Get Mystery Box with random crypto!

ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲመጡ ተጠየቀ፤ ጥበቃ ይደርግላቸዋ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲመጡ ተጠየቀ፤ ጥበቃ ይደርግላቸዋል ተብሏል
ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክሩ መድረኮች እንዲመጡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ፡፡ ኮሚሽኑ ለሚሳተፉ ታጣቂዎች ጥበቃ እንደሚደረግላቸውም ገልጿል።

የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ሥላሴ፤ ግጭት ሕይወትና ንብረትን ያጠፋል እንጂ ችግርን አይፈታም ሲሉ ገልጸው፤ “ታሪካዊ አጋጣሚ” በሆነው ሀገራዊ ምክክር በመሳተፍ ሐሳብን በማቅረብ መግባባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ኮሚሽነሯ አሁንም ታጣቂዎቹ ወደ ምክክሩ እንዲመጡ በመጠየቅ ሲመጡም ጥበቃ እንደሚደረግላቸው አረጋግጠዋል ተብሏል፡፡

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን ጨምሮ ሌሎች የሲቪክ ድርጅቶች በሀገራዊ ምክክሩ ከመሳተፍ እራሳቸውን አግልለዋል።

የ #ኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ስራ አስፈጻሚ ኪሚቴ አባል የሆኑት ሱልጣን ቃሲም በቅርቡ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረጉት ቆይታ ፓርቲያቸው የኮሚሽኑ ምስራታ ሂደት እና እያከናወነው ያለው ስራ ላይ ቅሬታ እንዳላቸው አስረድተዋል።
Join @ayuzehabeshaofficial