Get Mystery Box with random crypto!

#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ሰባት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ‹‹ከምን ያህል | አትሮኖስ

#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹ከምን ያህል የጊዜ ደንዛዜ ውስጥ እንደቆየች አታውቅም .የሳሎኑ በራፍ ተበርግዶ ሲከፈት ነው ከሀሳቧ ውስጥ በመከራ የወጣችው…ጊፍቲ ከፊት መድህኔ ከኋላ እያለከለኩ ተከታትለው ገቡ
በመጠጥ ተዳክሞ በተቆላለፈ አንደበቷ ‹‹ነይ እንጂ ኑ ብያለሁ››አለቻት..ያልጠበቀችን እና ከነመፈጠሩም ጭሩሱኑ ረስታው የነበረውን መድሀኔን ስታየው ብሶቷ በእጥፍ ጨመረባት፡

ጊፊቲም በራሷ ድንጋጤ ላይ ስለሆነች እሷ የምትለውን እየሰማቻት አይደለም..ጥያቄዋን አዥጎደጎደችው‹‹እንዴ ምን ተፈጥሮ ነው…?ቃልዬ የት አለ….?አመመው እንዴ….?››ተንደርድራ አልፋ የመኝታ ቤቱን በራፍ ከፈተችና ወደ ውስጥ አየች… ባዶ መሆኑን ስታይ ወደ ልዩ ተመለሰችና‹‹…ልዩ ንገሪኝ እንጂ…ተጣልታችሁ ነው….?አሁን እሱ የት ሄደ?››
ዝም ብላ አየቻት..ሆዷ ወደፊት እየገፋ ነው…በሶስት ወር ፣‹‹እንዲህ ያስታውቃል እንዴ…?››ስትል አሰበች ግራ ከመጋባቷ የተነሳ የማያሳስበው እያሳሰበት ነው፡፡መድህኔ እጁን በደረቱ ላይ አጣጥፎ ግራ በማጋባት ዝምብሎ ቁልቁል እያየት ነው፡፡አሳዝናዋለች.በጣም ነው ያሳዘነችው..ስሯ ተንበርክኮ ወደደረቱ አስጠግቶ እቅፍ አድርጎ ቢያፅናናት ደስ ይለዋል.ግን እንደዛ ማድረግ አይችልም…
‹‹ልዩ አረ በፈጠረሽ …አናግሪኝ በጭንቀት ልፈነዳልሽ ነው?››አለች ጊፊቲ
‹‹ቃል ከዛሬ ጀምሮ የለም››
‹‹የለም ማለት ምን ማለት ነው?››
‹‹መልሱ መኝታ ቤት ግቢና አልጋው ላይ አለልሽ››
ከተንበረከከችበት ተነስታ ተንደርድራ ወደመኝታ ቤት ስትገባ መድህኔ ‹‹ልጄን…›› አለ .አንድ ነገር እንዳይሆንበት የተሳቀቀ በሚመስል ሰውነቱን አሸማቆና ፊቱን አጨማዶ‹‹አረ ማሬ ቀስ በይ..ቀስ…..››
ፖስታውን በእጇ እያገላበጠች ተመልሳ መጣች፡፡‹‹የመጨረሻ ስንብት ማለት ምን ማለት ነው? ››ተንዘረዘረችባት
‹‹ወይዘሮ ጊፍቲ ብታነቢው እኮ የምትፈልጊውን  መልስ  ከውስጡ ታገኚያለሽ..››
ከፈተችውና ማንበብ እንደጀመረች እንደማዞር አደረጋት ፡፡ ተንገዳገደች….ተንደርድሮ ሄደና ክንዷን ያዛት …መድህኔ የልዩ የድሮ ፍቅር …ቃልን የማታገኝ መስሏት ለሌላ ሴት አሳልፋ የሸለመችው የልጅነት ጓደኛዋ …የረጅም ዘመን ፍቅረኛዋ… እየጎተተ ወሰዳትና  ወንበር ላይ አስቀመጣት፡፡ ለማንኛውም ብሎ ልክ እንደባለስልጣን ጋርድ ከጎኗ በተጠንቀቅ ቆመ ..እንደምንም ብላ ማንበቧን ቀጠለች…ልዩም መጠጧን እየሳበች እየተከታተለቻት ነው፡፡ ጨረሰችና ደብዳቤውን ወደመሬት ጣለችው›
‹‹አንብቤያለሁ ግን ምንም አልገባኝም››
‹‹እኔም እኮ አልገባኝ ብሎ ነው የጠራሁሽ..አንቺ ምን አልባት የልጅነት ጓደኛው ስለሆንሽ ጠባዩንና ድርጊቱን ከኔ በተሻላ ትረጂያለሽ ብዬ ስለማስብ  እንድታስረጂኝ ነበረ  …አንቺ ግን መልሰሽ እኔን እየጠየቅሽ ነው፡፡››
‹‹ቀስ ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና እየተጎተተች ሄዳ ከልዩ  ጎን ተዘረፈጠች…..የውስኪውን ጠርሙስ አንስታ ልትጋተው ወደላይ ስታነሳ..ልክ አንደ እግር ኳስ በረኛ ካለበት ተንደረድሮ ሸርተቴ በመግባት ከእጇ ላይ ቀለበው…
‹‹ምን ነካሽ..?እርጉዝ እኮ ነሸ››
‹‹ይቅርታ መድህኔ …ግራ ስለተጋባሁ ነው..እንዴት ነው ቃል ህይወቱን ጥሎ፤ ስራውን ጥሎ፤ አባቱን ጥሎ፤ እኛን ጥሎ ገዳም  የገባው…ገዳም መግባት ማለት ምን ማለት ነው…?››የመለሰላት የለም…..
መድህኔ ከሁለቱም ፊት ለፊት ቆሞ በጭንቀት እያፈራረቀ እያየቸው ነው..ምን እየተሰማው እንደሆን ልቡ ውስጥ ገብታ ማንበብ ብትችል ደስ ይለታል ..የድሮ ፍቅረኛውና የአሁኑ እጮኛው ሌላ ወንድ ጥሎን ገዳም ገባ በሚል ሰበብ ስብብርብር ብለው እንዲህ ሲነፈርቁ….በጣም ከባድ ነው……፡፡
‹‹የእኔ ፍቅር በቃ አንተ ወደስራህ ሂድ…..››
‹‹እንዴ እንዲህ ጥያችሁ እንዴት…..››
‹‹ግድ የለህም ..ሂድ ..እኛ ምንም አንሆንም…››
‹‹እውነቷን ነው እንደውም ብቻችንን ብትተወን ውለታ እንደዋልክልን ነው የምቆጥረው…›.አለችው
‹‹በቃ..የሆነች አጭር ስብሰባ አለቺብኝ..እሷን እንደጨረስኩ ተመልሼ እመጣና ወሰድችሓለው…፡፡
‹‹ሚስትህን መጥተህ መውሰድ ትችላለህ ..እኔ ግን የማድረው እዚህ ነው….ባይሆን ለእማዬ ደውለህ የሆነ ምክንያት ስጣትና እንደማድር ንገርልኝ››
እኔም እሷን ጥያት ስለማልሄድ ..ለዛሬ ተወን..ከፈለግንህ እንደውልልሀለን…› አለችው…››ጊፍቲ
‹‹ካላችሁ እሺ…ስልክሽ ግን እንዳይዘጋ….ቻው››   ቅር እያለው ወጥቶ ሄደ
የእግሩ ኮቴ መራቁን አረጋግጠው ሁለቱም የተነጋሩ ይመስል   እርስ በርስ ተቃቀፍና እየነፈረቁ ማልቀስ ቀጠሉ….ልክ የጋራ ቅርብ ዘመዳችው ሞቶ  ተረድተው ነው የሚመስለው….
‹‹በጣም አፍቅሬው ነበር እኮ……››አለቻት
‹‹አዎ ጠርጥሬ ነበር…በጣም አዝናለሁ››
‹‹እሺ አሁንም ምን ይሻለኛል….?እንዴት ነው የማደርገው?››
‹‹እኔ አላውቅም የእኔ ማር..እኔም ያለእሱ ምክርና ማበረታቻ ህይወትን መኖር አለመድኩበትም…እንዴትም እንደሚዘለቅ አላውቅም….››>
ማኒቲሱ የሚባል ነፍሳት አለ፡፡ የፌንጣ ዝርያ ነው፡፡የፍቅር ታሪካቸው በጣም ልብ ሰባሪ ነወ፡፡ ሴቷ ወንድ ዙሪያውን በመሽከርከር ስትደንስና ክንፎቾን እያማታች ስታማልልው  የወንዱ ስሜቱ ቀስ በቀስ ተነቃቅቶ በፈቅር ቅልጥልጥ ይላል..ከዛ እራሱን ከግንድና ካገኘው ጠንካራ ነገር ጋር ደጋግሞ ባማጋጨት ከሌላው ሰውነቱ በመለየት ቀንጥሶ ይጥለዋል..ምክንያም እንደዛ ሲያደርግ ብቻ ነው ከእሷ ጋር ወሲባዊ ተራክቦ በማድረግ ከውጥረቱ መርካት ሚችለው…..እና እንዳሰበው ከፍቅር መቅደስ ገብቶ ወሲባዊ መዝምር ዘምሮ …ፍፅማዊ እርካታ ይረካል..ግን ወደህይወት መመለስ አይችልም….ዳግመኛ የተቀነጠሰ አንገቱን ለብቻው ከተዘረረ ሰውነቱ ጋ የማጣበቅ ምንም አይነት ተፈጥሮአዊ ችሎታ የለውም..በዚህም ምክንያት የህይወት ፍፃሜው ይሆናል፡፡
‹‹እና ምን ማለት ነው?››
እኔም እንደዛ ሆኜለሁ…እንደሴቷ ሳይሆን እንደወንዱ…ቃልን አገኛለሁ ብዬ በክንዱ እቅፍ ውስጥ ለአንድ ቀን እንኳን ለመግባትን በፍቅር ትንፋሹን ለመማግ ቋምጬ አንገቴን ከሌላው ሰውነቴ ቀንጥሼ ጥያለሁ..ግን የሚገርመው እንደ ፌንጣው እንኳን የአንድ ቅፅበት እድል አላገኘሁም…ከእነ ፍቅር አምሮቴ ሕይወቴ አከተመላት…ይህ ከበደል ሁሉ የከረፋ በደል ነው፡፡ይቅርታ ማያሰጥ  ሀጥያት  ነው  የፈፀመብኝ››
‹‹ተይ ተይ ከእግዚያብሄር ጋር ለምን ታላትሚዋለሽ..››አለቻት ለቃል በመቆርቆር
‹‹እና ከሰይጣን ጋር ላድርገው..የሄደው እግዚያብሄርን ብሎ አይደል…?ታዲያ እግዚያብሄር ከእኔ ጋር የጀመረውን ጉዳይ አያውቅም ..እሱን ለማግኘት በመቋመጥ አንገቴን ከአከላቴ ቀንጥሼ መጣሌን አላየም..ተው    ግዴለህም እዛው ቆይላት አይለውም ነበር፡፡››

ይቀጥላል