Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቀሲስ በላይ ጉዳይ ከቤተክርስቲያኗ ጋር የሚያገናኘው | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቀሲስ በላይ ጉዳይ ከቤተክርስቲያኗ ጋር የሚያገናኘው ነገር እንደሌለ አስታወቀች
ከሰሞኑ ቀሲስ በላይ መኮንን በሀተኛ ሰነድ 6 ሚሊዮን 50 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገንዘብ ለማዘዋወር ሞክረዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉበት ጉዳይ ከቤተክርትያኗ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር እንደሌለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማስታወቋን ዶቸቬለ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ግለሰቡ በቤተክርስቲያኗ በከፍተኛ ኃላፊነት የሚያገለግሉ ቢሆንም፤ ተጭበርብሯል ከተባለው ሰነድ ጋር ግን ቤተክርስቲያኗን የሚያገናኛት ምንም ነገር እንደሌለ አስታውቃለች፡፡

መምህር ዶ/ር አካለወልድ ተሰማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ፓትሪያርክ ህዝብ ግንኙነት የሚዲያ ክፍል ዋና ኃላፊ “ሊቀ አዕላፍ በላይ መኮንን በህግ ጥላ ስር በዋሉበት ጉዳይ ላይ ቤተክርስቲያን ጉዳዩን የመከታተል ጥረት ላይ ትገኛለች ማለታቸውን  ሸገር ታይምስ ሚዲያ ከዜና ምንጩ ዘገባ ለመመልከት ችሏል።

ኃላፊው “እስካሁን በተደረገው ክትትል “ሊቀ አዕላፍ በላይ መኮንን በህግ ጥላ ስር የዋሉበት ጉዳይ ከቤተክርስቲያናችን ጋር የሚያገናኘው ምንም ጉዳይ እንደሌለና በግል ህይወታቸው ውስጥ የገጠማቸው ነገር እንደሆነ ነው የተረዳነው” ብለዋል።

መምህር ዶ/ር አካለወልድ አክለውም በቀጣይ ጉዳዩ ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ ነገር አለው ወይ? የሚለው በህግ ክፍል በኩል ማጣራት እንዲደረግ ትዕዛዝ መተላለፉንም አመልክተዋል፡፡
Join @ayuzehabeshaofficial