‹‹ሪች አመሰግናለሁ…..ታውቂያለሽ እኔም ወደሻለሁ…ግን ዳግመኛ እቴቴን አንገት ከማስደፋ እኔ አንገ | አትሮኖስ
‹‹ሪች አመሰግናለሁ…..ታውቂያለሽ እኔም ወደሻለሁ…ግን ዳግመኛ እቴቴን አንገት ከማስደፋ እኔ አንገቴን ቀንጥሼ ቢያበቃልኝ እመርጣለሁ….እና ቀድመሽ እዚህ ውሳኔ ላይ ስለደረሽም ሆነ ወደሀገርሽ ተመልሰሽ ለመኖር ስለወሰንሽ ምን ያህል ደስተኛ እንደሆንኩ አታውቂም፡፡ብዙ ነገር ነው ያቃለልሺልኝ፡፡››
‹‹ለማንኛውም የፊታችን እሁድ ሁላችንም እንመጣለን….የዛን ጊዜ ቀሪውን እናወራለን››
‹‹እሺ ሪች ደህና እደሪ…ተአምርን ሳሚልኝ›
‹‹እሺ ደህና እደርልኝ›ስልኩ ተዘጋ…..የሆነ ዥው ነው ያለብኝ፡፡ከሪች የሰማዋቸው ነገሮች ሁሉ ያልጠበቅኮቸውና በጣም ያስደሰቱኝ ናቸው…ከማውቃት የተለየች በሳል ሴት ሆና ነው ያገኘኋት፡፡ሰው በስድስት አመት ይሄን ያህል ይቀየራል….?እኔስ በእሷ መጠን በስዬ ይሆን?.እራሴን የጠየቅኩት ጥያቄ ነበር?መልሱ አኔ እንጃ ነው፡፡
ይቀጥላል