2022-12-11 18:04:13
#ሚስትን_መምታት_
እናንተ ወንድሞቼ ሆይ ሴትን መግረፍ (አግባብ በሆነ መልኩ) የተፈቀደ ቢሆንም የተመሰገነ ግን አይደለም።
አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና (የነብያችን ባለቤት) አዒሻ እንዲህ ትላለች የአላህ መልእክተኛ አንድም ቀን ሴትም ሆነ ኻድም መትተው አያውቁም። በራሳቸው ጉዳይም ሰዎችን ተበቅለው አያውቁም። የአላህ ህግ ስትነካ ሲቀር እንጅ የአላህ ህግ ስትነካ ግን ለአላህ ብለው ይቆጣሉ/ ይበቀላሉ። ከምርጥ ወንዶች፣ ከትልልቅ ወንዶች፣ ከፍ ካሉ ወንዶች፣ ከአቅለኛ ወንዶች ዘንድ ሴትን መምታት የተጠላ ነገር ነው።
(እንደ ሁኔታው በአግባቡ) ሴትን መግረፍ የተፈቀደ ከመሆኑም ጋር ግን ነብያችን እንዲህ አሉ:- ከናንተ አንድኛችሁ ልክ ባሪያውን እንደሚታው አድርጎ ሚስቱን አይምታት!! ከዛ (እንደት) አልጋው ላይ ይገናኛታል!!
ነብያችን (ዓለይሂ ሶላቱ ወሰላም) ከዚህ አይነት የሚቀፍፍ ፀባይ አስጠንቅቀዋል።
የተፈቀደ በሆነው መልኩ ሚስት ስርአት እንድትይዝ የምትቀጣበት መንገድ:-
{{እነዚያንም ማመጸቸውን የምትፈሩትን ገስጹዋቸው፡፡ በመኝታዎችም ተለዩዋቸው፡፡ (ሳካ ሳታደርሱ) ምቱዋቸውም፡፡ ቢታዘዟችሁም (ለመጨቆን) በእነርሱ ላይ መንገድን አትፈልጉ፤ አላህ የበላይ ታላቅ ነውና፡፡}} ኒሳእ/34
(አላህ) መግረፍን የመጨረሻ መድኃኒት ነው ያደረገው። ይሄ መግረፍ የተባለው ራሱ ከዑለሞች ዘንድ ሁኔታ/ መስፈርት አስቀምጠውለታል። በእጅ መዳፍ (በጥፊ) መምታት እንጅ አጥንት የሚሰብር፣ ሰውነት የሚያቆስል መሆን የለበትም። ፊትንም መምታት ነብያችን ከልክለዋል።
ሸይኽ ሙሀመድ ሀዲ አል መድኸሊ (ሀፊዘሁላህ)
የሚገርመው ግን እንደተለምዶ ሁኖ ሴትንማ ሲያቸናጓት/ሲያጠናግሯት ነው እንጅ የሚሉ ሰዎችን ማየት ያሳዝናል።
https://t.me/Aumu_Salihat
አብዱረህማን ዑመር
https://t.me/Aumu_Salihat
511 viewsኒቃቤን ከጠላህ እንዳድርስ ከዳጄ! "ሞትን አዘውትራችሁ አስታውሱ። , edited 15:04