Get Mystery Box with random crypto!

#የዘርሲዎች_ፍቅር ፡ ፡ #በፍቅረማርቆስ_ደስታ ፡ ፡ #ክፍል_ሦስት ካርለት መሳተፍ የማትችለውን | አትሮኖስ

#የዘርሲዎች_ፍቅር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


#ክፍል_ሦስት

ካርለት መሳተፍ የማትችለውን የሽማግሎች ስብሰባ በርቀት
እየተመለከተች አልፎ አልፎም የካሜራ ችፕስ  በተደረገበት ባለዙም ካሜራዋ ፎቶ ስታነሳ ቆይታ ጎይቲን ፍለጋ ወደ መንደር
ተመለሰች

"ካርለት ነጋያ ... ነጋያ ... ያ ፈያው" አሉ ህፃናት የካርለትን ነጭ እጅ ለመያዝ እየተሽቀዳደሙ "ነጋያኒ  ጎይቲ ዳ! ደህና ነኝ
ጎይቲ አለች ብላ ጠየቀቻቸው በሐመርኛ

"እእ  ዳኒ" አለች አንዷ ህፃን ራሷን ዝቅ አድርጋ ሽቅብ
በመናጥ አለች ለማለት ካርለት  መዝጊያ ወደሌለው መግቢያ ጎንበስ ብላ በጠባቧ በር ወደ ውስጥ ስታይ ምርግ በሌለው የእንጨት መከታ መሐል ለመሐል በሚገባው ብርሃን ጎይቲ በርከክ ብላ እጆችደ
ከወፍጮው መጅ ላይ ሳይነሱ ራሷን ብቻ ወደ በሩ መልሳ አየቻትደ ካርለት የጎይቲን ማራኪ ፈገግታና የምትወደውን ጥርሷን ስታይ የደስታ ስሜት ውርር አድርጓት እሷም ሳቀች  ተሳሳቁ"

"አርዳ?" አለች ጎይቲ በአንገቷ እንደምትስባት ሁሉ አገጯን ወደ ታች እየሰበቀች ካርለት ፈገግ እንዳለች እሷን፥ ከኋላዋ
የተንጠለጠሉትን የቁርበት ልብሶች ግርግሙ ላይ የተንጠለጠሉትን
ዶላዎች (የወተት መያዣዎች) ግልጥጥ ያለውን የምድጃ ፍም:
በቀበቶው ጉጥ ላይ ቁልቁል የተንጠለጠለውን ክላሽንኮቭ ጠመንጃ
ልጆች አመዱን በውሃ በጥብጠው መግቢያው ጥግ ባለው የግድግዳ
ልጥፍ ላይ ያዩትን ለመሳል ያደረጉትን ጥረት ... በዐይኗ ስትቃኝ.

"አርዳ!" አለች ጎይቲ ደግማ አትገቢም! ለማለት ቃሉን ረገጥ አድርጋ።

"ፈያኔ" ብላ ካርለት እንደ ጅራት ከኋላዋ የተንጠለጠለውን
የፍዬል ቆዳዋን በግራ እጅዋ ወደ እግሮችዋ መሐል አስገብታ ቀኝ
እግሯን በማስቀደም በጠባቧ በር ሹልክ ብላ ገባች የሐመር ቤት
መዝጊያ የለውም  ቀንም ሆነ ማታ እንግዳ የአባት ሙት መንፈስ ከመጣ ሁሌም ሳይጠብቅ: ደጅ ሳይጠና ሰተት ብሎ መግባት አለበት ትንሽዋ በር ደፍዋ ከፍ ያለ በመሆኑ ለከብትም ሆነ ለአውሬ
ለመግባት አታመችም ቤት ለሐመሮች መቀመጫና መተኛ እንጂ መቆሚያ  አይደለም"  ሁሉም ነገር ትርጉም  ሊኖረው ይገባል
ስለሆነም ካለ ህፃናት በስተቀር በጣም አጭር ሰው እንኳ ጎንበስ ብሎ
ካልሆነ መቆም አይችልም ይህ የሆነው ደግሞ እንጨት ጠፍቶ ቦታ
ጠቦ ሳይሆን ለትርጉሙ ነው"

"ጎይቲ?"

"ዬ!"

ምነው ዛሬስ ስትፈጭ መዝፈን: ማንጎራጎሩን ተውሽው?" ብላ ጠይቃት ካርለት ፈገግ ብላ ጎይቲን ሳመቻት እንደ
ሐመር ሴቶች የልብ ሰላምታ ጎይቲ ካርለት ለጠየቀቻት መልስ  ሳትሰጥ አንገቷን ደፍታ እጅዋ ወፍጮው
መጅ ላይ እንዳለ በተመስጦ ስታስብ ቆይታ በቀኝ እጅዋ ማሽላውን ግራና ቀኝ ሰብስባ  ወደ ወፍጮው ጥርስ አስገብታ
ወገቧን ወደ ኋላና ወደ ፊት
እያረገረገች "ሸርደም: ሸርደም አድርጋ ፈጨችውና ብርኩማዋ ላይ ተቀመጠች
ከዚያ እኒያን ሐጫ በረዶ የመሳሰሉ ጥርሶችዋን
ገልጣ ለዓመል ያህል ፈርጠም አለችና

"ይእ!ካርለቴ ኧረ አሁን ሳንጎራጉር ነበር መቼ
እንጉርጉሮዬን እንደ አቆምኩት ግን እንጃ! አዝኜ እንኳን ቢሆን ሁልጊዜ መፍጨት ስጀምር እህሉ ከታች ሲደቅ እኔ ከላይ ትዝታዬን እየጨመርሁ እንጉርጉሮዬን አቀልጠው ነበር አሁን እኮ ኮቶ እግሯ
ወጣ ከማለቱ ነው አንች የመጣሽ ከኮቶ ጋር እየተከራከርን ሁላ እዘፍን ነበር  በኋላ ግን ኮቶ ለመሄድ ስትቁነጠነጥ እያወራች እንድትቆይ ብዙ
ክርክር ገጠምኋት
ታውቂያታለሽ ተከራክራ ተከራክራ ካልረታች እንደ ፍየል ልዋጋ ስትል ታስቀኛለች ስለዚህ ጥላኝ ከምትሄድ ብዬ ነገር ጀመርኋት

"ኮቶ ከተማ አትሄጅም?" ስላት

"ይእ! ኧረ ምን አልሁሽ እቴ እኔስ ያገሬ ጅብ ይብላኝ
አለችኝ ትንሽ ላስለፍልፋት ብዬ እኔ ግን መበላቴ ታልቀረ የጅብ ዘመድ አልመርጥም አልኋት አይምሰልሽ ጅሊት! ያገርሽ ጅብ ገሎ ነው የሚበላሽ  የሰው አገር ጅብ ግን እየበላ ነው የሚገልሽ ስትለኝ ይእ! አንች ምነው ታልጠፋ አውሬ ጅብን እንዲህ ዘመድ
አዋቂ አደረግሽው?
አልኳት‥ ይሄ እንኳ ምሳሌ ነው ስትለኝ ሞጥሟጤ  ምሳሌሽን ቀይሪያ!ታለበለዚያ ካለ
ጥንባቸው ሌላ
የማያውቁትን ጅቦች ካለስማቸው
ስም ሰጥተሽ ቅዱስ አድርገሽ ታውሬው ሁሉ አታቀያይሚያቸው" ብላት ወገቤን ደቅታኝ ሹልክ ብላ ሄደች ከዚያ ማንጎራጎር ጀምሬ ነበር ወዲያው ግን ድምፄ ለከት የለሽ ሆኖ ልቤ ግንድ የሚያመሽክ ምስጥ ይርመሰመስበት ጀመር

"ምን ሆነሽ ነው ጎይቲ የምን ጭንቀት ነው?"

"ወደው አይስቁ አለ ያገሬ ሰው ..." ብላ ጎይቲ ከትከት ብላ ስቃ።

"ይእ! ምነው እንዳንች ጅል ሆኜ እድሜ ልኬን ስጠይቅ
በኖርሁ" ስትላት ተያይዘው እንደገና ተሳሳቁ

"ካርለቴ! እውን ሴት ልጅ እግርና እጅዋ የሚያጥረው፥
ቀትረ ቀላል ሆና ድምጿ የሚሰለው ... ለምን እንደሆን አታውቂም?

"አላውቅም ጎይቲ ለምንድን ነው?"

"ይእ! እንግዲያ ዝናብ እንደበዛበት ማሽላ ታለ ፍሬ መለል ብለሽ ያደግሽ አገዳ ነሻ! ሙች አንችስ ተህፃን አትሻይም አንቺ እኮ! ተንግዲህ ወዲያ ትልቅ ሰው ነሽ! ጉያሽና ልብሽ ላይ የትዝታ ምሰሶ የተተከለ
ፈጭተሽ የምታበይ ጭሮሽ ውሃ ቀድተሽ ለጥም
መቁረጫ የምታጠጭ
የወንድ ልብ ሲጎመራ ጫካ መሃል ገብተሽ የምትካፈይ
ፍቅርሽን እንደ ህፃን ልጅሽ የምትግች ትልቅ ሴት እኮ ነሽ?" ትልቅ ሴት እኮ ነሽ?"

"ጎይቲ የባሰ ግራ ገባኝ?"

"ይእ! እንዲያ ይሻላል! ቁም ነገር አታውቂም ብዬ ተመንገር ሌላ እህ ላሳይሽ?"  ብላ ጎይቲ በአድናቆት ጨብጨብ ጨብጨብ አድርጋ በሣቅ ተፍለቀለቀች

ካርለት ከተቀመጠችበት
ፈገግ ብላ ተነስታ ጎይቲን ገፋ አድርጋት የወፍጮውን መጅ በግራ እጅዋ ይዛ ከሾርቃው በቀኝ
እጅዋ ማሽላውን አፍሳ ጨምራ

"እሽ እኔ እፈጫለሁ አንች ንገሪኝ?" አለቻት

"ይእ! እውነት ታላወቅሽውማ እነግርሻለሁ  እንጂ ብላ እግሯን ዘርግታ ቁርበቱ ላይ ቁጭ አለች ጎይቲ ወደ ቁምነገር
ስትመለስ የሚያስጨንቃትን
ለመናገር ስትዘጋጅ ውስጧን የሚጎማምደው ችግሯ የፈገግታ ፀዳሏን እየቸለሰ አከሰመው ደሟ
እንደቀትር ማዕበል ደረቱን ገልብጦ እየዘለለ በመፍረጥ አረፋ ደፈቀ
ታወከ
"ሐመር ላይ ሴት ልጅ የግል ችግር የለባትም እምትበላውን መሬቷ እምትጠጣውን ላሞች: ፍቅርን ደግሞ የሐመር ወንዶች እንደ ማሽላ ገንፎ እያድበለበሉ ያውጧታል ሴት ልጅ ወንዝ
ብትሄድ እንጨት ለቀማ ጫካ ብትገባ እህል ልታቀና ገበያ ብትወጣ ብቻዋን አትሆንም ሰው ከብቶች: ዛፎች አሉላት ሴት ብቻዋን ችግር የሚገጥማት የማትወልድ ስትሆን ነው መሐንነት ትታይሻለች ያች ፀሐይ " ዝቅ ብላ በግርግዳው ቀዳዳ ጮራዋን ፈንጥቃ የምትንቦገቦገውን የረፋድ ፀሐይ እያሳየቻት

"ይኸውልሽ መሐንነት ያችን በሙቀት የምትነድ እሳት ዘላለም እንደ ጨቅላ ህፃን ደረትሽ ላይ ታቅፈሽ መኖር: ታቅፈሽ መሞት ነው" ተዚያ እድሜ ልክሽን መቃጠል: መንደድ ነው"

"መሐንነቱ የመጣብሽ ሳታስቢው የሴት ብልትሽን ውሃ ነክቶት ይሆናል ሆን ብለሽ ባታደርጊውም ትዕዛዝ ነውና ቅጣቱ ቃጠሎው ወደ ገለብ ብትሮጭም አታመልጭውም ስትቃጠይ ደግሞ ሰው የሻጉራ እያዬ ይሸሽሻል ባይሆን ከቃጠሎሽ  ባይጠቅምሽም
ለእነሱም ባይጠቅማቸውም ለአባትሽ ለእናትሽ ለእህትሽ
ለዘመዶችሽ ታካፍያቸዋለሽ የተረገመ ቤተሰብ እያሰኘሽ" ብላ ዝም አለች ጎይቲ  እንደተላጠ ጣውላ ሰውነቷ ሟሾ

ግዙፍነት ለካ በአጥንትና ስጋ ብቻ አይደለምና  መጠንም በህሊና ይወሰናል ውበትና ቁመና ህሊና በሚፈጥረው መተማመን ተገዥ ነውና! እያለች ካርለት ጎይቲን እያየች ስታስብ