Get Mystery Box with random crypto!

በተፈታኝ ተማሪዎች ላይ የትራፊክ አደጋ ደረሰ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጭኖ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

በተፈታኝ ተማሪዎች ላይ የትራፊክ አደጋ ደረሰ

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጭኖ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሲጓጓዝ በነበረ የህዝብ ተሽከርካሪ ላይ የትራፊክ አደጋ ደረሰ፡፡

የትራፊክ አደጋው የደረሰው መስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም በምዕራብ ጎጃም ዞን በሰሜን ሜጫ ወረዳ በአምቦ መስክ ቀበሌ ነው፡፡

መነሻውን ከባህርዳር ወደ ማርቆስ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ተሸከርካሪ እና ከምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጭኖ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ተሸከርካሪ በመጋጨቱ ነው አደጋው የተከሰተው።
የሰሜን ሜጫ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን
ለፈጣን መረጃ የቻናሌ ቤተሰብ ይሁኑ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial