Get Mystery Box with random crypto!

#MizanTepiUniversity ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አመራር ተመድቦለታል። ዋቆ ገዳ | ATC NEWS

#MizanTepiUniversity

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አመራር ተመድቦለታል።

ዋቆ ገዳ (ዶ/ር) የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበዋል።

ተረፈ ጌታቸው (ዶ/ር) ተጠባባቂ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት፣ ግርማ ጥላሁን (ዶ/ር) ተጠባባቂ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት እንዲሁም ይደግ ማሞ ተጠባባቂ የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ እና የቢዝነስ ልማት ም/ፕሬዝዳንት ሆነው መመደባቸው ተገልጿል።

አዲስ የተመደቡት አመራሮች ለአንድ ዓመት ተቋሙን እየመሩ እንደሚቆዩና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ምልመላ መመሪያ መሠረት ወደፊት በሚወጣ የውድድር ማስታወቂያ የቋሚ አመራሮች ምርጫ ይደረጋል ተብሏል።

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news