Get Mystery Box with random crypto!

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ ***** በፊልም ሥራዎቹ ብዙዎች ዘን | " አውደ ገሀድ "

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
*****

በፊልም ሥራዎቹ ብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን እና ዝናን ያተረፈው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ወጣቱ የፊልም ባለሙያ ባደረበት ሕመም ለሳምንታት በሕክምና ሲረዳ ቢቆይም ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል።

አርባ ያህል ፊልሞች ላይ የተወነው አርቲስት ታሪኩ በሕመም ምክንያት ሕይወቱ ማለፉን ኢፕድ ከአርቲስቱ የቅርብ ሰዎች ማረጋገጡን ዘግቧል።

አርቲስቱ ወጣት በ97፣ ወንድሜ ያዕቆብ፣ ላውንድሪ ቦይ፣ ማርትሬዛ፣ ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2፣ ሞኙ የአራዳ ልጅ 4፣ አንድ ሁለት፣ ብር ርርር፣ ወደው አይሰርቁ፣ ወፌ ቆመች፣ እንደ ቀልድ፣ ወቶ አደር፣ አባት ሀገር እና ሌሎችም ፊልሞች ላይ ተውኗል።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ የአንድ ልጅ አባት ነበረ።

ለመላው አድናቂዎቹ በሙሉ "አውደ ገሀድ" መፅናናትን ይመኛል።
.
.
.
.
.
ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻችሁን ለመጋበዝ
  @Awede_gehad
  @Awede_gehad