Get Mystery Box with random crypto!

የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ከተፈተኑ የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች 84.7% የመውጫ ፈተናውን | Bahir Dar University,Ethiopia

የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ከተፈተኑ የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች 84.7% የመውጫ ፈተናውን በብቃት አልፈዋል

ፈተና ከተሰጠባቸው 79 ፕሮግራሞች ውስጥ 32 ፕሮግራሞች ሁሉንም ማሳለፍ ችለዋል።

ሐምሌ 09/2015ዓ/ም(የውስጥ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን-BDU) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ79 ፕሮግራሞች 3229 ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና በማስፈተን 84.7 በመቶ የማለፊያ በቂ ውጤት አስመዘገቡ።

በመደበኛው መርሐ ግብር ብቻ ፈተናውን ከወሰዱ 2843 ተማሪዎች ውስጥ 89.5 በመቶ ከ>50% ያመጡ ሲሆን ፈተና ከተሰጠባቸው ፕሮግራሞች ውስጥ 32 ፕሮግራሞች 100% ሁሉም ተማሪዎች፣ በ14 ፕሮግራሞች ደግሞ በእያንዳንዱ ፕሮግራሞች 1ተማሪ ብቻ ሲቀር ሁሉም አልፈዋል።

በኤክስቴንሽን መርሐ ግብር 45 ተማሪዎች ተፈትነው 55.3% ፣ በርቀት ትምህርት መርሐ ግብር 305 ተማሪዎች ተፈትነው 43.9 ፣ በክረምት መርሐ ግብር 34 ተማሪዎች ተፈትነው 85.3% ያሳለፈ ሲሆን በሁሉም መርሐ ግብሮች 84.7 የመውጫ ፈተናውን በብቃት አልፈዋል።

ጥራት ላለው ትምህርትና ምርምር አበክሮ የሚሰራው የ60ዓመት ባለፀጋው አንጋፋው ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በዚሁ አጋጣሚ ለተፈታኝ ተማሪዎች፣ ቤተሰቦችና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

እንኳን ደስ አላችሁ!!