Get Mystery Box with random crypto!

#የዘርሲዎች_ፍቅር ፡ ፡ #በፍቅረማርቆስ_ደስታ ፡ ፡ #ክፍል_ስምንት ጎይቲና ካርለት እንጨታ | አትሮኖስ

#የዘርሲዎች_ፍቅር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


#ክፍል_ስምንት


ጎይቲና ካርለት እንጨታቸውን ለቃቅመው አስረው፤ ዛፍ ስር
ተቀምጠዋል ነፋሻ ነው ቀኑ ፀሐይዋን ግን ባዘቶ ዳመና እየሸፈናት ሽቅብ ወደ ቡስካ ተራራ ያቀናል" እፅዋቱ ይወዛወዛሉ ወፎች ያዜማሉ ጎይቲም ታዜማለች ... ካርለት ደግሞ ህብረ ዝማሬውን ህሊናዋን ከፍታ ትቀዳዋለች

"ይእ ዛሬ ማታ ትልቅ ፌስታ እኮ ነው"

"ለምን?"

"አያ ደልቲ ከብት ይወጋላ! ከዚያ እየተበላ: ሸፈሮ ቡና
እየተጠጣ ይቆይና ማታ ሰማዩ ላይ በምትዋኘው ጨረቃ ልብሽ ስውር
ብሎ ጫካ እስኪገባ መጫወት ነው! ብላ ጎይቲ ከተቀመጠችበት ተነስታ እያቀነቀነች ዳሌዋን በማዞር መደነስ ጀመረች ጎይቲ ልቧ በሃዘን የተሰበረ ቢሆንም እራሷን ለማስደሰት
የምታደርገውን ጥረት ካርለት ስታይ አይ የሰው ልጅ ለምን ይሆን
ከደስታ ጊዜ ይልቅ በመከራው ጊዜ መዝፈን የሚወድ? ብላ ስታስብ


"ይእ ቁጭ ብለሽ
ታያለሽ?" ጎይቲ ካርለትን ሳቅ ብላ "ጠየቀቻት

ካርለቴ!- ልጃገረድ
ዳንስ አይታ አስችሏት ተመልካች ትሆናለች ቢባል ማን ያምናል!"

ጎይቲ እንደ ወንዶች እየሰገረች በማቀንቀን ካርለትን እንደ ልጃገረድ ደንሽ አለቻት ተነሳች ካርለት እየተሳሳቁ እንደ ወንድና
ልጃገረድ እየሆኑ ሲደንሱ ቆዩና ሮጠው ከስኬ አሸዋ ሄዱ  እዚያም
ዘፈኑን አስነኩት ከዚያ ጭሮሽ ውሃው ጎን ጎይቲ የተፈጨውን የካሮ አፈር አውጥታ በጥብጣ ካርለትን

"ይእ! ነይ ልቀባሽ?" አለቻት

"ልቀባ ብለሽ ነው ጎይቲ?"
ታሾፊያለሽ ይሆን? ዛሬማ መቅበጥሽ የት ይቀራል!"

"ከማን ጋር  ጎይቲ?"

"ይእ ተአንበሳሽ ነዋ!"

"እሱማ ተቀይሞኝ ሄዷል ..."

"ይእ! አያ ደልቲ እንዳስቀየምሽው እንደናሱ
(የጎሳው አባል ብትሆኝ ኖሮ ይመታሽ ነበር አንች ግን ፀንጋዛ (ባዕድ) ነሽ
ከብት ዝላይ ላይ ወይም ታገባሽ በኋላ ካልሆነ ዝንብሽንም እሽ ማለት ስለማይችል ራቅ ብሎ ብስጭቱን ሊያቀዘቅዝ ነው የሄደ‥

የሐመር ወንድ ሲቀየም እንደ አንበሳ ነው ጎምለል ብሎ ጫካ ይገባል እንጂ እንደ ሴት ቃል መለዋወጥ አይወድም ወይ ይማታና
ካለበለዚያም ከአጠገብሽ ይሄድና በኋላ ሁሉንም ረስቶ ይመጣል ወንድ ቂም ሲይዝ ነውር ነው!''

"እኔና ደልቲም ዛሬውኑ እንታረቃለን በይኛ?"

ይእ! እየነገርሁሽ የሐመር ወንዶችን ባህሪ ልቅም አድርጌ ነው የማውቀው" በረቱ በከብት የሞላ የአባቱን ጠላት የገደለ
የሐመር ወንድ ልቡ እንደ ክረምት ወንዝ ሞልቶ የተንቸረፈፈ ነው አያ ደልቲ እንዲያ ስለሆነ ነው ሲንጎማለል ሲያገሳ ሲጨብጥ ልቡ እንደ አዙሪት አሽከርክሮ ሳንቃ ደረቱ ላይ የሚጥል" አለቻት

"ዛሬ እድለኛ ነኛ! ካርለት ሳቅ ብላ ጎይቲን አየቻት

"ይእ! ዛሬማ የልብሽ መቦረቂያ ቀን ናት አያ ደልቲ ያን ሁሉ ጎጆ አልፎ አንች ዘንድ ለምን መጣ?ውሃ አምጭልኝስ ብሎ
ለምን ላከሽ  ሞኝት! ተኝቶ አልሞሻል ማለት ነው ተዚያ ህልሙን ሊያይ መጣ አየሽ  ስትንቀሳቀሽ ደግሞ ዳሌሽን ማዬት ፈልጎ ውሃ አምጭልኝ ብሎ ላከሽ  ህልሙ እውን መሆኑን አረጋግጦ
በዐይኖቹ የሚያረግደውን ሰውነትሽን ጎረሰው  ያን ጉርሻውን ማታ ጫካ መካከል ወስዶሽ እስቲውጠው ሲያመነዥከው ያመሻል  ዛሬ ማታ በጨረቃ ድባብ የአያ ደልቲ የጥም መቁረጫ አንች ነሽ!" ጎይቲ
በተናገረች ቁጥር ልቧ ቅልጥ ብላ የፈሰሰች ያክል ሰውነቷ ዛለ ዐይኖችዋ ተስለመለሙ ካርለትም ጎይቲ በተናገረችው ጎመጀች  ጮማ እንደሚያኝክ ሰው አፏ ደስ በሚል ፈሳሽ ተሞላ

"ጎይቲ ዛሬ አንች ለምን ከእሱ ጋር አትቀብጭም?"

"ይእ! እንዲያ በይኝ!" ብላ ጎይቲ እያጨበጨበች ሳቀችና

  "ምነው ካርለቴ ይኸማ ነውር ነው!" ብላ ኮስተር አለች

ካርለት ኮስተር ብላ ስታያት ስሜቷ ተምታታባት ኦ!
አምላኬ አጠፋሁ ይሆን! ጎይቲ ያለችው ከሐመር ማህበራዊ ህይወት
ጫፍ ላይ ነው ካላረገዘች
ተደግፋ ወደማትነሳበት
ገደል ትወድቃለች ስለዚህ
ምን አልባት የመውለድ ችግሩ የከሎ ከሆነ ብላ አስባ

"ጎይቲ ምን ችግር አለው - እስቲ ማህፀንሽንም ፈትሽው”?"

ካርለቴ በሆነማ በማን እድሌ የአባቴ ደንብ ግን አይፈቅድም" ብላ ትክዝ አለችና" ከሎ ስንቱን  የለመድሁትን ህይወት ነስቶኛል የእኔ በደል ግን የከፋ ነው ልጅ ወልዶ እንዳይስም በልጅነቱ የተሰበረው ልቡ እንዳይጠገን አደረኩት ያ
በደሌ አንሶኝ ደሞ ከደሙ ውጭ ልክዳው! የአባቴን ደንብ ከምሽር: የእሱን እምነት ከማጣ አሁኑኑ ጦሽ ብዬ እንደ ወፍ እንቁላል ለምን አልፈርጥም አለች
ካርለት የምትናገረው  ጠፋት ጓደኛዋ: አዛኝዋ መካሪዋ ጎይቲ አንተነህ ፅልመት ሊውጣት እየገሰገሰ ገው እሷ ደግሞ
በጓደኝነቷ ወደ ብርሃኑ ስባ ልታስቀራት ትፈልጋለች ከእሷ ጉተታ ጎን ባህልና ደንብ ፅልመቱ ውስጥ ሆኖ ጠምጥሞ አስሮ ወደ እሱ
እየሳባት ነው" ጎይቲ ህይወቷ በጨለማ አይዋጥም ባለኝ አቅም
ሊጥላት ከሚስባት ጋር እሳሳባለሁ ... እያለች ካርለት ስታስብ

"ካርለቴ ዙሪ ላሸክምሽ?"  ብላ ጎይቲ እንጨቱን አሸክማት የራሷንም ተረዳድተው ተሸክማ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ጎይቲ
እያንጎራጎረች እየተሳሳቁ ከኋላ በጨሌ የተሽቆጠቆጠውን የፍዬል
ቆዳቸውን እያወናወኑ የማታ ጀምበር ሳትጠልቅ ለመድረስ ወደ መንደራቸው ሄዱ።

ካርለትና ጎይቲ መንደር ደርሰው ዕረፍት ከወሰዱ በኋላ ጎይቲ ካርለትን ጉያዋ አስገብታ ፀጉሯን በካሮ አፈር እንደገና እጣንና ቅቤ
አላቁጣ ስታለሳልስላት አንድ ጊዜ የሴት ጩኸት ሰሙና ተሯሩጠው
ሄዱ ጩኸቱን ወደሰሙበት  አቅጣጫ ኮቶ ቀደም ብላ የአየችውን በምልክት እያሳየቻቸው አፏን በመተምተም ዝም በሉና ተደበቁ ብላ በጆሯቸው አንሾካሾከችላቸው"
ሸረንቤ ሚስቱን ጎንበስ አድርጎ እየገረፉት ነው ካርለት ያን ስታይ ስቅጥጥ አላት" ኮቶና ጎይቲ ግን አስቂኝ ትርኢት እንደሚያዩ
ሁሉ በሳቅ ይፍነከነካሉ

ጎይቲ ለምን ይመታታል?" ካርለት አካሏ በፍርሃት
እየተንገጫገጨ ጠየቀቻቸው"

"ይእ! ሚስቱ አይደለች,"

"ብትሆንስ? አለች ካርለት ዐይኗን በየተራ ወደሁለቱም
አቅጣጫ እያንከራተተች ኮቶና ጎይቲ በካርለት ጥያቄ ሳቁባት

ይእ! ሴት ስትገረፍ ጥሩ ነዋ!" አለች ኮቶ ፈገግ በማለት ወደ ካርለት ዞራ

"ለምን?" የካርለት የግንባር ቆዳ ተጨማደደ ፊቷ ጨው
እንደነሰነሱበት ሁሉ ነጣ

"ይእ! ደግማ አታጠፋማ  ደሞ መመታት ፍቅር ነው ሴት ልጅ ባሏ ዘንድ ስትመጣ እንደ ዱባ ድፍንፍን ብላ ነው ድቡልቡሉን የሴትን ልጅ ልብና ጭን የሚበረግደው ግርፊያ ነው" ብላ ሳቀች ኮቶ

"አሁን እናንተ ስትመቱ ደስ ይላችኋል?"

"ይእ! ግርፊያ አይነት አይነት አለው በዓይነቱ ተሆነ:
ናፍቀሽ ከጠበቅሽው ደስ ይላል ለምን ደስ አይለን" አለች ኮቶ ጎይቲ ግን ዝም አለች

"አንችስ ጎይቲ?"


"እኔማ እድሜ ለእንዳንች አይነቱ ብመኝስ የታባቴን አገኘዋለሁ  እንደምትታለብ ላም አንገቴን በዚ
ለስላሳ የህፃን እጁ ይሸኝ እንጂ  እይ ይልቅ! ተመልከቱ የሚያረጋትን ..." አለች ጎይቲ ግርፊያውን በጉጉት እያየች

ሸሮምቤ ሚስቱ የሆነ ነገር ስትቀባጥር ከቆየች
ግርፊያውን አቁሞ ቀና በይ? አላት አርጩሜውን ወርውሮ በሾርቃ ከተቀመጠው ቅቤ በቀኝ እጁ ጣት ጠንቁሎ ጀርባዋን ቀባ ቀባ አደረገላት„ ሚስቱ ግን ቆጣ ቆጣ ትላለች እንባዋን እየጠረገች።

ካርለት ለተገረፈችው ሴት አዘነችላት በመጨረሻ ግን እጅዋን ጎትቶ ወደ ጎጆው ይዟት ገባ ጎይቲና ኮቶ ተያይተው ከልባቸው
ተሳሳቁ

"ምንድነው?" ካርለት የባሰ ግራ ተጋባች

"ይእ! ቆጣ ቆጣ ስትል አላየሻትም አሁን ትንሽ ቆይተሽ ብታያት ቁጣዋ በደስታ ተተክቶ ታገኛታለሽ "