Get Mystery Box with random crypto!

የ እናቴ ልጅ ክፍል ሦስት . ከቤት ወጥቼ ሰፈር ውስጥ ከሚገኝ አንዲት አነስ | አትሮኖስ

የ እናቴ ልጅ
ክፍል ሦስት .

ከቤት ወጥቼ ሰፈር ውስጥ ከሚገኝ አንዲት አነስተኛ ሱቅ ጋር ቆምኩኝ ፣ የሱቁ ባለቤት ልጅ ፣በድሪያ ትባላለች ፣ ፈራ ተባ እያለች " ምን ልስጥህ "አለችኝ ዝምብዬ ሳያት ወደዋላዋ አፈግፍጋ ቆመች ልጅ ናት የቀድሞ በጥባጭነቴ እሷም ጋር ተፅህኖ ሳያሳርፍ አይቀርም "እ ብስኩት ስጪኝ ካፒችኖ አለሽ "አልኳት በጨዋ ደንብ "አለኝ "ብላ ሰጠችኝ ብሯን ከፍያት ፣ልሄድስል ከኛ ጊቢ እልፍ ብለው የሚኖሩ ሴት ቀስ እያሉ መጥተው ቆሙ እናም ወደኔ በመዞር "ናቲ እንዴት አደርክ "አሉኝ ከዚ በፊት አናግረውኝም ሆነ ስሜን ጠርተውኝ ስለማያውቁ ደንገጥ አልኩ በዝምታ ሳያቸው "ምነው ናታን የእግዜር ሰላምታ እኮ አይከለከልም "አሉ ለስለስ ብለው
"አይ እኔ ከዚበፊት አናግረውኝ ሰለማያውቁ ገርሞኝ ነው "አልኳቸው በግልፅ
"አሂሂሂ መቼስ ልባችን ቢፈልግስ በየት በኩል እናንተ ከሰው አትቀርቡ ፣ለነገሩ ችግሩ የእናንተም አይደለ እናታቹ ናት እንጂ እንዳትቀርቡ ያደረገች እናንተማ ያው ልጆች ናቹ የተመራችሁትን ነው "ብለው ሽሙጥ መሰል ነገር ተናገሩ ፣ዝምብዬ አየዋቸው እንደ እውነቱ ከሆነ እማማ ሸዋዬ ትልቅ ሰው ባይሆኑ በናቴ የመጣ ቱግ ባልኩ ነበር "እማማ እሺ አሁን ሰላም ይዋሉ "ብዬ መንገድ ልጀምር ስል "ቆይ ቆይ እንደው መጀመሪያ ለደናደርኩ ' ደና ይመስገን ነው መልሱ እእእ የሆነስ ሆነና እኔስ ድንገት ሳገኝህ በውስጤ የሚመላለስ ነገር ነበርና ስለ እናንተ ቤተሰብ ላናግርህ ነበር መቼም አንተ በክፉም ሆነበደግ ታገናኘን ነበር ፣"አሉ
እኚሴቲዮ እየተፈታተኑኝ ነው ግን ትህግስት ላድርግ ብዬ "እሺ ቶሎ ይበሉና ይንገሩኝ"አልኳቸው ወደበድርያ ሳይ የጨነቃት ይመስላል እጇን ታፍተለትላለች ድንቡሽቡሽ ቀይ ፊቷ ያሳዝናል ፣ወደ እማማ ሸዋዬ አተኮርኩ መልሼ
"እኔማ ምን መሰለህ መቼም እዝች ምድር ላይ በሕይወት ስትኖር ክፉ ደግ አለ እንዳማሩ ዘላለም አይኖርም ደስታም እንዳለ አዘን አለ ማገኘትም ማጣትም እንደዛው ፣ እና ከሰው ተለይቶ ምንም ነገር አይሆንም ምንድነው ሁልጊዜም ስለ እናንተ ሳስብ ምንም ብትሆኑ ለኔ ይጨንቀኛል ፣እነዚ ልጆች እናታቸው አንድ ነገር ብትሆን እድር የለ ምን የለ ከሰው አይግባቡ እላለው እንደው በሌላ ነገር አትይብኝ እና ሰው ነንና ነገ ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም ናቲዬ አይለኛም ብትሆን አንተን ማናገር ለኔ ይቀለኛል ፣ እስኪ አንተ እናትህን እንደምንም ጨቅጭቀ የሰፈሩን እድር እንድትገባ አድርጋት ከሰው ቀስ በቀስ ትቀላቀል "አሉ መጀመሪያ ስላሟረቱብን ውስጤ ደስ ባይለውም የተናገሩት ነገር ከምር አሳሰበኝ ፣ እውነት አንድነገር ቢፈጠር አይበለውና ሆሆሆ እማማ ሸዋዬ ጭንቀት ፈጠሩብኝ
"እእእ እውነት ነው እማማ ልክ ነዎት አናግራታለው ለመልካም አሳቦት አመሰግናለው "ብያቸው ነገር ከመቀጠላቸው በፊት ፈጠን ብዬ ተራመድኩ
"ሰው ነው ብዬ ቀውስ..."ሲሉ ትንሿ በድሪያ ስትስቅ ሰማዋት "አንቺ ደሞ ጥርስሽ ይርገፍ ሻማ ስጪኝ አሁን "ብለው የውሸት እርግማን ሲያወርዱባት ፣ስትስቅ ሳልወድ በግድ ፈገግ እያልኩ ለራሴ የገዛውትን ካፒቺኖ ጨምድጄ እንደያዝኩ ሰፈሩን ለቅቄ ሌላቦታ ለመዋል ፈጠንኩ ፣ወይ እማዬ,,,,,..ኀ
እሷ እንደው ከማንም ጋር ምንም ነገር ለመነጋገር ፍላጎቱም ስሜቱም የላት እና እኔ ምን ማድረግ እችላለው ፣ በተለይ በአሁን ጊዜ ከወንድሜ አቤል በስተቀር ሰውም የላት እሱ ሁሉ ነገሯ ሆኗል አማካሪዋ መልህክተኛዋ አዛኟ ተንከባካቢዋ ...እኔን ማቅረብ በጭራሽ አትፈልግም ኧረ እሱም አልፈቀደልንም ፣አንዳንዴ እልም ብዬ ብጠፋስ እላለው እውነት ያን ያክል ለነሱ ችግር ከሆንኩ ።ሌላ ቦታ ሄጄ እራሴን ልፈትን ብዬ አስባለው የእናቴ በሚስጥር የተሞላ ሕይወት እና የታናሽ ወንድሜ እኔላይ ያለው ጥላቻ መጨመር እያሳሰበኝ መጥቷል ለምን ይሆን?,,,,,,

ደራሲ unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj