይወት የሚሰጠን ደግሞ ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ስራ ነውና ምድራዊ ስራን እዳታዳንቁ ተጠንቀቁ እላችኋለሁ።

እወዳችኋለሁ

@Balerai_wetat
@Balerai_wetat
@Balerai_wetat
241 viewsሌዊ, 15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 21:14:35 ሙሽራው ሲመጣ መሯሯጥ
ተቻኩሎ ዘይትን ለማግኘት
አያዋጣም በሩ ይዘጋል
ጊዜው አልፎ መች ይከፈታል......
@anechenashicaraka
@anechenashicaraka
@anechenashicaraka

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን አዲስ አበባ ሰበካ ኮተቤ ንኡስ አጥቢያ ሃሌሉያ ኳየር መዘምራን
279 viewsሌዊ, 18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 18:02:30
ዛሬም ይህ ልቤ ኢየሱስ ኢየሱስን ይለኛል ፍለጋው መቼ ይቆማል
እሱ የነፍሴ ዋስትናዋ ነው
እፈልገዋለሁ...........
ድንቅ መዝሙር አድምጡት ትወዱታላችሁ
@anechenashicaraka
@anechenashicaraka
@anechenashicaraka

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሰበካ ጎፋ አጥቢያ አጠቃላይ ኮንፈረንስ
271 viewsሌዊ, 15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 18:08:18 በቶሎ ይነበብ ልንነቃ ይገባል
ለማንበብ 15 ደቅቃ ብቻ ስጥ ህይወትን ይቀየራል አትሳሳት ምክኒያቱም እውነትና እየተፈፀመ ያለ ነገር ስለሆነ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ዓለም ወዴት እየሄደች ነው? 1. - መጽሐፍ ቅዱስን ማቃጠል በኡጋንዳ በይፋ ተረጋግጦአል
* በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ፣ ወንድ ወይም ሴት በዝሙት ምክንያት ሌላውን የመክሰስ መብት የለውም
*በአሜሪካ እየታየ ያለው የወንድ ለወንድና የሴት ለሴት ጋብቻ
*ጀርመን ወንድም እህቱን ማግባት እንደሚችል ፣ አባት ልጁን:እናት ልጆአን የማግባት ፍቃድን መስጠቱ ፡፡
*የmiami ከተማበመንገድ ላይ ፣ በቤተ ክርስቲያን ፣ በገቢያ ፣ በእግር ኳስ ሜዳ ወዘተ ውስጥ ወሲባዊ ግንኙነት በማንኛውም መንገድ ማግኘት እንዲችሉ መፍቀዶአ
.*ካናዳ (ከእንስሳት ጋር የ sexታ ግንኙነትን መፍቀዶአ
* በስፔን ውስጥ-የወሲብ ፊልሞች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና በዩኒቨርሲቲዎች መፈቀዱ *- ለአካለ መጠን ያልደረሱ ዝሙት አዳሪዎች ፈቃድ ማሪ ሉክ በህግ መፈቀዱ *በመጨረሻም ዩኤስ አሜሪካ የሰይጣንን ቤተ ክርስቲያን ከፍታለች ፡፡ በይፋ።
የተከበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች ፣ መጨረሻው ተቃርቧል ፣ ጌታ ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል! ማርታናታ!!!
ክርስትያኖች ትኩረታቸው እየተከፋፈሉ ሲሆን ዲያቢሎስ መለኮታዊውን ምህረት ለማስቆም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ነፍሳት ከእርሱ ጋር ሊወስድ ይፈልጋል ፡፡ ደቂቃ ካለዎት ... ይህንን መልእክት ያጋሩ ፡፡ ለምን በቤተክርስቲያን ውስጥ እንተኛለን ? ስለ እግዚአብሔር ማውራት ከባድ የሆነው ለምንድነው ሐሜት ለመናገር በጣም ቀላል የሆነው ለምንድነው? የእግዚአብሔርን መልእክት ችላ ማለት ለምን ቀላል ሆነ?
ይህንን መልእክት ለጓደኞችዎ ይልካሉ ወይም ችላ ይላሉ? እግዚያበሔር “በሰዎች ፊት ብትክዱኝ በአባቴ ፊት እክድዳችሁአለሁ” አለ ፡፡ እግዚያበሔር ከወደዱ ይህንን መልእክት ለምርጥ ጓደኞችዎ እና በቡድን በ 60 ሴኮንድ ውስጥ ያጋሩ ፡፡ እግዚአብሔር ይባርኮት. ኣሜን
የአለም መጨረሻ ተቃርቧል አትዘናጉ
አሁን ያለንበት 2014 ዓም + 5500 ዘመን=7514 ስለዚህ ከ 8ኛው ሽ ላይ ቀንሱት ።
8000 – 7514= 486 ዓም ይቀራል።
ነገር ግን ሰምታችሁ ከሆነ ዘንዶ 400 ዓመት ገዝቷል ይባላል እስኪ ጠይቁ።
እና የዘንዶው ሲቆጠር 486 – 400 =86 አመት ቀረው።ትንቢቱም እየተፈፀመ ነው። ሌላው ይህ በንዲህ እንዳለ ደሞ
666 አሁን እዚህ በደጃችን ነው፡፡ አጠንክረን እንፀልይ፡፡ የአውሬው
ቁጥር 6 6 6 የሚፈፀምበት የትንቢት ጊዜ አልቋል/ተፈፅሟል፡፡
የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ባስተላለፈው የኦባማን የጤና
ሽፋን ረቂቅ በህግ እንዲካተት ተደርጓል፡፡ የህግ ተግባሩ በቅርቡ
ይጀምራል፡፡ ይህን የጤና ሽፋን ረቂቅ በእያንዳንዱ የአሜሪካ ዜጋ
የሰውነት ክፍል ላይ ግላዊ የሬዲዬ ፍሪኩዌንሲ ቺፕስ መልክ (RFID
CHIPS) እንዲተከል ታዟል፡፡ ይህ ቺፕስ በግንባር ወይም በክንድ ላይ
ይደረጋል፡፡ ይህ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው በራዕይ 13 :
15 -18 የተቀመጠውን የአውሬው ምልክት ይፈፀም ዘንድ ነው፡፡ እና
አሁንም ስለ ፍፃሜው ትጠራጠራለህ? ታውቃለህ ለኦባማ የተለየ
መኪና እንደተሰራ አውሬው የሚባል? ተዘጋጅ ንጥቀት አሁን
ይጀምራል፡፡ ራዕይ 13ን ቀድመው ተጫውተውታል፡፡ ብዙዎች ግን
ይህን አልተገነዘቡትም፡፡ 1. ለምንድን ነው ይህ ችፕስ ከባንክ
አካውንት ጋር የተቆራኘው ወይም የተገናኘው? አስታውሱ መጽሐፍ
ቅዱስ እንደሚለው ካለ አውሬው ቁጥር 666 ልትገዙም ወይም
ልትሸጡም አትችሉም ስለሚል፡፡ እስኪ ገምቱ ይህ ቺፕስ ከገንዘብ
ዝርዝር መረጃ ጋር ለምን ተገናኘ? እንዲያውም በጣም ያሳዘነኝ
በቤተክርስቲያን ያሉ ብዙዎች ሰዎች ጌታ ሲመጣ ይህን ሁኔታ
ሊያልፉት አይችሉም፡፡ ደግሞም ብዙዎቹ መጨረሻው እንደቀረበ
አያውቁም፡፡ የቴክኖሎጂ በጣም መራቀቅ ምክንያት ነው ብላችሁ
መልስ እንዳትሰጡኝ፡፡ በማንኛውም የህይወት ጎዳናችሁ
ከእግዚአብሔር ጋር ካልተስማማ አሁኑኑ ንሰሀ ግቡና ተለወጡ፡፡
ካለበለዚያ መንግስተ ሰማያትን ካጣችሁት ገሀነምን አታጡትም፡፡
ስለዚህ አስቡበት፡፡ ገሀነም መልካም ስፍራ አይደለም በጣም
አስከፊው ክፍሉ እንደ መንግስተ ሰማያት ዘላለማዊነት እንዳለበት
እዚህም እንደዛው ነው፡፡ ጆሮ ያለው ይስማ መንፈስ ለአብያተ
ክርስቲያናት የሚለውን ይስማ፡፡ ጠቃሚ ያልሆነ ነገር ከምትልኩ ይህን
ለሌላው ብታስተላልፉ መልካም ነው፡፡ ለምታውቋቸው ቅርብ
ለሆኗችሁ ሰዎች ላኩላቸው፡፡ እስኪ የወንጌላዊ ስራ እንስራ፡፡
እባካችሁ ለምታውቋቸው ለእያንዳንዳቸው በየስማቸው ላኩላቸው፡፡
ለሞባይል እንደምንጠነቀቅ ያክል ለእግዚአብሔር ቃል ብንጠነቀቅ
ምን እንደሚሆን ልትገምቱ ትችላላችሁ፡፡ ከዚህ ደግሞ በጭራሽ
ልንላቀቅ ነፃ ልንሆን አንችል፡፡ ስለዚህ የቻልነውን ያክል እንትጋ
እንጋደል፡፡ 7% የሚሆኑቱ ናቸው መልዕክቱን የላኩት በድጋሚ 93%ቱ
ግን አልላኩም አላወቁም ስለዚህ ጠንክረን እንስራ፡፡ ሰይጣን
እንዲህ ይላል፡- " የሚገርመኝ ሰው እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ
አይታዘዝም እኔን ይጠላኛል ግን ይታዘዘኛል፡፡" ይህን መልዕክት በኋላ
እንዳትልኩት አሁኑኑ ላኩት!!!

ቅዱስ ለ #15 ሰው እባካችሁ
466 viewsሌዊ, 15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 03:16:27 #3ኛ ሰዎች የሚሉት፦ (ጆሆባዎች) ሚካኤል ወልድ ለመሆን ከድንግል ማርያም ተወለደ እንጂ ቃል ሥጋ አልሆነም ነው
#ይህ አእምሮ ኢየሱስ ያለውን ሲናገር እንዲህ ይላል፦ ዕብ1÷5-6 "ከመላዕክትስ አንተ ልጄ ነህ እኔ ወልጄሃለሁ ደግሞም እኔ አባት እሆንነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል ያለው ከቶ ለማን ነው? ደግሞም በኩርን ወደ አለም ሲያገባ የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ" እንደሚል አላነበባችሁምን? "እኔና አብ አንድ ነን በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል" ዮሐ12÷44-45፣ ዮሐ14÷7-11
#ሰዎች የሚሉት፦ "አንድ አምላክ በአንድ አካል ኢየሱስ ተገልጦአል" የሚሉ አብንና መንፈስ ቅዱስን ክደዋል ነው።
#ይህ አእምር ኢየሱስ ያለውን እንዲህ ይመልሳል፦ በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው ነው። ሐዋ2÷23፣ ዮሐ3÷13፣ 1ኛ ቆሮ12÷6፣ ዮሐ14÷6-10 በአጠቃላይ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰብከው አንድ አምላክን እንጂ ሁለት ወይም ሦስት አምላክ(ሦላሴን) አይደለም ነውየሚለው።
ሁለተኛውንና ስድስተኛውን የበጎ የአእምሮ አይነት ለሁላችን ክርስቶስ ይቸርን አሜን
ያገሬ ልጆች እወዳችኋለሁ

@anechenashicaraka
@Balerai_wetat
@anechenashicaraka
@Balerai_wetat
@anechenashicaraka
@Balerai_wetat
196 viewsሌዊ, 00:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 03:16:27 ይህ የአእምሮ አይነት በጣም አስደናቂ መረዳቶች ያሉት ነው። ካለው ጥበብ የተነሳ ከእግዚአብሔር ቁጣ እንኳ ያዘገየዋል ደግሞ ይቅር ባይ አእምሮ ነው። ይህ አእምሮ የማይፈቱ ባልና ሚስቶች የማይጣሉ ባልና ሚስቶች ሳይሆኑ በይቅርታ የሚኖሩ ባልና ሚስቶች እንደሆኑ የሚያምን፤ ይቅርታ የማይንደው የክፋት ከፍታ የማይደፍነው የጥላቻ ጉድጓድ የማይሽረው የውስጥ ቁስል እንደሌለ የሚያስብና ይቅርታን -የክፋት መዶሻ -የቂም ማርከሻ -የቃል ኪዳን ማደሻ -የቤቱ ጋሻ የሚያደርግ ይቅር ባይነቱም ለክብር የሚሆንለት በጥበብ እጅግ የተባረከ አእምሮ ነው።
5, ምክርን የሚሰማ አእምሮ ምሳ20÷5 "ምክር በሰው ልብ እንደ ጠሊቅ ውሃ ነው፤ አእምሮ ያለው ሰው ግን ይቀዳዋል።"
ይህ አእምሮ ለመስማት የፈጠነ ለመናገር ግን የዘገየ ነው። አንድ አፍን በሁለት ጆሮው የሚመረምርና መልካም መምክርን ከሰው ሁሉ አፍ የሚቀዳ የአእምሮ አይነት ነው።
6, ለክርስቶስ የተማረከ አእምሮ 2ኛቆሮ10÷3-5 "በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤ የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤ የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥..."
ይህ አእምሮ ለክርስቶስ ኢየሱስ የሚታዘዝ እግዚአብሔርንም ከፍ ብለናል ብለው የሚፈታተኑትን የሚያፈርስ ቅዱስ ወንጌሉን ለፍጥረት ሁሉ እየሰበከና እየመሠከረ አእምሮንና ነፍሳትን የሚማርክ የእግዚአብሔር ምስክር እንደ ማለት ነው። ይህ አእምሮ ሰዎች የሚሉትን እየነቀፈ ኢየሱስ የሚለውን ይነገራል። ለምሳሌ፦ #ሰዎች የሚሉት፦ 1ኛ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር የኢየሱስና የመንፈስ ቅዱስ የማዳን ስም ነውና ለጥምቀት ስንጠቀምበት ያድነናል የሚል ነው።
#ይህ የአእምሮ አይነት ኢየሱስ እንዳለው ሲመልስ ደግሞ እንዲህ ነው፦ የእግዚአብሔር አብም የወልድም የመንፈስ ቅዱስም አዳኝ ስም ኢየሱስ የተባለው ስሜ ብቻ ሰለሆነ ለእግዚአብሔር አብ ክብር የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም ብቻ አድርጉ ነው ኢየሱስ ያለው፦ ማቴ1÷20-23፣ ሉቃ24÷47፣ ቆላ3÷17፣ ፊል2÷9-11፣ ሐዋ4÷12፣ ዮሐ5÷43፣ ዮሐ16÷23-24፣ ዮሐ17÷26
#2ኛ ሰዎች የሚሉት፦ የአብ ልጅ እግዚአብሔር ወልድና የማርያም ልጅ ክርስቶስ በተዋህዶ አንድ አካል ናቸው የሚል ነው።
#ይህ አእምሮ ኢየሱስ እንዳለው ሲመልስ እንዲህ ነው፦ እኔና አብ በተዋህዶ አንድ አካል ነን የሚል ነው ዮሐ1÷1-4 ዮሐ14÷6-10 እግዚአብሔር በስጋ ተገልጦ የተገለጠበት ስጋው ወልድ ተባለ እንጂ አብና ወልድ ሁለት አካል አይደለም ዮሐ1÷14፤ ከአብርሃም በፊት የነበረው አምላክ በሥጋ መጣ እንጂ እንደ አዲስ አልተወለደም ዮሐ8÷58 ነው የሚለው።
171 viewsሌዊ, 00:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 03:16:27 5, ከንቱ አእምሮ፡-ኤፌ 4፡14 " እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ህፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም።"

‹‹በትምህርት ነፈስ ሁሉ›› ሲል፡- ይህ ሀሳብ ጠቢቡ ሰሎሞን ከንቱ ነፋስ ካላው ጋር ተዛማጅነት ያለው ሲሆን ሰሎሞን እንዲህ ነው የሚለው "ከንቱ ነፋስን እንደ መከተል ነው" ከንቱ ንፋስ እዚጋም እዛጋም የሚል፤ እንደ ያዕቆብ የበኩር ልጅ(እንደ ሮቤል) የሚወላውል፤ የማይጸና ማለት ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በትክክል ሊያስተላልፍ የፈለገው ሀሳብ ዛሬ ታይቶ ነገ በሚጠፋ፤ በማይጸና ትምህርት እየተልፈሰፈስን(እየተፍገመገምን) ወደፊት ህፃናት መሆን እንደማይገባን ሐዋርያው ጳውሎስ ይዘግባል፡፡
የዚህ አይነቱ አእምሮ፦ የተበታተነ ብዙ ቅጠል ያየች ፍጀል እዚህም እዛም እንደምትል ልክ እንደዛ ይህም አእምሮ ወላዋይና ተቅበዝባዥ ነው።

6 የጠፋ አእምሮ 1ኛ ጢሞ6÷4-5 "እግዚአብሔርን ለመምሰል በሚስማማ ትምህርት የማይጠጋ ቢሆን፥ በትዕቢት ተነፍቶአል አንዳችም አያውቅም፥ ነገር ግን ምርመራን በቃል መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፥ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ።"
ይህ አይነት አእምሮ ካንተ በላይ ስላንተ እኔ አቅልሃለሁ የማለት ባህሪን የሚያሳይ አይነት ነው። በቅንዓቱ፣ በክርክሩ፣ በክፉ አሳቡና በስድቡ ሁሉ የሚያሳየው እኔ ነኝ ስላንተ ካንተ በላይ የማቀው አይነት ባህሪ አለው። ለምሳሌ በስድቡ ስናይ አንድን ውሻ ያልሆነን አካል ውሻ ይላሉ። ያልሆነውን ነው ይላል። እውነት ከእርሱ ጠፍታለች። እግዚአብሔርን መምሰል እንካ ማትረፊያ እንደሆነ እያሰቡ በእግዚአብሔር ፊት እንኳን እንደ አዋቂ ያደርጋቸዋል ግን ምንም አያቁም።
ለ, በጎ አእምሮ
1, ጸጋና ጥበብ የተሞላ አእምሮ ኤፌ1÷8-9 "ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን።"
ይሄ የአእምሮ አይነት በግልጽ ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ስለገለጸው ማብራሪያ አያስፈልገውም። እንደተሰጠው ጸጋ መጠን በአገልግሎቱ በጥበብና በማስተዋል ነገሮች ሁሉ እንዲ በጥበብና በማስተዋል የሚያደርግ ነው።
2, መጽሐፍትን የሚያነብና የሚረዳ አእምሮ ሉቃ 24÷45 "በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤"
ይሄኛው የአእምሮ አይነት መጽሐፍትን ለማንበብ የማይታክት የማይሰለቸው ደግሞ ያነበበውን መጽሐፍ በትክክል መረዳት የሚችል ለማንበብ ካለመሰላቸቱ የተነሳ እለት እለትም አዲስ እውቀትን ያገኛል እርሱም እራሱ አዲስን ነገር ይሻል
3, ነገሮችን በጥልቀት በማየት አጥብቆ የሚረዳ አእምሮ ሮሜ14÷5 "ይህሰው አንድ ቀን ከሌላ ቀን እንዲሻል ያስባል፥ ያ ግን ቀን ሁሉ አንድ እንደሆነ ያስባል እያንዳንዱ በገዛ አእምሮው አጥብቆ ይረዳ።"
ይህ አእምሮ እያንዳንዱን ነገር በጥልቀት ማስተዋል አጥብቆ የሚረዳ ለነገሮች ሁሉ ትኩረት የሚሰጥ ግዴለሽነት የማያጠቃው ትጉ አእምሮ ነው።
4, እጅግ ጥበበኛ የሆነ አእምሮ ምሳ19÷11 "ሰውን ጠቢብ አእምሮው ከቁጣ ያዘገየዋል፥ ለበደለኛውም ይቅር ይል ዘንድ ክብር ይሆንለታል።"
136 viewsሌዊ, 00:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ