Get Mystery Box with random crypto!

ልናውቃቸው የሚገቡ ጠቃሚ ነጥቦች •════••• •••════• ➀➛  ተውራት የወረደው ለነብዩላህ | 🌸 🇸🇦የሱኒዮች ቻናል ቅድሚያ ለታዉሂድ 🇸🇦🌸

ልናውቃቸው የሚገቡ ጠቃሚ ነጥቦች
•════••• •••════•

➀➛  ተውራት የወረደው ለነብዩላህ ሙሳ ነበር።
➁➛ ኢንጂል የወረደው በነብዩላህ ኢሳ ዐ.ሰ ላይ ነበር።
➂➛ ዛቡር የወረደው በነብዩላህ ዳውድ ዐ.ሰ ላየ ነበር።

➃➛ አላህ ሱ.ወ ለሶዶማውያን የላከው ነብይ ነብዩላህ ሉጥ ዐ.ሰ ነበር።
➄➛ ነብዩላህ ሉጥ ዐ.ሰ የአናጢነት ሙያ ባለቤት ነበሩ።

➅➛ ነብዩላህ ሙሳ ዐ.ሰ እረኛ ነበሩ።
➆➛ ነብዩላህ ኢብራሂም ዐ.ሰ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰይፍ የተዋጉ ነብይ ነበሩ

➇➛ ነብዩላህ ሱለይማን ዐ.ሰ ለመጀመሪያ ጊዜ بسْـــــــــــــــــــمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيْم ብለው የፃፉ ነብይ ናቸው።

➈➛ነብዩላህ ኢብራሂም ዐ.ሰ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢስላም ብለው የተሰደዱ ነብይ ናቸው።

➉➛ነብዩላህ ሱለይማን ዐ.ሰ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳሙናን የተጠቀሙ ነብይ ናቸው።

⓫➛ነብዩላህ ኢሳ ዐ.ሰ ለመጨረሻው ወደ እስራኤል ልጆች የተላኩ ነብይ ናቸው።

⓬➛ነብዩላህ አደም ዐ.ሰ ወደ መሬት ከመውረዳቸው በፊት በጀነት ይኖሩ ነበር።

⓭➛ነብዩላህ አዩብ ዐ.ሰ ለረጅም ጊዜያት በህመም ሲሰቃዩ ኖረዋል።
⓮➛የነብዩላህ ዩሱፍ ዐ.ሰ ልብስ ታሪክ በቅዱስ ቁርአን ተገልፃል።

⓯➛የብዩላህ አደም ዐ.ሰ የተፈጠሩት በጁመዓ ቀን ነበር።
⓰➛ነብዩላህ ኢብራሂም ዐ.ሰ የተቀበሩት በፊልሰጤም አል ኻለል በተባለች ቦታ ነው።

⓱➛አላህ በድምፅ ብቻ ከሁለት ነብያቶች ጋር አውርቷል። እነሱም ነብዩላህ ሙሳ ዐ.ሰ እና ነብዩ ሙሀመድ ﷺ ናቸው።

⓲➛124,000 ነብያቶች ወደ ሰው ልጆች ተልከዋል።

⓳➛ሚና ከተማ በምስራቅ አቅጣጫ ከመካ በ3 ማይል ርቀት ላይ የምትገኝ በረሃማ ቦታ ስትሆን ከሐጅ ስርዓቶች አብዛኛው የሚከናወነው በዝችው በረሃማ ከተማ ሚና ላይ ነው።

⓴➛ቁርአን በአለም ለይ በ103 ቋንቋዎች ገደማ ተተርጉሟል።

➁➀➛የኮሙኒዝም ስርዓት በተፈጥሮ ሃይማኖትን ይቃወማል በተለይም እስልምናን

➁➁➛የመጀመሪያው ኃጢያት (ወንጀል) ኩራት ነው። እሱም በሰይጣን (ኢልቢስ) ነው የተፈፀመው።

➁➂➛በፍርድ ቀንየሚጠየቀው የመጀመሪያ ጥያቄ "ሰላት" ነው።
➁➃➛አንዲት ሴት ባለቤቷ ከሞተ በኃላ ትዳር ለመመስረት 4 ወራት ከ10 ቀናት መቀመጥ ይኖርባታል። ከዚያ በኃላ አዲስ ትዳር መመስረት ትችላለች

➁➄➛አብደላህ እና አብዱረህማን ተመራጭ የኢስላም ስሞች ናቸው። ሙሀመድ የሚለው ስም በአለም አንደኛው ስም ነው።

➁➅➛ጀነት በጣም ጥልቅና እጅግ በጣም ሰፊ ከመሆኗ የተነሳ ስፋቱ በሰዎች ሊደረስበት አይችልም።

➁➆➛ሰዎች በጀነት ውስጥ ምን እንደሚመስሉና ምን እንዳለ ቢያውቁ ኖሮ በዚህ ዱንያዊ ኑሮ አይደሰቱም ነበር

➁➇➛የፈርዖን ሚስት የሆነችው አስያ በተትረፈረፈ ጀነት ውስጥ ትሮራለች፤ ባለቤቷ ፈርዖን ደግሞ በጀሃነም ለዘላለም ይኖራል።

➁➈➛ አልይ ረ.ዐ በኢስላም የመጀመሪያው እስር ቤት የገነቡ ሰው ናቸው።
➂Ⓞ➛ዑመር ረ.ዐ በኢስላም የመጀመሪያውን ደብዳቤ ስርዓትን የተጠቀሙ ሰው ናቸው።

➂➀➛ዑመር ረ.ዐ በኢስላም የመጀመሪያውን የሂጅራ ካላንደር የፃፉ ሰው ናቸው።
➂➁➛አጅማዕ ማለት ኡለሞች የተስማሙበት ማጣቀሻ ነው።

➂➂➛የእስልምና ህግ (ህገ-መንግስት) ሸሪዓ ይባላል።
➂➃➛የኢደል ፊጥረ በአል የሚከበረው በሸዋል ወር ውስጥ ነው።

➂➄➛የኢደል አድሃ (አረፋ) በአል የሚከበረው በዙለሂጃ ወር ውስጥ ነው

➂➅➛የኢድ ሰላት ሁለት ረካዓ አሉት። የመጀመሪያው ረከዓ 7 ተክቢራ፤ ሁለተኛው ደግሞ 5 ተክቢራ አለው

➂➆➛ረመዳን በሂጅራ አቆጣጠረ 9ኛው ወር ነው።
➂➇➛ሙሃረም በሂጅራ አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር ነው።

➂➈➛ለይለቱል ቀድር በረመዳን ወር እንደምትገኘ ገልፆዋል።
➃Ⓞ➛ሽርክ አላሀ ሱ.ወ ይቅር የማይለው ወንጀል ነው።

➃➀➛የደጃል መምጣት ከየውመል ቂያማ ምልክቶች ትልቁ ነው።
➃➁➛አቂቃ ማለት አዲስ ልጅ ሲወለድ በመሰዋትነት መልኩ የሚቀርብ እንስሳ ነው።
➃➂➛ዚክር (አላህ ሱ.ወ ማውሳት) ማለት ሲሆን በልብም በምላስም የሚተገበር ነው።
➃➃➛ዱዓ ማለት አላህ ሱ.ወ አላህ ሱ.ወን የሚፈልጉትነ ነገር መለመን ማለት ነው።

➃➄➛ታማኝ ምንጭነታቸው ከተረጋገጡት ውስጥ ሰሂህ አል ቡኻሪ እና ሙስሊም ዋናዎቹ ናቸው።

➃➅➛ኢህራም ማለት አንድ ሰው ሀጅ ወይም ኡምራ ለማድረግ መነየት ነው

➃➆➛ኢስቲንጃ ማለት ራስን ከቆሻሻ (ነጃሳ) ነገር በንፁህ ውሃ ወይም አፈር መፀዳዳት ነው።

➃➇➛ተቅዋ ማለት የአላህን ሱ.ወ መፍራት ሲሆን እሱ ያዘዘውን መስራት፤ እሱ የከለከለውን መራቅ ማለት ነው
➃➈➛ጠዋፈ ማለት የአላህን ሱ.ወ ቤት (ካባን) 7 ጊዜ መዞር ነው።

➄Ⓞ➛በመስጂደ ሀረም(መካ) መስገድ የ100,000 ደረጃ ያህል ከሌሎች መስጂዶች በለጨ ነው።

➄➀➛በመስጂደል ነበዊ (መዲና) መሰገድ የ1000 ደረጃ ያህል ከሌሎች መስጂዶች ይበልጣል።

➄➁➛የውሙል ቂያማ ቀን የሚውለው በአርብ (ጁመዓ) ቀን ላይ ነው።
➄➂➛የጀነት በር የሚከፈተው በነብዩ ሙሀመድ ﷺ ነው።

➄➃➛ህፃናት፣ ባሪያዎች፣ በሽተኞች፣ ሴቶች  እና መንገደኞች የጁመዓን ሰላት  መስገድ አይገደዱም።

➄➄➛አንድ ሙስሊም ትዳር ለመመስረት 2 ምስክሮች ያስፈልጉታል።
➄➅➛ሎተሪ በኢስላም አይፈቀድም።

➄➆➛በወርቅ፣ በብር ላይ መብላት (መጠጣት) ሃራም ነው።
➄➇➛በኢስላም ብድር ይፈቀዳል። ነገር ግን   ወለድ ካለው ሃራም ነው።

➄➈➛አንዲት ሴት ባሏ ከሞተባት የሚፈቀድላት 1/8ኛውን(አንደ ስምንተኛውን) ብቻ ነው።

➅Ⓞ➛ተይሙም ካደረጉ በኃለ ውሃ ሲገኝ ተይሙም ይበላሻል።

➅➀➛በአጋጣሚ አንድ ሰው ካስመለሰው ፆሙ አይበላሽም።

➅➁➛ለመንገደኛ ፆም ለመፆም አይገደድም።

➅➂➛ሴቶች የውበት ጌጣ ጌጦችን
መጠቀም ይችላሉ።

➅➃➛ኮከብ ማስቆጠርም ሆነ መቁጠር በኢስላም ሃራም ነው።


  ሸር በማድረግ ለሌሎችም ያድርሱ

የቴሌግራም ቻናሉን ተቀላቀሉ
  
የሱና ኡስታዞች ደዕዋ አጫጭር ቲላዋ ጣቀሚ ምክሮች እንዲውም የተላያዩ የምክር ፁሁፎች ይላቀቁበተል ኢንሻአላህ ተውሂድ የበላይ ይሆናል
قال النبي ﷺ :- « مَنْ سَلَكَ طَرِيقًا يَلْتَمِسُ فِيهِ عِلْمًا،
سَهَّلَ اللهُ لَهُ طَرِيقًا إِلَى الْجَنَّة ».
የሱኒዮችየቴሌግራም ቻናል ይቃለቃሉ
https://t.me/Aumu_Salihat