Get Mystery Box with random crypto!

Awolia School

የቴሌግራም ቻናል አርማ awoliaschool5 — Awolia School A
የቴሌግራም ቻናል አርማ awoliaschool5 — Awolia School
የሰርጥ አድራሻ: @awoliaschool5
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.34K
የሰርጥ መግለጫ

የእወሊያ ትምህርት ቤቶች የቴሌግራም ቻናል እና ግሩፕ ስልክ ቁጥር ነው! 0988489131
Awolia Schools
Channel (ቻናል)
👉 t.me/awoliaschool5
Group (ግሩፕ)
👉 t.me/awoliaschool6
ARDO
Channel (ቻናል)
👉 t.me/ardoeth
Group (ግሩፕ)
👉 t.me/ardoethG

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-15 17:13:46 አወሊያ ሙስሊም ት/ቤቶች የ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከዕሮብ ሐምሌ 13/2014 ዓ/ል ይጀምራል፡፡ የምዝገባ ቀናትና ሰዓት ዘውትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡30 - 6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 - 9፡30 ሲሆን ለነባር ተማሪዎች 1. ከሐምሌ 13/2014 እስከ ሐምሌ 30/2014 ያለ ቅጣት 2. ከነሐሴ 01/2014 እስከ ነሐሴ 30/2014 ከ200 ብር ቅጣት ጋር 3. ነባር…
805 viewsKalid Somalew, 14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 16:12:37
ቀን 05/12/2014

በዛሬው ዕለት በአወሊያ መሰብሰቢያ አዳራሽ አዲስ የተመረጡት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚዎች ከአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት መምህራንና ሠራተኖች ጋር የትውውቅና የውይይት ፕሮግራም አካሂደዋል፡፡
በአወሊያ እተሰሩ ያሉ የተለያዩ ስራዎችንም
ጎብኝተዋል፡፡

አወሊያ ት/ቤት ቴሌግራም
t.me/awoliaschool5
1.9K viewsKalid Somalew, 13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 18:15:06
ቀን 04/12/2014

ማስታወቂያ
የደረጃ ተማሪዎችን የነፃ የት/ት ዕድል (Sponsorship) ይመለከታል

የአወሊያ ሙስሊም ሚሲዮን ቁ.1 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2014 የትምህርት ዘመን ከየክፍሉ ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል የተሻለ ውጤት ያስመሰገቡ ተማሪዎችን ማበረታታትና ድጋፍ ማድረግ ለሌላ ተማሪዎች ቀና የፉክክር መንፈስ እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋፅዖ ስላለው የትምህርት ቤቱ መኔጅመንት ኮሚቴ በቀን 28/11/2014 ተወያይቶ ከዚህ በታች ስማቸው የተጠቀሱትን ተማሪዎች ለቀጣይ አንድ አመት ማለትም በ2015 የትምህርት ዘመን በነፃ እንዲማሩ ውሳኔ አስተላልፏል።

የተማሪ ስም ክፍል ውጤት
1.ጃዕፋር ሰኢድ አብዶ 1ኛ 97.9
2.ሁዳ ጀማል ወርቁ 2ኛ 97.3
3.መርየም መሀመድ 3ኛ 99.4
4.ሱመያ አስማማው 4ኛ 98
5.መሀመድ አሚን 5ኛ 99
6.ኢክራም አ/ረህማን 6ኛ 96
7.ዛኪር አብደላ 7ኛ 96.6


አወሊያ ት/ት ቤት ቴሌግራም
t.me/awoliaschool5
1.9K viewsKalid Somalew, 15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 18:57:54
ቀን 30/11/2014

ማስታወቂያ
የደረጃ ተማሪዎችን የነፃ የትምህርት ዕድልን ይመለከታል!

የአወሊያ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ት ቤት በ2014 የትምህርት ዘመን በየክፍሉ ከሚማሩ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ማበረታታትና ድጋፍ ማድረግ ለሌሎች ተማሪዎች ፉኩክር እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋፅዖ ስላለው የትምህርት ቤቱ የማኔጅመንት ኮሚቴ በቀን 28/11/2014 በተወያየው መሰረት ከዚህ በታች ስማቸው የተጠቀሱት ተማሪዎች ለቀጣይ አንድ ዓመት በ2015 የት/ት ዘመን በነፃ እንዲማሩ ውሳኔ አስተላልፋል።

የተማሪ ስም ክፍል ውጤት
1 አ/ከሪም ሁሴን 8ኛ 97.5
2 ሃፍሳ ሁሴን 9ኛ 95.79
3 ሂክማ ሱዓዱ 9ኛ 95.79
4 ሩመይሷ አ/ሰላም 10ኛ 97.58
5 ኢክራም ሀሩን 10ኛ 96.63
6 ኼይሪያ ሱዓዱ 10ኛ 96.29
7 ሂክማ ያሲን 11ኛ 95.95


ትምህርት ቤቱ

አወሊያ ት/ት ቤት ቴሌግራም
t.me/awoliaschool5
1.2K viewsKalid Somalew, 15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 18:09:39
#National_Exam

የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ/ል ጀምሮ ይሰጣል።

ፈተናው ከመስከረም 30/2015 ዓ/ል ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የፈተና ደንብ ጥሰቶች #በህግ ያስጠይቃሉም ተብሏል።

የ2014 ዓ/ል ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ከመስጠት ባለፈ የፈተና ኩረጃ እና ስርቆትን ለመከላከል በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ከቀናት በፊት መገለፁ ይታወሳል።

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው እንደነበር አይዘነጋም።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ ሲሆን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን ለማድረግ የታሰበ ነው።

የትምህርት ምዘና ፈተናዎች አገልግሎት

አወሊያ ት/ት ቤት ቴሌግራም
t.me/awoliaschool5
942 viewsKalid Somalew, 15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 07:47:50
የሱቅ የጨረታ ማስታወቂያ


ቦታው: አወሊያ ዋናው ግቢ


የአወሊያ ት/ት ቤት ቴሌግራም
t.me/awoliaschool5
960 viewsKalid Somalew, edited  04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 07:47:21
የጨረታ ማስታወቂያ!

ለአወሊያ ካፌ!

ቦታው: አወሊያ ዋናው ግቢ

የአወሊያ ት/ት ቤት ቴሌግራም
t.me/awoliaschool5
898 viewsKalid Somalew, edited  04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 21:45:58 አወሊያ ሙስሊም ት/ቤቶች
የ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከዕሮብ ሐምሌ 13/2014 ዓ/ል ይጀምራል፡፡

የምዝገባ ቀናትና ሰዓት
ዘውትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡30 - 6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 - 9፡30 ሲሆን

ለነባር ተማሪዎች
1. ከሐምሌ 13/2014 እስከ ሐምሌ 30/2014 ያለ ቅጣት
2. ከነሐሴ 01/2014 እስከ ነሐሴ 30/2014 ከ200 ብር ቅጣት ጋር
3. ነባር ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ 1 ጉርድ ፎቶና ሪፖርት ካርድ(ሰርተፌኬት) ይዘው መምጣት አለባቸው፡፡

ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች
ለጀማሪ (ነርሰሪ) የኬጂ ተማሪዎችና ለ1ኛ ክፍል ከሐምሌ 13/2014 ጀምሮ
ለሌሎች ክፍሎች ከሐምሌ 25/2014 እስከ ነሐሴ 30/2014
ለክልላዊ ፈተና ተፈታኞች ውጤት ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ

ለአፀደ ህፃናት አዲስ ተማሪዎች በምዝገባ ጊዜ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
ዕድሜያቸው 4 ዓመት የሞላ
የልደት(የክትባት) ሰርተፊኬት ዋናውን እና ኮፒ
የተማሪው ሁለት ጉርድ ፎቶ-ግራፍ
የወላጅ አንድ ጉርድ ፎቶ-ግራፍ
አንድ ክላሰር

ከአፀደ-ህፃናት ውጪ ላሉ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በምዝገባ ጊዜ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
አማካይ ውጤት 65 እና ከዛ በላይ
ያላቋረጠና ያልደገመ፡፡
ሲማር ከነበረበት ት/ቤት በዲሲፒሊን ግድፈት ያልተባረረ መሆኑንና ጥሩ ስነ-ምግባር ያለው ስለመሆኑ የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
መሸኛና ሌሎች የትምህርት ማስረጃዎችን አሟልቶ ማቅረብ የሚችል
ት/ቤቱ ያዘጋጀውን የመግቢያ ፈተና ያለፈ
የተማሪው ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ
የወላጅ አንድ ጉርድ ፎቶግራፍ
አንድ ክላሰር

ለቅናሽ ክፍያ የሚያበቁ መስፈርቶች
የዓመቱን ክፍያ በአንድ ጊዜ ለሚከፍሉ 10 % ቅናሽ
በት/ቤቱ ውስጥ 3 ልጅ ለሚያስተምሩ ለአንድ ልጅ 20% ቅናሽ
በት/ቤቱ ውስጥ 4 ልጅ ለሚያስተምሩ ለአንድ ልጅ 30% ቅናሽ
በት/ቤቱ ውስጥ 5 ልጅ ለሚያስተምሩ ለአንድ ልጅ 50% ቅናሽ
6 እና ከ6 ልጅ በላይ ለሚያስተምሩ 1 ልጅ በነፃ

የምዝገባ ቦታዎች
ዊንጌት አልፎ አስኮ መንገድ ላይ በሚገኘው አወሊያ ግቢ (ከአፀደ-ህፃናት አስከ መሰናዶ)
አወሊያ ቁ.1 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፒያሳ ቅርጫፍ (ከ1ኛ - 8ኛክፍል)
አወሊያ ቁ.2 ት/ቤት ዘነበ ወርቅ ቅርንጫፍ (ከአፀደ-ህፃነት እስከ 10ኛ ክፍል)

ማሳሰቢያ
1. በምዝገባ ወቅት የመመዝገቢያና የመስከረም ወር ወርሃዊ ክፍያ እና የመማሪያ መጽሃፍ ግዢ ክፍያ በሙሉ መፈጸም ይኖርበታል፡፡
2. ት/ቤቱን ለመልቀቅ መሸኛ የሚጠይቁ ወላጆች ከሐምሌ 15/2014 እስከ ሐምሌ 30/2014 ድረስ 100 ብር በመክፈል መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ከነሐሴ 01/2014 ጀምሮ ደግሞ 300 ብር ቅጣት በመክፈል መልቀቂያ እንዲወስዱ ይደረጋል፡፡
3. ዩኒፎርም
ለሴቶች ጥቁር በ “A Shape” የተሰፋ፣ ስፌት የማያጣብቅ እና ጉርዱ ቁርጭ ጭሚት ድረስ የረዘመ መሆን አለበት፡፡
ለወንዶች ጠባብ(ቃሪያ/ስኪኒ) ያልሆነና የእግሩ ስፋት 18 ሳ.ሜ መሆን አለበት፡፡

ለበለጠ መረጃ
ቀጥሎ ባሉት ስልክ ቁጥሮች ይደውሉ
አስኮ አወሊያ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል
(09 13 85 84 32 / 09 13 12 51 46)
አስኮ አወሊያ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ
(09 11 74 60 21 / 09 24 55 58 71)
ፒያሳ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል
(09 14 50 01 16 / 09 20 51 67 23)
ዘነበ ወርቅ ከኬጂ እስከ 10ኛ ክፍል
(09 13 08 77 75 / 0913 02 48 14/ 09 12 48 93 97)
አስኮ አወሊያ አፀደ-ህፃናት
(09 13 49 18 48/ 0912 44 86 90)

የምዝገባ ክፍያ
1. ለነባር ተማሪዎች መመዝገቢያ 250 ብር
2. ለአዲስ ተማሪዎች መመዝገቢያ 250 ብር
3. ከት/ቤቱ መልቀቂያ ለሚወስዱ ተማሪዎች (ያለ ቅጣት) 100 ብር
4. ከት/ቤቱ መልቀቂያ ለሚወስዱ ተማሪዎች (በቅጣት) 300 ብር
5. ለመግቢያ ፈተና መውሰጃ 50 ብር

ወርሃዊ ክፍያ
1. ለአፀደ ህፃናት (አስኮ ቅርንጫፍ) 1000 ብር
2. ከ1ኛ አስከ 4ኛ ክፍል (አስኮ እና ፒያሳ ቅርንጫፍ) 900 ብር
3. ከ 5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል (አስኮ እና ፒያሳ ቅርንጫፍ) 950 ብር
4. ከ 9ኛ እስከ 10ኛ ክፍል (አስኮ ቅርንጫፍ) 1000 ብር
5. ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል (አስኮ ቅርንጫፍ) 1050 ብር
6. ለአፀደ ህፃናት (ነስር ቅርንጫፍ) 950 ብር
7. ከ1ኛ አስከ 4ኛ ክፍል (ነስር ቅርንጫፍ) 850 ብር
8. ከ 5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል (ነስር ቅርንጫፍ) 900 ብር
9. ከ 9ኛ እስከ 10ኛ ክፍል (ነስር ቅርንጫፍ) 950 ብር

አወሊያ ት/ቤት ቴሌግራም
t.me/awoliaschool5
1.5K viewsKalid Somalew, 18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 10:56:50
ቀን 25/11/2014

ማስታወቂያ
ለ9ኛ ክፍል ነባር እና አዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች በሙሉ

የ2015 የትምህርት ዘመን ለ9ኛ ክፍል ነባር እና አዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ ከታች የተጠቀሰውን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
1. የተማሪው የሚኒስትሪ ካርድ (ሰርተፊኬት)፡፡
2. ተማሪ እና ወላጅ ግዴታ መምጣት አለባቸው፡፡
3. የተማሪ 2 ጉርድ ፎቶ እና የወላጅ 1 ጉርድ ፎቶ፡፡

ማሳሰቢያ
- ለነባር ከ8ኛ ወደ 9ኛ ክፍል ያለፋችሁ ተማሪዎች ምዝገባ እስከ ነሐሴ 14/2014 ሲሆን ከዚያ ብኋላ የሚመጣ ተማሪ በቅጣት ስለሆነ እንዲሁም በአዲስ ተመዝጋቢ ተማሪ በምትኩ ስለምንመዘግብ ከወዲሁ እንድትመዘገቡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

ት/ቤቱ

አወሊያ ት/ት ቤት ቴሌግራም
t.me/awoliaschool5
1.9K viewsKalid Somalew, 07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 09:23:46 ምዝገባ በአወሊያ ት/ት ቤቶች

የ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከዕሮብ ሐምሌ 13/2014 ዓ/ል መጀመሩ ይታወቃል፡፡
ስለሆነ ያልሰማችሁ ሁሉም ት/ት ቤቶች ምዝገባ ላይ መሆናቸውን በድጋሚ ለማሳወቅ ነው።

የምዝገባ ቀናትና ሰዓት
ዘውትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡30 - 6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 - 9፡30 ሲሆን

ለነባር ተማሪዎች
1. ከሐምሌ 13/2014 እስከ ሐምሌ 30/2014 ያለ ቅጣት
2. ከነሐሴ 01/2014 እስከ ነሐሴ 30/2014 ከ200 ብር ቅጣት ጋር
3. ነባር ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ 1 ጉርድ ፎቶና ሪፖርት ካርድ(ሰርተፌኬት) ይዘው መምጣት አለባቸው፡፡

ት/ት ቤቶቹ


አወሊያ ት/ቤት ቴሌግራም
t.me/awoliaschool5
1.3K viewsKalid Somalew, edited  06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ